TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ቼልሲ ነጥብ ተጋርተዋል !

በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከ ዌስትሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የቼልሲን ግብ ጇ ፊሊክስ ከመረብ ሲያሳርፍ ለዌስትሀም የአቻነቷን ግብ ኤመርሰን አስቆጥሯል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተከታታይ ያደረጋቸውን ሶስት የሊግ ጨዋታዎችን አቻ ወጥቷል።

ጇ ፊሊክስ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቼልሲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥብ በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ዌስትሀም በሀያ ነጥቦች አስራ አምስተኛ ደረጃ መቀመጥ ችለዋል።

ቼልሲ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ከ #ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ዌስትሀም ከ ቶተንሀም የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ድል ቀንቶታል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን ጋር ያደረገውን የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ሞሀመድ ሳላህ እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- ኮዲ ጋክፖ ለመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሞሀመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ በሀያ ጨዋታዎች #ስምንተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰላሳ ሁለት በማድረስ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤቨርተን በበኩሉ በአስራ ስምንት ነጥቦች አስራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ #ኒውካስል_ዩናይትድ እንዲሁም ኤቨርተን ከ ሊድስ ዩናይትድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ ነጥብ ተጋርተዋል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ መቻል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል ።

የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች መስፍን ታፈሰ ፣ ራምኬል ጀምስ እና መሀመድ ኑር ናስር ሲያስቆጥሩ የመቻልን ግቦች እስራኤል እሸቱ 2x እና በረከት ደስታ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የቡናማዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች መሀመድ ናስር በውድድር አመቱ ስድስተኛ የሊግ ጎሉን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ በደረጃ ሰንጠረዥ አስራ ዘጠኝ ነጥቦች በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ መቻል በበኩላቸው በአስራ ስባት ነጥቦች አስራ አንደኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም መቻል ከ ለገጣፎ ለገዳዲ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ጣፋጭ ሶስት ነጥብ አስመዝግቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግብ ጁሊያን አልቫሬዝ ፣ ኬቨን ዴብሮይን ፣ ካይ ጉንዶጋን እና ጃክ ግሪሊሽ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሊቨርፑል ሞሀመድ ሳላህ አስቆጥሯል።

ሊቨርፑል በሁሉም ውድድሮች ተከታታይ ሶስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሚመሩት ሊቨርፑሎች በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን ስልሳ አራት በማድረስ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አምስት ማጥበብ ችሏል።

ሊቨርፑል በበኩሉ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ስድስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ሊቨርፑል ከ ቼልሲ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ድል ቀንቶታል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን የሊጉ ተስተካካይ መርሐ ግብር 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የማንችስተር ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ማርከስ ራሽፎረድ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎረድ በውድድር አመቱ አስራ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀምሳ ሶስት በማድረስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ #አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ብሬንትፎርድ በበኩሉ አርባ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን እንዲሁም ብሬንትፎረድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

- በሌላ ተስተካካይ የሊጉ መርሐግብር ኒውካስል ዩናይትድ ዌስትሀም ዩናይትድን 5ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የባህር ዳር ከተማን ግቦች ሀብታሙ ታደሰ እና አደም አባስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለኢትዮጵያ መድን ሳይመን ፒተር እና ሀቢብ ከማል ማስቆጠር ችለዋል።

- የኢትዮጵያ መድኑ ተጨዋች ሀቢብ ከማል በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ሲያስቆጥር ሌላኛው ተጨዋች ሳይመን ፒተር ስድስተኛ ጎሉን ከመረብ አሳርፏል።

- የባህርዳር ከተማው ተጨዋች ሀብታሙ ታደሰ በውድድር አመቱ ሰባተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- ባህርዳር ከተማ በአርባ ሶስት ነጥቦች #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ መድን በሰላሳ ስምንት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇧

በሊጉ ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ብራይተን ከ ዎልቭስ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 6ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ዳኒ ዌልቤክ 2x ፣ ግሮስ 2x እና ኡንዳቭ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢው ቡድን ብራይተን ማሸነፉን ተከትሎ ቀሪ ጨዋታዎች እያሉት በሀምሳ ሁለት ነጥቦች #ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

- የብሬንትፎርዱ የፊት መስመር ተጨዋች ኢቫን ቶኒ በውድድር አመቱ ሀያኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ብሬንትፎርድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀምሳ በማድረስ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናን ሁለት ግቦች መሐመድ ኑር ናስር ሲያስቆጥር ለአዳማ ከተማ አድናን ረሻድ እና ደስታ ዮሀንስ ከመረብ አሳርፈዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኑር ናስር በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል

- ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ አንድ ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲዳማ ቡና ድል አድርጓል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከ ፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግብ ደስታ ደሙ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሲዳማ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ፋሲል ከነማ በሰላሳ ሰባት ነጥብ #አራተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከ ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድሬዳዋ ከተማ አሸንፏል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋን የማሸነፊያ ግቦች እያሱ ለገሰ እና ሱራፌል ጌታቸው ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለወልቂጤ ከተማ ጌታነህ ከበደ አስቆጥሯል።

የወልቂጤ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ጌታነህ ከበደ በውድድር አመቱ አስራ ስድስተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልቂጤ ከተማ በሀያ ዘጠኝ ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ መቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኢትዮ ኤሌክትሪክን ግቦች አብዱራህማን ሙባረክ 2x ሲያስቆጥር የመቻልን የአቻነት ግቦች እስራኤል እሸቱ እና ተሾመ በላቸው ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

መቻል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሶስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአስራ ሁለት ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአስራ ሁለት ነጥቦች ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊጉ መውረዳቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለገጣፎ ለገዳዲ ድል አድርጓል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ለገጣፎ ለገዳዲ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የለገጣፎ ለገዳዲን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አማኑኤል አረቦ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ለገጣፎ ለገዳዲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን አስራ አምስት በማድረስ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አዳማ ከተማ በሰላሳ ሶስት ነጥቦች ነጥቦች #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

በሀያኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የኖቲንግሀም ፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች ዶምኒጉዌዝ እና ጊብስ ዋይት ሲያስቆጥሩ ለማንችስተር ዩናይትድ ማርከስ ራሽፎርድ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ #ዘጠነኛ እንዲሁም በሁሉም ውድድሮች አስራ አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

7️⃣ኛ :- ማንችስተር ዩናይትድ ( 3️⃣1️⃣ ነጥብ )

1️⃣5️⃣ኛ :- ኖቲንግሀም ፎረስት ( 2️⃣0️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ዕሁድ - ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

ቅዳሜ - ብሬንትፎርድ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ድል አድርጓል !

በስፔን ላሊጋ አስራ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከኦሳሱና ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቪኒሰስ ጁኒየር (3x) እና ጁድ ቤሊንግሀም ማስቆጠር ችለዋል።

ቪኒሰስ ጁኒየር በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ የላሊጋ ግቡን አስቆጥሯል።

ቪኒሰስ ጁኒየር በዚህ የውድድር ዘመን ባደረጋቸው አስራ ሰባት ጨዋታዎች አስራ ስምንት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

ድሉን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ ከመሪው ባርሴሎና ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #ስድስት ዝቅ ማድረግ ችሏል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

2⃣ ሪያል ማድሪድ - 27 ነጥብ

5⃣ ኦሳሱና - 21 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ?

- ሌጋኔስ ከ ሪያል ማድሪድ

- ኦሳሱና ከ ቪያሪያል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ድል አድርጓል !

በዩሮፓ ሊግ አምስተኛ ዙር ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድ ሲያሸንፍ ቶተንሀም ከሮማ ጋር ነጥብ ተጋርተዋል።

በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ከቦዶ ጋር የተጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ በሆይሉንድ 2x እና ጋርናቾ ግቦች ታግዞ 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሀም ከሮማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ግቦችን ለቶንሀም ሰን ሁንግ ሚን እና ጆንሰን እንዲሁም ለሮማ ዲካ እና ሁሜልስ ማስቆጠር ችለዋል።

ራስመስ ሆይሉንድ በአውሮፓ ውድድሮች #ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቀያይ ሰይጣኖቹ በውድድር አመቱ #ሁለተኛ የዩሮፓ ሊግ ድላቸውን አሳክተዋል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንችስተር ዩናይትድን እየመሩ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ማሸነፍ ችለዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች ሪያል ሶሴዳድ አያክስን 2ለ0 እንዲሁም ሬንጀርስ ኒስን 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የክለቦቹ ደረጃ ምን ይመስላል ?

9️⃣ ቶተንሀም - 10 ነጥብ
1⃣2⃣ ማንችስተር ዩናይትድ - 9 ነጥብ
2⃣1️⃣ ሮማ - 6 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብሮች ?

- ቪክቶሪያ ፕልዘን ከ ማንችስተር ዩናይትድ
- ሬንጀርስ ከ ቶተንሀም

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe