#እነሆ! #አቢሲንያ_ባንክ_ጊዜፔይ_የተሰኘ_አዲስ_የሞባይል_ዋሌት_አገልግሎት_ለደንበኞቹ_አበረከተ፡፡
//
ጊዜፔይ ቀደም ሲል ደንበኞች ወደባንክ ቅርንጫፎች በመሄድ የሚያገኙአቸዉን አገልግሎቶች ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን📲 ብቻ በመጠቀም እንዲሁም በአቅራቢያቸው ካለው ህጋዊ #የጊዜፔይ_ወኪል ጋር በመቅረብ የሚገለገሉበት ስርዓት ነው፡፡
/
#ጊዜፔይ_ተጠቃሚ_እንዴት_መሆን_ይቻላል?
⭕️ #የአቢሲንያ_ባንክ_ደንበኛ_ከሆኑ
*817# ላይ በመደወል ወይም https://gizepay.bankofabyssinia.com/dw_customer የሚለዉን ድረገጽ በመጠቀም ወይም የሞባይል መተግበሪያዉን ከጎግል ፕሌይስቶር አዉርደዉ ስልክዎ ላይ በመጫን በቀላሉ ተመዝግበዉ የጊዜፔይ ደንበኛ መሆን ይችላሉ፤
በመቀጠልም ከባንክ ሂሳብዎ ጋር ለማገናኘት (Link Bank Account) የምትለዋን የአገልግሎት አይነት በመምረጥ የአቢሲንያ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥርዎን በማስገባት ያገናኙ፤
በመጨረሻም ገንዘብን ለመጫን (load Money) የሚለዉን በመምረጥ የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን ወደ ጊዜፔይ ዋሌት ሂሳብዎ በማዘዋወር ባንኩ ያቀረበልዎትን የጊዜፔይ አገልግሎቶች መጠቀም ይችላሉ፡፡
/
⭕️ #የአቢሲንያ_ባንክ_ደንበኛ_ካልሆኑ
የታደሰ መታወቂያና ማንኛዉንም አይነት ተንቀሳቃሽ ስልክ በመጠቀም በአቅራቢያዎ ወዳለዉ የአቢሲንያ ባንክ ቅርንጫፍ ወይም የጊዜፔይ ወኪል ዘንድ ቀርበዉ ገንዘብዎን ወደ ዋሌት ሂሳብዎ ገቢ በማድረግ አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ፡፡
/
⭕️ #ጊዜፔይ_ምን_ምን_አገልግሎቶችን_ይዟል
📌ገንዘብ ገቢ እና ወጪ ማድረግ፤
📌ገንዘብ መላክ፤
📌ክፍያ መፈፀም፤
📌የአየር ሰዓት መሙላት፤ እና
ሌሎችም፡፡

#አቢሲንያ_የሁሉም_ምርጫ!