TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ፈረሰኞቹ የሊጉን መሪነት ተረክበዋል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግብ ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በውድድር ዓመቱ አስራ አራተኛ የሊግ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ በደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ ዘጠኝ ነጥቦች በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀድያ ሆሳዕና በበኩላቸው በሀያ አንድ ነጥብ #አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬ ዳዋ ከተማ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ መድን የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ድል ቀንቷቸዋል !

በፈረንሳይ ሊግ የሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ፒኤስጂ ከሊል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ለፒኤስጂ የማሸነፊያ ግቦችን ኔይማር ፣ ኪሊያን ምባፔ 2x እና ሊዮኔል ሜሲ ከመረብ ሲያሳርፉ የሊልን ግቦች ዲያኪቴ ፣ ጆናታን ዴቪድ እና ባምባ አስቆጥረዋል።

የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በውድድር ዓመቱ አስራ አምስተኛ የሊግ ጎሉን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ጆናታን ዴቪድ እና ኪሊያን ምባፔ በአስራ አምስት ጎሎች የከፍተኛ ግብ አግቢነቱን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ጁንዬር አስራ ሶስተኛ የሊግ ጎሉን ባስቆጠረበት ጨዋታ የእግር ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ተቀይሮ ወጥቷል።

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ #በክለብ ጨዋታዎች ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን 699 አድርሷል።

ፒኤስጂ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሊል በአርባ አንድ ነጥቦች #አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፒኤስጂ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ማርሴ እንዲሁም ሊል ከ ብረስት የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን የሊጉን መሪነት ተረክቧል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

- ኢትዮጵያ መድን የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ደርዛ በመጨዋታው መጠናቀቂያ 90+5 ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል።

- ኢትዮጵያ መድን ማሸነፉን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ከቅዱስ ጊዮርጊስ መረከብ ችሏል።

- በጨዋታው የሀድያ ሆሳዕናው ተጨዋች ፍሬዘር ካሳ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል።

- ሀድያ ሆሳዕናዎች ባለፉት ተከታታይ ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።

- በውድድር ዓመቱ ሀድያ ሆሳዕና ያለፉትን ስድስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

- ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #ሰላሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀድያ ሆሳዕና በሀያ አንድ ነጥቦች አራተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከ መቻል የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በጀርመን ቦንደስሊጋ የ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ከተከታዩ ዩኒዬን በርሊን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግቦች ቺፖ ሞቲንግ ፣ ኮማን እና ሙስያላ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የባየር ሙኒኩ ሴኔጋላዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሳድዮ ማኔ ከ110 የጉዳት ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ተመልሷል።

ባየር ሙኒክ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ ስድስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ዶርትመንድን በግብ ክፍያ በልጦ #አንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ዩንዬን በርሊን በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ከስቱትጋርት እንዲሁም ዩንዬን በርሊን ከ ኮሎኝ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ሽንፈት አስተናግዷል !

በስፔን ላሊጋ የሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከ አልሜሪያ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የአልሜሪያን ብቸኛ የማሸነፍያ ግብ ኢል ቢላል ቱሬ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በአሰልጣኝ ዣቪ የሚሰለጥኑት ባርሴሎናዎች በውድድር ዓመቱ #ሁለተኛ የሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ባርሴሎና በሊጉ ደረጀ ሰንጠረዥ ሀምሳ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አልሜርያ በበኩሉ በሀያ አምስት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባርሴሎና ከ ቫሌንሽያ እንዲሁም አልሜሪያ ከቪያርያል የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ድል ቀንቶታል !

በፈረንሳይ ሊግ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ፒኤስጂ ከተከታዩ ማርሴይ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ 2x እና ሊዮኔል ሜሲ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ያስቆጠራት ግብ በእግር ኳስ ታሪኩ ሰባት መቶኛ የክለብ ግቡ ሆና ተመዝግባለች።

የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለፒኤስጂ ሁለት መቶኛ ግቡን በማስቆጠር ከክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኤድሰን ካቫኒ ጋር መስተካከል ችሏል።

ኪልያን ምባፔ በውድድር አመቱ ያስቆጠረቸውን የሊግ ግቦች አስራ ሰባት በማድረስ የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

ፒኤስጂ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ በማድረስ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ማርሴይ በበኩላቸው በሀምሳ ሁለት ነጥብ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፒኤስጂ ከ ናንትስ እንዲሁም ማርሴይ ከሬንስ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ ወሳኝ ድል አስመዝግበዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ሲያስቆጥሩ የድሬዳዋ ከተማን ግብ ቢኒያም ጌታቸው ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- የፈረሰኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ኦሮ አጎሮ በውድድር ዓመቱ አስራ አምስተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- የብርቱካናማዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቢንያም ጌታቸው በውድድር ዓመቱ #ስምንተኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

- ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ በአስራ ስምንት ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | አል ናስር 3-1 አል ባቲን

ግሀሬብ ሎፔዝ
ፋቲል
ማራን

- የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ከ አል ባቲን ባደረገው የሊግ መርሐ ግብር ወሳኝ ድል በማስመዝገብ መሪነቱን አጠናክሯል።

- አል ናስር ከተመሪነት በመነሳት በጨዋታው መገባደጃ ከ 90ኛው ደቂቃ በኋላ ባስቆጠራቸው ሶስት ግቦች ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል።

- አል ናስር በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ ስድስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ አል ኢትሀድ በሁለት ነጥብ ርቆ #አንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- በቀጣይ የሳውዲ አረቢያ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ አል ናስር ከተከታያቸው አል ኢትሀድ ጋር ተጠባቂ ጨዋታቸውን ሀሙስ ምሽት የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል እና ቼልሲ ድል ቀንቷቸዋል !

በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ በርንማውዝ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ቼልሲ በበኩሉ ሊድስን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

- የአርሰናልን የማሸነፊያ ግቦች ቶማስ ፓርቴ ፣ ኔልሰን እና ቤንጃሚን ዋይት ሲያስቆጥሩ ለበርንማውዝ ቢሊንግ እና ሰነሲ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፎፋና ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- አርሰናል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በርንማውዝ በሀያ አንድ ነጥቦች በወራጅ ቀጠናው አስራ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል።

- ቼልሲ በበኩላቸው በሰላሳ አራት ነጥቦች #አስረኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችሉ ሊድስ ዩናይትድ በሀያ ሁለት ነጥብ አስራ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከ ፉልሀም እንዲሁም ቼልሲ ከሌስተር ሲቲ የሚገናኙ ይሆናል።

- በሌሎች የሊግ መርሐ ግብሮች ዎልቭስ ቶተንሀምን 1ለ0 ፣ ብራይተን ዌስትሀምን 4ለ0 እንዲሁም አስቶንቪላ ክሪስትያል ፓላስን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ድል ቀንቷቸዋል !

በፈረንሳይ ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፒኤስጂ ከናንትስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ሊዮኔል ሜሲ ፣ ፔሬራ ፣ ኪሊያን ምባፔ እና ሀጃም በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በውድድር አመቱ አስራ ሶስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረንሳያዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በውድድር አመቱ አስራ ስምንተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፒኤስጂ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ናንትስ በበኩላቸው በሀያ ስምንት ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፒኤስጂ በወራጅ ቀጣናው ከሚገኘው ብረስት የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አሳክተዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ፍሪምፖንግ ሜንሱ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ሲያስቆጥሩ የኢትዮጵያ መድንን ግብ ሲሞን ፒተር ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ኦሮ አጎሮ በውድድር አመቱ አስራ ስድስተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኙት ፈረሰኞቹ በተከታታይ ያደረጓቸውን ያለፉት አስራ አንድ ጨዋታዎች አልተሸነፉም።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምስት ነጥብ ዝቅ ብለው #ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ አርባምንጭ ከተማ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ድል ቀንቶታል !

በስፔን ላሊጋ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባርሴሎና ከ አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

የባርሴሎናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ራፊንሀ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባርሴሎና በውድድር አመቱ አስራ ዘጠኝ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት ችለዋል።

ባርሴሎና ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አትሌቲክ ቢልባኦ በሰላሳ ሶስት ነጥቦች ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባርሴሎና ከ ሪያል ማድሪድ እንዲሁም አትሌቲክ ቢልባኦ ከ ሪያል ቫላዶሊድ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርጀንቲና በፊፋ ደረጃ ቀዳሚ ልትሆን ነው ! የአለም ሻምፒዮኖቹ አርጀንቲና ያደረጓቸውን ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ማሸነፋቸውን ተከትሎ በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ አንደኛ ደረጃን እንደሚይዙ ይፋ ተደርጓል። በአሁን ሰዓት በአንደኛነት እየመራች የምትገኘው ብራዚል በሞሮኮ የደረሰባትን ሽንፈት ተከትሎ ደረጃዋ ዝቅ ሊል እንደሚችል ተገልጿል። አርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ኩሩካኦን በሰፊ የጎል ልዩነት 7ለ0 ሲያሸንፉ…
አርጀንቲና በፊፋ ደረጃ ቀዳሚ ሆናለች !

የአለም ሻምፒዮኗ አርጀንቲና በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ ሰንጠረዥ ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ #አንደኛ ደረጃን መያዝ ችለዋል።

በሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ሽንፈት የገጠማት ብራዚል ደረጃዋን ስትነጠቅ ወደ ሶስተኛ ዝቅ ብለዋል።

ወርሀዊ ደረጃው ምን ይመስላል ?

1ኛ - አርጀንቲና                2ኛ - ፈረንሳይ

3ኛ - ብራዚል                  4ኛ - ቤልጅዬም

5ኛ - እንግሊዝ                 6ኛ - ኔዘርላንድ

7ኛ - ክሮሽያ                   8ኛ - ጣልያን

9ኛ - ፖርቹጋል                10ኛ - ስፔን በመሆን ከአንድ እስከ አስር ያለውን ደረጃ ይዘው ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ እና ዶርትመንድ ድል ቀንቷቸዋል !

በጀርመን ቡንደስሊጋ የሀያ ሰባተኛ ሳምንት መርሐግብር ባየር ሙኒክ ፍሬቡርግን 1ለ0 እንዲሁም ዶርትመንድ ዩንዬን በርሊንን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የባየር ሙኒክን የማሸነፊያ ግብ ዴ ላይት ሲያስቆጥር ለዶርትመንድ ማለን እና ሞኮኮ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ባየር ሙኒክ በሀምሳ ስምንት ነጥቦች #አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ዶርትመንድ በሀምሳ ስድስት ነጥቦች #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ይከተላል።

ሽንፈት ያስተናገዱት ዩንዬን በርሊን እና ፍሬቡርግ በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ባየር ሙኒክ ከ ሆፈንሄም እንዲሁም ቦርስያ ዶርትመንድ ከ ስቱትጋርት የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#BeComeASponser

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደምቀው ከሚታዩበትና የሀገራችን ሰንደቅ አላማ በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ ከሚውለበለብበት ስፖርታዊ መድረኮች መካከል አንዱ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነው።

ሀገራችን ከአመት በፊት በተደረገው በዚህ ውድድር ላይ ከአለም ሁለተኛ እንዲሁም ከአፍሪካ #አንደኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።

በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ በሚደረገው የዘንድሮው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የአምናው ታሪክ ዘንድሮም በአትሌቶቻችን ሊደገም ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን ትልቅ የውድድር መድረክ ከስፍራው በመገኘት ጭምር በቲክቫህ ስፖርት እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቻናሎቹ በልዩ ሁኔታ ከዝግጅት ጊዜ አንስቶ እስከ ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ ልዩ የዜና ሽፋን የሚሰጥ ይሆናል።

በዚህ ሰፊ ሽፋን በሚሰጠው የስፖርት መድረክ ድርጅቶችና ተቋማት ምርትና አገልግሎታችሁን በልዩ ሁኔታ በማስተዋወቅ የታሪኩ አካል እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

በዚህ ውድድር ላይ አብረው መስራት የምትፈልጉ ድርጅቶች በ +251974699712 / @TikvahEthiopias መልዕክት ይላኩልን።
ሂሩት መሸሻ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች 🇪🇹

የ1,500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር በመጨረሻም ምድብ ተካፈለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ሂሩት መሸሻ #አንደኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሁለት አትሌቶቻችን ግማሽ ፍፃሜ ደረሰዋል !

በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ወርቅነሽ መለሰ እና ሀብታም አለሙ #ሶስተኛ እና #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

በርቀቱ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ትዕግስት ግርማ ውድድሯን ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።

የሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን አርብ ምሽት 3:25 ላይ የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ በሶስተኛ ምድብ የምትገኘው ወርቅነሽ መሰለ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ሀብታም አለሙ ቀጣዩን ዙር መቀላቀል አልቻለችም።

አትሌት ሀብታም አለሙ በማጣሪያ ውድድሩ 2:02.19 በሆነ ሰዓት ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

አትሌት ሀብታም አለሙ በቀጣይ " repêchage " በተባለው የአለም አትሌቲክስ አዲስ ህግ ሌላ ውድድር የምታደርግ ይሆናል።

ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ያልቻሉ አትሌቶች ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ነገ የ " repêchage " ማጣሪያ ውድድራቸውን ቀን 6:10 የሚያደርጉ ይሆናል።

የ800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ምሽት 3:35 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ በአምስተኛ ምድብ የተካፈለችው አትሌት ፅጌ ዱጉማ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

አትሌት ፅጌ ዱጉማ የማጣሪያ ውድድሯን 1:57.90 በሆነ ሰዓት በመግባት በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች።

ቀድመው በተደረጉ የማጣሪያ ውድድሮች አትሌት ወርቅነሽ መሰለ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል አትሌት ሀብታም አለሙ ቀጣዩን ዙር #በቀጥታ መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።

ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ያልቻሉ አትሌቶች ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ነገ የ " repêchage " ማጣሪያ ውድድራቸውን ቀን 6:10 ጀምሮ የሚያደርጉ ይሆናል።

የ800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ምሽት 3:35 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በሁለተኛው ምድብ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ የማጣሪያ ውድድሩን  3:55:10  በሆነ ሰዓት ውድድሩን #አንደኛ ደረጃን እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋዬ የማጣሪያ ውድድሩን  3:56:41 በሆነ ሰዓት #አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:25 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe