#አቢሲንያ_ባንክ_ለሚሰጣቸው_ከወለድ_ነፃ_የባንክ_አገልግሎቶች_መሰረታዊ_የሆኑ_መረጃዎች
//
📌 አቢሲንያ ባንክ ከወለድ ነፃ የሚሰጣቸው የተቀማጭና የተንቀሳቃሸ ሂሳቦች ምን ምን ናቸው⁉️
አቢሲንያ ባንክ የሚከተሉትን የቁጠባና የተንቀሳቃሽ የባንክ አገልግሎቶች ለደንበኞች አቅርቧል፡፡
/
ወዲዓህ-ያድ-ዳማናህ የተንቀሳቃሽ ሒሳብ፣
ወዲዓህ-ያድ-ዳማናህ የቁጠባ ሒሳብ፣
የሀጅ የቁጠባ ሂሳብ፣
የባለውለታዎች የቁጠባ ሂሳብ /ሙሲኒን/፣
የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ /ፊቲያህ/፣
የሴቶች የቁጠባ ሂሳብ /ዘህራህ/፣
የዲያሰፖራ ሂሳብ /በውጭ ምንዛሪ የሚከፈት/፣
የልጆች የቁጠባ ሒሳብ ናቸው፡፡
/
📌 አቢሲንያ ባንክ ለሚሰጣቸው ከወለድ ነጻ #የቁጠባና_የተንቀሳቃሽ_ሂሳቦች የሚከተላቸው የሸሪዓ መርህ ምን ላይ መሰረት ያደረገ ነው⁉️
/
ባንካችን ከወለድ ነጻ ለሚሰጣቸው ለቁጠባና ለተንቀሳቃሽ የሂሳብ አገልግሎቶች የሚከተለው #የሸሪያ_መርህ #አል_ዋዲያ_ያዳማናህ ሲሆን፣
ይህ ውል የደንበኞች ገንዘብን፣ የከበሩ ዕቃዎቸን እና ማስረጃዎቸን በአደራ መልክ መቀበል እንዲሁም በፈለጉት ሠዓትና ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመመለስ ዋስትና የሚሰጥበት የመርህ አይነት ነው፡፡
/
📌 አቢሲንያ ባንክ የሚሰጣቸው ከወለድ ነጻ የተቀማጭ እና የተንቀሳቃሽ የባንክ አገልግሎቶች ያሏቸው ባህሪያት ምን ምን ናቸው⁉️
/
ከወለድ ነጻ የተንቀሳቃሽም ሆነ የቁጠባ ሂሳብ ሲከፈት ገቢ ለሚደረገው ማንኛውም የገንዘብ መጠን በአስቀማጩ /በደንበኛው/ ገቢ የሚደረገው ገንዘብ ምንጭ በሸሪያው ህግ ከተፈቀዱ የስራ መስኮች የተገኘ ለመሆኑ በደንበኛው ፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
ደንበኛው ሂሳብ በሚከፍትበት ወቅት፣ ወጪ፣ ገቢ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን ለመጠቀም በሚመጣበት ወቅት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጁ የሂሳብ መክፈቻ፣ የገቢና የወጪ ቅጾችን መጠቀም ይኖርበታል፡፡
የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በልዩ መልክ የተዘጋጀ የቁጠባ ሂሳብ ይኖራቸዋል፡
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በተለየ መልክ የተዘጋጀ የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ባንካችን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ሂሳብን የሚስተናገደው ከመደበኛው የባንክ ደንበኞች ሂሳብ ጋር ሳይገናኝ ለብቻው በተለየ ሲስተም ነው፡፡
ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች አገልግሎቱን በሁሉም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ብቻ በሚሰጡ የባንካችን ቅርንጫፎች (Dedicated branch) እንዲሁም በሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች ለወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ብቻ በተለዩ መስኮቶች (Window) በመጠቀም፣ አገልግሎቱን በተሟላ መልኩ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በቼክ ለሚንቀሳቀስ የቁጠባ ሂሳብ መነሻ የሂሳብ መክፈቻ የብር መጠን ብር 1,000 (አንድ ሺህ)፣ ለሀጅ የቁጠባ ሂሳብ ብር 25 (ሃያ አምስት)፤ ለሌሎች የቁጠባ ሒሳብ አይነቶች በብር ዜሮ (0) ወይም ያለምንም መነሻ ተቀማጭ ብር መክፈት የሚቻል ሲሆን፣ በወሩ መጨረሻ ላይ ግን የተከፈቱ ሂሳቦች ውስጥ ምንም ተቀማጭ ከሌለ ሂሳቡ ሙሉ በሙሉ የሚዘጋ ይሆናል፡፡
ደንበኛው የኤ.ቲ.ም (ATM)፤ የክፍያ ማሽን (PoS)፤ ሞባይል ባንኪንግ (Mobile banking) ኢንተርኔት ባንኪንግ (Internet banking) መጠቀም ይችላል፡፡
ደንበኛው ያስቀመጠውን ተቀማጭ ብር፤ የከበሩ ማዕድናት እና ማስረጃዎችን ለመውሰደ በፈለገ ሰዓት ባንኩ ለደንበኛው እንደሚሰጥ ሙሉ ዋስትና ይሰጣል፡፡
ደንበኛው በሁሉም የቁጠባ ሒሳብ ውስጥ ያስቀመጠውን ብር በፈለገው ጊዜ የማውጣት ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን፣ በደረጃ ትልቅ እና መካከለኛ ውስጥ የተመደቡ የእቁብ አይነቶች እና ለሀጅ የቁጠባ ሂሳብ ላይ ግን ባንኩ ወጪ ማድረግ የሚቻልበትን የጊዜ ገደብ ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡
የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ /ፊቲያህ/ ደንበኛ እድሜው 29 ሲደርስ የቁጠባ ሂሳቡ ወደ መደበኛ ወዲዓህ-ያድዳማናህ የቁጠባ ሒሳብ የሚዞር ይሆናል::
/
📌 የአቢሲንያ ባንክ የሚሰጣቸውን ከወለድ ነጻ የቁጠባ እና የተንቀሳቃሽ ሂሳቦችን ለሚጠቀሙ ደንበኛ የሚሰጣቸው ልዩ የሆኑ ጥቅማጥቅሞች ምን ምን ናቸው⁉️
/
ባንኩ የወለድ ነጻ ደንበኞችን ተቀማጭ ገንዘብ በመጠቀም ትርፍ የሚያገኝ ከሆነ በባንኩ ውሳኔ መሰረት ለወዲዓህ-ያድ-ዳማናህ የተንቀሳቃሽ እና የቁጠባ ሒሳብ ባለቤቶች ስጦታ ሊያበረክትላቸው ይችላል::
ባንኩ ለሀጂ እና ለኡምራ ተጓዦች ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን የዉጪ ምንዛሪ ያመቻቻል::
የባለውለታዎች፤ የሴቶች እና የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ ባለቤት ለሆኑ ደንበኞች ባንኩ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ከሚያስከፍለው የአገልግሎት ክፍያ ከፍተኛ ቅናሽ ያደርጋል::
ለባለውለታዎች፤ለሴቶች እና ለወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች ያለምንም ክፍያ የኤ.ት.ኤም ካርድ ይሰጣል::
የባለውለታዎች የቁጠባ ሒሳብ ደንበኞች የወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ወረፋ ሳይጠብቁ በልዩ መልክ ይስተናገዳሉ
ለሴቶች የቁጠባ ሂሳብ /ዘህራህ/ ደንበኞች ኤ.ቲ.ኤም ካርዳቸውን በመጠቀም ሌሎች በአንድ ቀን ማውጣት ከሚችሉት የብር መጠን በላይ ማውጣት ይችላሉ፡፡
የሴቶች የቁጠባ ሂሳብ /ዘህራህ/ ደንበኞች ልጅ በሚወልዱበት ሰዓት ባንኩ በተወለደው ልጅ ስም ቁጠባ ሂሳብ በመክፈት ስጦታ ለወላጅ ያበረክታል፡፡
የሴቶች የቁጠባ ሂሳብ /ዘህራህ/ ተጠቃሚ ደንበኞች ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ብቻ በሚሰጡ ቅርንጫፎች በሴት ሰራተኞች ብቻ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
የባለውለታዎች፤የሴቶች እና የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ ደንበኞች ከባንኩ ጋር በአጋርነት ከሚሰሩ የተለያዩ አገልግሎቶችን ከሚሰጡ ድርጅቶች ጋር ለምሳሌ ሆስፒታሎች፤ ሱፐርማርኬቶች፤ የውበት መጠበቂያ ሳሎኖች የመሳሰሉት የንግድ ተቋማት ጋር፣ ዕቃ በአሚን ካርዳቸው ሲገዙ ወይም አገልግሎት በሚያገኙበት ሰዓት በአሚን ካርዳቸው ሲከፍሉ ከዕቃው ዋጋ ወይም ከአገልግሎት ክፍያው ላይ ቅናሽ እንዲያገኙ ባንኩ ያመቻቻል፡፡
#አቢሲንያ_ባንክ_ለሀገር_መከላከያ_ሠራዊት_እና_በጦርነቱ_ለተጎዱ_አካላት_የአስር_ሚሊየን_ብር_ድጋፍ_ሰጠ!
//
ባንካችን የማኅበራዊ ሓላፊነቱን_በመወጣት ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች የብር አስር ሚሊየን (10,000 000) ድጋፍ አድርጓል!
/
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የአቢሲንያ ባንክ ድረ ገጽ https://www.bankofabyssinia.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የአቢሲንያ ባንክ የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/bankofabyssinia ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የአቢሲንያ ባንክ ቴሌግራም ቻናል https://yangx.top/BoAEth ይቀላቀሉ
ለአቢሲንያ ባንክ ኢንስታግራም ምስሎች https://www.instagram.com/abyssinia_bank/
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/abyssiniabank ይወዳጁን
/
እናመሰግናለን!
/
#አቢሲንያ_የሁሉም_ምርጫ!
#እነሆ! #አቢሲንያ_ባንክ_ጊዜፔይ_የተሰኘ_አዲስ_የሞባይል_ዋሌት_አገልግሎት_ለደንበኞቹ_አበረከተ፡፡
//
ጊዜፔይ ቀደም ሲል ደንበኞች ወደባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ የሚያገኙአቸዉን አገልግሎቶች ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን📲 ብቻ በመጠቀም እንዲሁም በአቅራቢያቸው ካለው ህጋዊ #የጊዜፔይ_ወኪል ጋር በመቅረብ የሚገለገሉበት ስርዓት ነው፡፡
/
#ጊዜፔይ_ተጠቃሚ_እንዴት_መሆን_ይቻላል?
⭕️ #የአቢሲንያ_ባንክ_ደንበኛ_ከሆኑ
*817# ላይ በመደወል ወይም https://gizepay.bankofabyssinia.com/dw_customer የሚለዉን ድረገጽ በመጠቀም ወይም የሞባይል መተግበሪያዉን ከጎግል ፕሌይስቶር አዉርደዉ ስልክዎ ላይ በመጫን በቀላሉ ተመዝግበዉ የጊዜፔይ ደንበኛ መሆን ይችላሉ፤
በመቀጠልም ከባንክ ሂሳብዎ ጋር ለማገናኘት (Link Bank Account) የምትለዋን የአገልግሎት አይነት በመምረጥ የአቢሲንያ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥርዎን በማስገባት ያገናኙ፤
በመጨረሻም ገንዘብን ለመጫን (load Money) የሚለዉን በመምረጥ የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን ወደ ጊዜፔይ ዋሌት ሂሳብዎ በማዘዋወር ባንኩ ያቀረበልዎትን የጊዜፔይ አገልግሎቶች መጠቀም ይችላሉ፡፡
/
⭕️ #የአቢሲንያ_ባንክ_ደንበኛ_ካልሆኑ
የታደሰ መታወቂያና ማንኛዉንም አይነት ተንቀሳቃሽ ስልክ በመጠቀም በአቅራቢያዎ ወዳለዉ የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የጊዜፔይ ወኪል ዘንድ ቀርበዉ ገንዘብዎን ወደ ዋሌት ሂሳብዎ ገቢ በማድረግ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ፡፡
/
⭕️ #ጊዜፔይ_ምን_ምን_አገልግሎቶችን_ይዟል
📌ገንዘብ ገቢ እና ወጪ ማድረግ፤
📌ገንዘብ መላክ፤
📌ክፍያ መፈፀም፤
📌የአየር ሰዓት መሙላት፤ እና
ሌሎችም፡፡

#አቢሲንያ_የሁሉም_ምርጫ!
ለተከበሩ የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮን

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ኢካገባ/ምዳ/019/17 በጻፈው ደብዳቤ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 መሰረት በሰነደ ሙዓለ ንዋይ አውጭዎች የተያዙ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤትነት መዝገቦች በማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት በሚዘጋጅ ባለቤትነት በኤሌክትሮኒክ ዘዴ በሚመዘገብበት የሂሳብ መዝገብ ስርዓት መተካት ያለበት በመሆኑ፤ ይህንን ለመፈጸም እንዲቻል የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ባለቤቶችን (የባለአክሲዮኖችን) መረጃ እስከ ታህሣስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ዝግጁ እንድናደርግ አሳውቆናል፡፡
በመሆኑም፣ የፋይዳ ልዩ ቁጥርዎን (FIN)፣ የብሔራዊ መታወቂያዎን ኮፒ፣ የአድራሻ ለውጥ አድርገው ከሆነ አዲሱን አድራሻ፣ ኢ-ሜል፣ ስልክ ቁጥር፣ የቤት ቁጥር፣ ወረዳ፣ ክ/ከተማ፣ ከተማ፣ ክልል እና ሀገር፤ ባለአክሲዮኑ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የወኪሉ ሰው ሙሉ መረጃ በዋናው መ/ቤት 8ኛ ፎቅ አክሲዮን እና ኢንቨስትመንት ክፍል እንዲያሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#አቢሲንያ_ባንክ #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#አቢሲንያ_ባንክ

ይታፈሳል!
ነገ ቅዳሜ ጥር 3 ከረፋዱ 4:30 ቀጣይ ዙር የጥያቄ እና መልስ ውድድር በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ይደረጋል። በየሳምንቱ አስር አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀልና ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ ይሸለሙ!

የቴሌግራም ሊንክ 👇
https://yangx.top/BoAEth

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ