TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.4K links
加入频道
TIKVAH-SPORT
ከሴካፋ ውድድር አንድ ሀገር ራሷን አገለለች ! በቀጣይ ሳምንት በሀገራችን አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር #ሩዋንዳ በውድድሩ #እንደማትሳተፍ ተገልጿል። የሩዋንዳ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እስከ አሁን ዝግጅት አለመጀመራቸው ሲገለፅ ለውድድሩ ወደ ኢትዮጵያ #እንደማይመጡ ታውቋል። ሩዋንሳ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ ፣ ብሩንዲ ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ጋር ተደልድላ እንደነበረ…
ኤርትራ ራሷን ከሴካፋ ውድድር አግልላለች !

ከ 17ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ከኢትዮጵያ ጋር በአንድ ምድብ የተደለደለችው #ኤርትራ በውድድሩ እንደማትሳተፍ በደብዳቤ አሳውቃለች።

በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ሀገር ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድላ የነበረችው ኤርትራ ለአወዳዳሪው አካል ውሳኔዋን ማሳወቋ ተረጋግጧል።

የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 9/2015 በአበበ ቢቂላ ስታዲየም #በስምንት ሀገራት መካከል የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe