TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ቼልሲ ነጥብ ተጋርተዋል !

በእንግሊዝ ፕርምየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከ ዌስትሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የቼልሲን ግብ ጇ ፊሊክስ ከመረብ ሲያሳርፍ ለዌስትሀም የአቻነቷን ግብ ኤመርሰን አስቆጥሯል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተከታታይ ያደረጋቸውን ሶስት የሊግ ጨዋታዎችን አቻ ወጥቷል።

ጇ ፊሊክስ ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመጀመሪያ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቼልሲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥብ በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ ዌስትሀም በሀያ ነጥቦች አስራ አምስተኛ ደረጃ መቀመጥ ችለዋል።

ቼልሲ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ከ #ሳውዝሀምፕተን እንዲሁም ዌስትሀም ከ ቶተንሀም የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe