TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
#PressConferenceLive

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከ ደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክተው ስለነበራቸው ዝግጅት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ባረፉበት አቫንቲ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ።

*ጋዜጣዊ መግለጫውን #በቀጥታ#ቮይስ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
በርናርዶ ሲልቫ ይቅርታ ጠየቀ !

ፖርቹጋላዊው የ መስመር ተጫዋች በርናርዶ ሲልቫ ትላንት ሀገሩ ለ ኳታሩ አለም ዋንጫ #በቀጥታ ማለፍ አለመቻሏን ተከትሎ ይቅርታ ጠይቋል ።

በተለይም ፖርቹጋል በመጨረሻው ደቂቃ በተቆጠረባት ግብ ማለፍ ሳትችል ስትቅር ተጨማሪ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎችን ለመጫወት ተገደዋል ።

ክሰተቱን ተከትሎ " ለ ፖርቹጋል መጥፎ ጨዋታ ነበር ፣ ማየት ያልነበረባቸውን ጨዋታ የተመለከቱ ፖርቹጋላዊያን ደጋፊዎቻችን በሙሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ " ሲል በርናርዶ ሲልቫ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ መልዕክቱን አስተላልፏል !

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለ ኳታሩ የአለም ዋንጫ #በቀጥታ አለማለፋቸውን ተከትሎ የሚከተለውን መልዕክቱን አስተላልፏል ።

" የምሽቱ ውጤቱ ከባድ ነበር ፣ ነገር ግን ተስፋ ሊያስቆርጠን የሚችል አይደለም ፣ ፈታኝ መንገዶች በስተመጨረሻ ወደሚፈለገው ውጤት የሚመሩ ናቸው " ሲል በ ማህበራዊ ገፁ አስነብቧል ።

ፖርቹጋል በቀጣይ ለ ኳታሩ የአለም ዋንጫ ለማለፍ የ ጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ማካሄድ ይጠበቅባታል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን የሚሳተፉበት የኦሪጎን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በይፋ ተጀምሯል ።

አሁን እየተደረገ ባለ የ 3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደረው ጌትነት ዋለ 8.17.49 በመግባት አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ።

ውጤቱን ተከትሎ አትሌታችን ጌትነት ዋለ ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ በሌሎች ምድቦች የሚመዘገቡ ውጤቶችን ይጠብቃል ።

በ 3,000ሜትር መሰናክል ማጣርያ የመጀመሪያውን ሶስት ደረጃ የያዙ አትሌቶች #በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል ።

ስድስት ምርጥ ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶች ከየምድቦቹ አላፊ የሚሆኑ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Ethiopia 🇪🇹 ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን የሚሳተፉበት የኦሪጎን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በይፋ ተጀምሯል ። አሁን እየተደረገ ባለ የ 3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ በመጀመሪያው ምድብ የተወዳደረው ጌትነት ዋለ 8.17.49 በመግባት አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ። ውጤቱን ተከትሎ አትሌታችን ጌትነት ዋለ ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ በሌሎች ምድቦች የሚመዘገቡ ውጤቶችን ይጠብቃል ። በ 3,000ሜትር…
ለሜቻ ግርማ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል !

አሁን እየተደረገ ባለ የ 3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ #በሁለተኛው ምድብ የተወዳደረው ለሜቻ ግርማ 8.19.63 በመግባት #አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል ።

ውጤቱን ተከትሎ አትሌታችን ለሜቻ ግርማ #በቀጥታ ወደ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል ።

የ 3,000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር የፊታችን ሰኞ ሌሊት 11:20 ላይ የሚደረግ ይሆናል ።

በ 3,000ሜትር መሰናክል ማጣርያ የመጀመሪያውን ሶስት ደረጃ የያዙ አትሌቶች በቀጥታ የሚያልፉ ይሆናል ።

ስድስት ምርጥ ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶች ከየምድቦቹ አላፊ የሚሆኑ ይሆናል ።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ወደ ፕርሚየር ሊጉ ማን ያድጋል ?

በቀጣይ ዓመት የእንግሊዝ ፕርሚየር ተሳታፊ ለመሆን በሚደረገው ፉክክር ሁለት ቡድኖች አስቀድሞ በቀጥታ ማለፋቸውን የሚያረጋግጡ ይሆናል።

ሻምፒየን ሺፑን በርንሌይ ከተከታዩ ሼፍልድ ዩናይትድ በስምንት ነጥቦች ርቀው እየመሩ ሲገኙ ሶስት ነጥብ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን ያረጋግጥላቸዋል።

በዛሬው ዕለት በማይክል ካሪክ የሚመራውን ሚድልስቦሮ የሚገጥሙትበ በርንሌዎች ካሸነፉ ወደ ሊጉ #በቀጥታ ማለፋቸው እውን ያደርጋሉ።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ?

1ኛ - በርንሌይ ( ሰማንያ አራት ነጥብ )
2ኛ - ሼፍልድ ዩናይትድ ( ሰባ ስድስት ነጥብ )
3ኛ - ሉተን ታውን ( ስልሳ ስምንት ነጥብ )
4ኛ - ሚድልስቦሮው ( ስልሳ ሰባት ነጥብ )
5ኛ - ሚል ዋል ( ስልሳ ሁለት ነጥብ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በፓሪስ ኦሎምፒክ 800ሜ ሴቶች ማጣርያ በአምስተኛ ምድብ የተካፈለችው አትሌት ፅጌ ዱጉማ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

አትሌት ፅጌ ዱጉማ የማጣሪያ ውድድሯን 1:57.90 በሆነ ሰዓት በመግባት በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች።

ቀድመው በተደረጉ የማጣሪያ ውድድሮች አትሌት ወርቅነሽ መሰለ #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል አትሌት ሀብታም አለሙ ቀጣዩን ዙር #በቀጥታ መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።

ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ያልቻሉ አትሌቶች ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ነገ የ " repêchage " ማጣሪያ ውድድራቸውን ቀን 6:10 ጀምሮ የሚያደርጉ ይሆናል።

የ800ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን እሁድ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም ምሽት 3:35 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe