TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.8K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
#Ethiopia🇪🇹

ዋልያዎቹ ዛሬ ከረፋዱ 3:30 ጀምሮ የ መጨረሻ ልምምዳቸው በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ሰርተዋል ።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዛሬ አመሻሽ ላይ ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ኢትዮጵያ ፈጣን ተጫዋቾች አሏት "

ከ ሰባት አመታት በፊት ኢትዮጵያ ከ ደቡብ አፍሪካ በ አዲስ አበባ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ ከሚታወሱ ተጫዋቾች መካከል ቀዳሚው በርናርድ ፓርከር ነው ።

ባፋና ባፋናዎቹ ከ ዋልያዎቹ ከሚያደርጉት ጨዋታ አስቀድሞ ምክሩን ለ ቡድን አጋሮቹ የለገሰው ፓርከር " ዋልያዎቹ ፈጣን ተጫዋቾች አሏቸው ፣ እኛ በመልሶ ማጥቃት በመጫወት የተሻለ ብቃት አለን ።

ስድስት ነጥቦችን ከዚህ ሁለት ጨዋታ ለማግኘት አቅደን መጫወት አለብን " ሲል በ ቡድኑ ያልተካተተው የ ፊት መስመር አጥቂ ፓርከር ተናግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ ወሩ ምርጥ ተጫዋች !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ መስከረም የወሩን ምርጥ ተጫዋች ይፋ አድርገዋል ።

ይህንንም ተከትሎ የ ማንችስተር ዩናይትድ ፖርቹጋላዊው የ ፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የወሩ የሊጉ ምርጥ ተጫዋች በመባል ተመርጧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ባህር ዳር ለመጫወት የሚያስፈራ ቦታ ነው "

የ ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ከ ሰባት ዓመታት በፊት በ ዋልያዎቹ ሲሸነፉ የቡድን ግብ ጠባቂ የነበረው ኢቱሙሌንግ ኩኔ ስለነገው ጨዋታ የሚከተለውን ብሏል ።

" ከዚህ ቀደም ከ ኢትዮጵያ ጋር መጫወት ችለናል ፣ ያኔ የምንፈልገውን ውጤት ማግኘት አልቻልንም ነበር ።

አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ስለተጫወትን ከእኛ ጋር ሲነጻጸር የነገው የተለየ ነው ፣ ይህ ጨዋታ ባህርዳር ላይ ነው ።

ለመጫወት የሚያስፈራ ቦታ ነው ፣ በ ስታዲየሙ ውስጥ ደጋፊዎች ከሌሉ ውጤቱ ወደ እኛ የሚያደላ ይሆናል " ሲል የ ባፋና ባፋና የቀድሞ ግብ ጠባቂ አስተያየቱን ስለ ጨዋታው ሰጥቷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ፕርሚየር ሊጉ የ ወሩ ምርጥ አሰልጣኝ !

የ ሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሴናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርሀ መስከረም ምርጥ አሰልጣኝ በመባል መመረጡ ይፋ ሆኗል ።

አርቴታ በወሩ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሶስቱን መድፈኞቹ ሲያሸንፉ በሁለት ጨዋታዎች ግብ አልተቆጠረባቸውም ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PressConferenceLive

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከ ደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክተው ስለነበራቸው ዝግጅት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ ባረፉበት አቫንቲ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ።

*ጋዜጣዊ መግለጫውን #በቀጥታ#ቮይስ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia🇪🇹

ዋልያዎቹ ባረፉበት ብሉ ናይል አቫንቲ ሆቴል በ አሁን ሰዓት የ ኮቪድ ምርመራ አካሂደዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#SouthAfrica

በነገው ዕለት ዋልያዎቹን የሚገጥመው የ ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ የ መጨረሻ ልምምዳቸውን በ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም አከናውነዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ባሎን ዶር የመጨረሻ ሰላሳ እግር ኳስ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ተደርጓል ።

ሙሉ ዝርዝሩ በምስሉ ላይ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Audio
የ ዋልያዎቹ ጋዜጣዊ መግለጫ !

የ ዋልያዎቹ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና የ ብሔራዊ ቡድኑ ዋና አምበል ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ ለ ጋዜጠኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

ከ ደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀውን ሙሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ከላይ ተያይዟል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለ ኳታሩ የ አለም ዋንጫ የ ማጣርያ የ ምድቡ ሶስተኛ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ከ ደቡብ አፍሪካ ጋር የምታካሂድ ይሆናል ።

ዋልያዎቹ በተሻለ የ ግብ ክፍያ የሚያሸንፉ ከሆነ የ ምድባቸው መሪ የሚሆኑበት አጋጣሚ ይፈጠራል ።

ጨዋታው ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe