TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
የባርሴሎና ጨዋታ ተራዘመ !

የባርሴሎና ኤና ኦሳሱና የሊግ መርሐግብር ለሌላ ጊዜ መራዘሙን የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን በይፋ አስታውቋል።

ጨዋታው የተራዘመው በባርሴሎና መልበሻ ክፍል ያለ የተጨዋቾቹ ቅርብ ሰው ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ህይወታቸው ያለፈው ግለሰብ የዋናው ቡድን ሀኪም መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተጨዋቾቹ ጨዋታው እንዲራዘም መጠየቃቸው ሲገለፅ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ላሊጋውም መስማማታቸው ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የባርሴሎና ጨዋታ ተራዘመ ! የባርሴሎና ኤና ኦሳሱና የሊግ መርሐግብር ለሌላ ጊዜ መራዘሙን የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን በይፋ አስታውቋል። ጨዋታው የተራዘመው በባርሴሎና መልበሻ ክፍል ያለ የተጨዋቾቹ ቅርብ ሰው ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ህይወታቸው ያለፈው ግለሰብ የዋናው ቡድን ሀኪም መሆናቸውን ገልጸዋል። ተጨዋቾቹ ጨዋታው እንዲራዘም መጠየቃቸው…
#Update

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የዋናው ቡድን ሀኪም የነበሩት ካርልስ ሚናሮ ጋርሽያ ዛሬ ምሽት ህይወታቸው ማለፉን በይፋ አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት ባርሴሎና ዛሬ ምሽት ከኦሳሱና ጋር ሊያደርገው የነበረው የሊግ መርሐግብር ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል።

የባርሴሎና መልበሻ ቤት ከህክምና ባለሙያው ህልፈተ ህይወት በኋላ መረበሹን የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል።

የህክምና ባለሙያው በባርሴሎና መልበሻ ቤት ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸው እና በሁሉም የሚወደዱ ባለሙያ እንደነበሩ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከካሜሩን ጋር ያደረገውን የአለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ 5ለ2 ተሸንፏል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልሱን ጨዋታ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
The National Finance Academy (NFA), the only accredited training institution for Insurance in the country, is pleased to announce the launch of its 4-month Professional Diploma Program in Insurance.

As part of our commitment to social responsibility, NFA offers FULL and PARTIAL scholarships in collaboration with Ethiopian Reinsurance Company, Africa Reinsurance Company, Association of Ethiopian Insurers, Ethio Life and General Insurance, Awash Insurance S.C, and Africa Insurance S.C.
  Registrar Office: Around Magenagna infront of Ministry of Agriculture Tel: +251116661297 or  +251945253515
Can PlayStation

PlayStation 5 Packed jestic በ 11,000ብር

ብዛት አቅርበናል
ለክፍለ ሀገር እናቀርባለን ይደውሉ

በቅናሽ PlayStation ይግዙ
ከ Can PlayStation

PlayStation 4 Dubai jestic=3500
Ps4 Dubai Used Orginal jestic=5000
PlayStation 5 Packed jestic=11,000

🤝Tanks for choice

አድራሻ፦
ቁጥር 1  መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
   
ቁጥር 2   ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ  ምድር ላይ


ስልክ፦ 0910529770 ወይም                  0977349492
0914646972  ይደውሉ

ለአዳዲስ መረጃ Telegram channel join ይበሉ ፦
https://yangx.top/CanPlaystation

                       👍Update Your Life
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

10:00 ሄታፌ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

11:00 ቼልሲ ከ ሌስተር ሲቲ

11:00 ቶተንሀም ከ በርንማውዝ

11:00 ናፖሊ ከ ፊዮሬንቲና

12:00 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ስሑል ሽረ

12:15 ሪያል ማድሪድ ከ ራዮ ቫዬካኖ

1:30 ማንችስተር ዩናይትድ ከ አርሰናል

2:00 ኢምፖሊ ከ ሮማ

4:45 ጁቬንቱስ አታላንታ

🔴የዛሬው የይገምቱ ሽልማታችን የቼልሲ ፣ ሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ ሽልማቶቻችን 9:30 ፣ 11:00 ፣ 12:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

ያንብቡ

🔴 መገመት የሚቻለው በተጠቀሱት ሰዓቶች ላይ ብቻ ነው።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ሀላፊ ለመሾም ተቃርቧል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በኤዱ ጋስፐር ምትክ አዲስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ለመሾም መቃረቡ ተገልጿል። መድፈኞቹ የቀድሞውን የአትሌቲኮ ማድሪድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ ለመሾም መቃረባቸው ተነግሯል። በአለም እግርኳስ ውስጥ ስማቸው በጉልህ የሚነሳው አንድሬ ቤርታ ከኤሲ ሚላን ጥያቄ ቀርቦላቸው ለአርሰናል ቅድሚያ መስጠታቸው ተገልጿል። ጣልያናዊው…
አርሰናል ሀላፊ ለመሾም ተስማማ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በኤዱ ጋስፐር ምትክ አዲስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ለመሾም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የቀድሞውን የአትሌቲኮ ማድሪድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል።

አንድሬ ቤርታ ከተለያዩ ክለቦች ጥያቄዎች ቢቀርቡላቸውም ለአርሰናል ቅድሚያ በመስጠት ክለቡን ለመቀላቀል መስማማታቸው ተነግሯል።

ጣልያናዊው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ በአትሌቲኮ ማድሪድ ቤት ከአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ ጋር ለአስራ ሁለት አመታት ሰርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሬንስ የበለጠ ፈትኖናል " ኤንሪኬ

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ትላንት ምሽት ከሬንስ ጋር ያደረጉት የሊግ ጨዋታ ከሻምፒየንስ ሊጉ ጨዋታ የበለጠ ፈታኝ ሆኖብን ነበር በማለት ተናግረዋል።

ፒኤስጂ ትላንት ምሽት ባደረገው የሊግ መርሐ ግብር ሬንስን 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ " ሬንስ ከአንድ አንድ የሻምፒየንስ ሊግ ቡድኖች በበለጠ ፈትኖን ነበር።" ብለዋል።

የፒኤስጂ ተጨዋቾች ከሊቨርፑል ይልቅ በሻምፒየንስ ሊጉ የገጠሟቸው አርሰናል እና ባየር ሙኒክ “ ከባድ ናቸው “ ብለው እንደሚያምኑ ተገልጿል።

በፒኤስጂ ውስጥ ያለ ሁሉም ሰው ሊቨርፑልን አንፊልድ ላይ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ዙር እንደሚያልፉ እርግጠኛ መሆናቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል እና ፒኤስጂን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን ማክሰኞ በሊቨርፑል እና ፒኤስጂ መካከል የሚደረገውን ተጠባቂ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

ማክሰኞ ምሽት 5:00 የሚደረገውን ተጠባቂ የመልስ ጨዋታ ሮማኒያዊው ዳኛ እስቴቫን ኮቫችስ በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

ዋና ዳኛው ባለፈው አመት ፒኤስጂ ባርሴሎናን በሜዳው 4ለ1 ያሸነፈበትን የሻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መርተዋል።

ፒኤስጂ የመጀመሪያውን ጨዋታ በሜዳው 3ለ2 ተሸንፎ ባርሴሎናን በሜዳው 4ለ1 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀላቸው አይዘነጋም።

የመጀመሪያውን ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ1ለ0 በማሸነፍ መመለሳቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የየእለቱን የቲክቫህ ዜናዎችን በSMS እናግኝ! 🗞📲

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30000 SMS አሁኑኑ በመላክ ወይም ወደ *799# በመደወል የቲክቫህ ትኩስ መረጃዎችን እናግኝ!
በቀን 1ብር ብቻ! ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት ⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
ቀመረኛው!!
ዛሬም የሚያሸንፉባቸው የእለቱ የውርርድ ጥቆማዎች እነሆ!
አሁን ነው ማሸነፍ እድሜ ለቀመረኛው!!
ቀመረኛው - በቤቲካ ብቻ!
" ጠንካራ ድጋፍ ያስፈልገናል " ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የክለቡ ደጋፊዎች በዛሬው የሌስተር ሲቲ ጨዋታ ጠንካራ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

“ ደጋፊዎቻችን ዘጠና ደቂቃ ያስፈልጉናል “ ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ጨዋታውን ማሸነፍ በጣም ያስፈልገናል በማለት ገልጸዋል።

“ ጨዋታውን ማሸነፍ የምናልመውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታ ለማግኘት አንድ እርምጃ ይወስደናል “ ሲሉ ኢንዞ ማሬስካ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይገምቱ ይሸለሙ

የቼልሲ እና ሌስተር ሲቲን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 11:00 ሰዓት ብቻ ነው።

🔴 ይነበብ

አንድ የቤተሰባችን አባል ግምት ማስቀመጥ የሚችለው #አንዴ ብቻ ነው። ከአንድ ጊዜ በላይ የመለሰ ቤተሰባችን ሽልማት አይደርሰውም።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
የጨዋታ አሰላለፍ !

11:00 ቼልሲ ከ ሌስተር ሲቲ

11:00 ቶተንሀም ከ በርንማውዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አርሰናል ለዋንጫ እየተፋለመ ነው " አሞሪም

የቀያዮቹ ሴጣኖች ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የማንችስተር ዩናይትድ እና አርሰናል ተቀናቃኝነት በአሁኑ ሰዓት በተለየ ሁኔታ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ሲናገሩም " አሁን ከሮይ ኪን እና ፓትሪስ ቬራ ጊዜ ፍፁም የተለያየ ወቅት ላይ ነው የምንገኘው " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም " አርሰናል ለዋንጫ እየተፋለመ ነው እኛ ግን በተለየ ሁኔታ ውስጥ ነው የምንገኘው " ብለዋል።

" ውጤታችን የወረደ ነው ፤ እንቅስቃሴያችን እየተሻሻለ አይደለም ነገርግን ጥሩው ነገር ብዙ ነገሮችን እየተማርን ፤ ብዙ ነገሮችንም እየቀየርን ነው።" አሞሪም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዩናይትድ የቡድን አባላቱን መመገብ አልቻለም " ጋሪ ኔቭል

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ጋሪ ኔቭል ማንችስተር ዩናይትድ ከሀብታም ክለቦች ተርታ ደረጃው ወርዷል በማለት ተናግሯል።

“ ማንችስተር ዩናይትድ ደረጃው ከሀብታም ክለቦች ተርታ ወርዶ የቡድን አባላታቸውን መመገብ የማይችሉ ክለቦች ተርታ ተገኝቷል " ሲል ጋሪ ኔቭል ገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቅርቡ ለክለቡ አባላት የሚቀርበውን ነፃ ምግብ መመገቢያ ስፍራ መዝጋቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቡናማዎቹ ከሶስት ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ ኢትዮጵያ ቡና - 33 ነጥብ
1️⃣5️⃣ ሀዋሳ ከተማ - 20 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ?

ሐሙስ - ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን

አርብ - መቻል ከ ኢትዮጵያ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe