TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
293 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ማዕከል በነገው እለት ግንቦት 10/ 2016 ዓ/ም ስታዲየም በሚገኘው የቀይ መስቀል ማህበር ጊቢ ውስጥ ከጠዋቱ 4 እስከ 11 ሰዓት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ በላከው መረጃ ገልጿል። ስለሆነም በመርሃግብሩ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ደም ሁሌ ተፈላጊ እንዲሆን የሚያረጉት ምክንያቶች ምንድናቸው ?

- የተፈጥሮ እና የ ሰው ሰራሽ አደጋዎች መጨመር
- የድንገተኛ ወረርሽኝ መከሰት
- ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት መስፋፋት
- የደም እና የደም ተዋፅኦ የአገልግሎት ጊዜ አጭር መሆን/ ፕላስማ 1 አመት
- ደም አማራጭ/መትክ/ የሌለው መድሀኒት መሆኑ 
- ደም በ አይነት ብቻ ለ ታካሚው የሚሰጥ መሆኑ

ደም የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው?

- የደም ማነስ ህመምተኞች
- ከፍተኛ የቀዶ ህክምና የሚስፈልጋቸው እና የካንሰር ህመምተኞች
- በወሊድ ወቅት ብዙ ደም የሚፈሳቸው እናቶች
- በተለያዩ የጤና ችግሮች ሳቢያ እንደተወለዱ ደም ሚፈሳቸው ህፃናት
- በዘር ውርስ የሚመጡ የደም መድማትና መሟሸሽ ችግሮች ያሉባቸው።

ደም ከመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች ምንድናቸው?

- የደም አይነት ያለ ክፍያ ማወቅ ይቻላል።
- ሰዎች በ ደም እጥረት ምክንያት አይሞቱም።
- የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በ አንዳንድ ምርምሮች ሲገለፅ ማለትም ከ ሌሎች ደም ከማይለግሱት የተሻለ በ heart attack  የመጋለጣቸው አድል አነስተኛ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ በ 0940512564 ይደውሉ

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

የአውራ አምባ ማይክሮ ፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን በ Branch Manager, Accountant, Coustomer service officer እና Cahshier የስራ መደቦች ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

በመሆኑም አመልካቾች የስራ መደቦቹ የሚፈልጉትን ልምድ እና መስፈርት ከተያያዘው ምስል ላይ በመመልከት በአዲስ አበባ ለገሃር አቅራቢያ በሚገኘው የአማራ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ ሁለተኛ ፎቅ ላይ በመገኘት ማመልከት እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

ለተጨማሪ መረጃ በ +251918317021 ወይም +251955991544 መደወል እንደምትችሉም ተገልጿል።

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) በሀገር አቀፍ ደረጃ እድሜአቸው ከ11 አመት በላይ ለሆኑ እና ፍላጎት ላላቸው የሳይበር ክህሎት የስልጠና ምዝገባ እና የቻሌንጅ መርሃግብር መጀመሩን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።

ተቋሙ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ወጣቶችን መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚመዘገቡ ሰልጣኞችን  ደረጃ በደረጃ የሚመለምልበት ፈተና (ቻሌንጅ) እና ክህሎታቸውን የሚለይበት ሳይንሳዊ መስፈርት ማዘጋጀቱን ተገልጿል።

ተቋሙ የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች ምንድናቸው ናቸው?

- በሳይበር ደህንነት፣
- በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የድረገፅ፣ የመተግበሪያ እና ተያያዥ ልማት (development)፣
- የስማርት ፕሮጀክት ሲስተሞች ፣
- በኤሮስፔስ እና ሎሎችም እንደሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ለአንድ ወር ይሰጣል የተባለ ሲሆን አመልካቾች በዌብሳይት  https://talent.Insa.gov.et በመግባት እስከ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም መመዝገብ እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

ለበለጠ መረጃ +251904311833 +251943579970

+251904311837

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

"በጎ ስጦታ" የበጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ከውጪ ካሉ ለጋሽ አካላት ጋር በመተባበር በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ያላቸው ግን በአቅም ማነስ ምክንያት ትምህርታቸውን ለመከታተለ የከበዳቸውን ተማሪዎች ድጋፍ ለማረግ ማቀዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ተቋሙ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በኪያሜድ ኮሌጅ በነርሲንግ ዲፓርትመንት በዲፕሎማ መርሀ ግብር 20 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ከትምህርት ጋር የተያያዙ ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እድሉን ማመቻቸቱን ገልጿል።

የዚህ እድል ተሳታፊ የሆኑ ልጆች ምን ማሟላት አለባቸው?

- ከ 2014 እስከ 2015 የ 12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ለዲፕሎማ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ፤

- በዲፕሎማ በቀን መርሀ ግብር ነርሲንግ መማር ፍላጎት ያላቸው።

- አቅም እንደ ሌላቸው ከቀበሌ ማስመስከር የሚችሉ፤

- ትምህርቱን ከጀመሩ በኋላ ውጤታቸውን አስጠብቀው መጓዝ የሚችሉ፤

- ተቋሙ ከትምህርት ውጪ ያሉ ወጪዎችን ስለማይሸፍን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ይህንን የምታሟሉ / በአከባቢያችሁ በትምህርታቸው ጎበዝ የሆኑ የምታቋቸው ካሉ በዚህ እድል እንዲጠቀሙ ይህንን መልዕክት አድርሷቸው።

ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም @elzabet18/@Dr_Daniel_D ወይም በስልክ ቁጥር +251912671410 /+251938327771/ +251953146834 ላይ ያግኙ።

BegoSitota.com

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በተለያዩ ክፍት የሥራ መደቦች ላይ ብቁ የሆኑ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ዝርዝር መረጃውን ከተያያዘው ምስል በመመልከት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስረጃችሁን በመያዝ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በዚህ ሊንክ https://forms.gle/9H9JCyjZkTkdw1Z86 መመዝገብ እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

#JobAlert

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

በኢትዮጵያ የመጀመርያው የአቪዬሽን የቴሌቪዥን ዝግጅት፣ ዛሬ ምሽት በ2 ሰዓት በአርትስ ቴሌቪዥን ይቀርባል፡፡ ፕሮግራሙ በ90 ዓመታት የአቪዬሽን ታሪካችን ያልተሰነዱ ታሪኮችን በመሰነድ ለተመልካች ሊያደርስ መሆኑ ነው የተገለጸው።

የፕሮግራሙ ዋና አዘጋጅ እና አቅራቢ ዮናታን መንክር ካሳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ይህ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ያሁኑና መጪው ትውልድ በታሪኮቹ ውስጥ ባሉት ዕሴቶች እንዲማር፣ የመጪውንም ዘመን እንዲሰራበት ለማበረታታት የተዘጋጀ ነው።

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

በዳግማዊ ምኒሊክ በአታ ለማርያም ገዳም በክረምት መርሃ ግብር የአብነት ትምህርት ለማስተማር ምዝገባ ተጀምሯል።

ትምህርቱ በመደበኛ ቀን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በዳግማዊ ምኒሊክ በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ካህናት ማሰልጠኛ መንፈሳዊ ግቢ ውስጥ በተመረጡ አዳሪ ደቀ መዛሙርት መምህራን የሚሰጥ የደቂቀ ቅዱስ እስጢፋኖስ   የክረምት መረሀ ግብር ነው ተብሏል።

በመሆኑም በዚህ መርሃግብር ላይ ልጆችን ለማስመዝገብ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ማስመዝገብ እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

0955252387
 0922675398

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ከዩ.ኤስ.ኤድ ጋር በመተባበር ተግባራዊ እያደረገ ባለው የአደጋ ስጋት አስተዳደር ሦስተኛ ዙር ሥልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

በስልጠናው ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ያሉ በተያያዥ የትምህርት ዘርፍ ተመራቂ ለሆኑ የቀረበ ሲሆን ሁለት ዓመት የሚቆይ የአጫጭር ስልጠና እንዲሁም የተግባር ላይ ልምምድን ያካተተ ነው።

በሦስተኛው ዙር ስልጠና 150 የሚሆኑ አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን ለመቀበል ማስታወቂያ የወጣ ሲሆን ከ2015 ወዲህ ላሉ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ውጤት ይጠይቃል።

ምዝገባው የሚደረገው እስከ ነሐሴ 5 ድረስ ነው።

በሚከተለው የመመዝገቢያ ሊንክ ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል 👉 https://url1.io/WCWSw

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ ለሚያከናውነው የግብርና ናሙና ቆጠራ 43,500 ሠራተኛ ይፈልጋል።

የሥራ ሁኔታው #በኮንትራት ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ወጣቶች በመረጃ ማሰባሰብ ሥራው ላይ ለመሳተፍ ማመልከት ይችላሉ።

ምዝገባውን በሌበር ማርኬት ፖርታል- E-LMIS http://lmis.gov.et ላይ በማድረግና አቅራቢያችሁ ባለ አንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይዛችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

ጂ.አይ.ዜድ በኢትዮጵያ ወጣት ሰዓሊያንን የሚያሳትፍ የስዕል ውድድር አዘጋጅቷል። የስዕል ውድድሩ ዋና ሀሳብ "መልካም አስተዳደር ለእናንተ ምን ማለት ነው? የሚል ነው።

ተወዳዳሪዎች የስዕል ሥራቸውን እስከ ነሐሴ 24/2016 ድረስ ካዛንቺስ በሚገኘው ሜትሮፖሊታን ሆስፒታሊቲ (MHB) ህንፃ 11ኛ ፎቅ በጂአይዜድ S2GG ቢሮ በአካል ተገኝቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

በውድድሩ አሸናፊ የሆነው ሥዕል የ25ሺ ብር ሽልማት የሚያገኝ ሲሆን ሁለተኛ እና ሦስተኛ የሚወጡ ሥዕሎች 15ሺ እና የ10 ሺ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ።

የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ከላይ #1 በተያያዘው ምስል መመልከት የሚችሉ ሲሆን ሥዕሉን ሲያቀርቡ ሞልተው መቅረብ ያለባቸውን ፎርም #2 በተያያዘው ምስል ላይ ያገኙታል።

ተሳታፊዎች ስለ ፕሮጀክቱ https://www.giz.de/en/worldwide/142660.html መመልከት ይችላሉ።

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከላይ በምስሉ በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደቦች አወዳድሮ መቅጠር እንደሚፈልግ አስታውቋል።

ለበለጠ መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ: አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለማስተማር የኦንላይን ምዝገባ ጀምሯል።

ምዝገባው እስከ መስከረም 25/ 2017 ዓ/ም የሚቆይ ሲሆን ትምህርቱ መስከረም 27 የሚጀመር መሆኑን ተገልጿል። በመሆኑም መመዝገብ የምትፈልጉ ከታች ባለው ሊንክ እንድትመዘገቡ ጥቆማ ቀርቧል።

www.allianceaddis.org

ለበለጠ መረጃ፡.በስልክ ቁጥር 0911247354 / 0965166416

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የአውራ አምባ ማይክሮ ፋይናንስ በአዲስ አበባ ለሚከፍታቸው ቅርንጫፎች በ4 የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

በመሆኑም ከላይ ተያያዙትን መረጃዎች በመመልከት እስከ መስከረም 18/ 2017 ድረስ ማመልከት እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

አድራሻ፦ ለገሃር አመልድ ህንፃ አማራ ባንክ የሚገኝበት 2ኛ ፎቅ የአውራ አምባ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ቅርንጫፍ።

በኢሜል ለመላክ [email protected] መጠቀም ትችላላችሁ ተብሏል።

Via @tikvahmagbot

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

ሥልጠናው በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ ጠዋት ከ3:00-5:00 ሰዓት፤ ለአስር ተከታታይ ሳምንት የሚሰጥ ይሆናል።

ለስልጠናው የግቢው ተማሪ ለሆኑ 500 ብር ከውጭ ለሚመዘገቡ 2000 ብር ያስከፍላል።

ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ ሰርተፊኬት እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ፣ 8ኛ ፍሉር ፎረም ህንጻ

ምዝገባ የሚያበቃው: መስከረም 21/2017 ዓ.ም

ስልጠናው የሚጀምረው: መስከረም 25/2017 ዓ.ም

የስልጠናው ቦታ: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር በጋራ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ላሉ ዲጂታል ስታርታፖች እና ከፍትኛ የማደግ አቅም ያላቸውን ዲጂታል ኢንትርፕራይዞች የቴክኒክ ድጋፍ የስልጠና መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ገልጿል።

ዘጠኝ ቀናት ይቆያል በተባለው በዚህ የቡትካምፕ፥ ሰልጣኞች ንግዳቸውን ከፍ ለማድረግ አስፈላጊ ክህሎቶችን እና ግንዛቤዎችን ለመውሰድ እንዲሁም ሥራዎን ለማሳደግ የሚያስችላቸውን የፋይናንስ ድጋፍ ያገኙበታል ሲል ነው ያስታወቀው።

🗓 የስልጠና ጊዜ፡ ህዳር 02 – 13፣ 2017 ዓ/ም

📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ

🗓 እስከ፡ ጥቅምት 15, 2017 ድረስ ያመልክቱ

🔗 የማመለካቻ ሊንክ ፡ https://shrturl.app/uz1mH5

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ: 4ኛው የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የጥበብ ሥራዎች ውድድር ተጀምሯል።

ውድድሩ በሕይወት የመኖር መብት በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ፣ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ዘርፍ ደግሞ በበቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብት ላይ የሚያተከኩር ሲሆን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

- የሥዕልና የፎቶግራፍ ውድድሩ ትኩረቱን በቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብቶች ላይ ያደርጋል።

- የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውድድር ደግሞ በሕይወት የመኖር መብት በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ የሚያተኩር ነው፡፡

በአጫጭር የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ዘርፍ ለውድድር የሚቀርብ ሥራ ከ 3 ገጽ ያልበለጠ (ከ600 ቃላት ያላነሰ፣ ከ1200 ቃላት ያልበለጠ) ሊሆን ይገባል።

በሁለቱም ዘርፎች የሚቀርቡ የጥበብ ሥራዎች ዘጋቢ፣ ምናባዊ ወይም እውነተኛ ታሪክ ላይ መሠረት ያደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል።

ለውድድሩ የኪነጥበብ ሥራዎችን የመላክ ሂደት ምን ይመስላል ?

ለውድድሩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. እኩለ ለሊት ወይም ድረስ ለውድድር የሚቀርበውን የኪነጥበብ ሥራ እንዲሁም የተሞላ እና የተፈረመበት የተሳትፎ ቅጽ በማያያዝ፤

በኢሜል [email protected]
በቴሌግራም @EthioHRC መላክ ይቻላል።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቢሮዎች በአካል በመገኘት መላክ ይችላሉ ተብሏል።

#ተጨማሪ: ውድድሩ የሚካሄድባቸውን ከተሞችንና የውድድሩን ዘርፎች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ።

@tikvahethmagazine 💬@tikvahmagbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ

የ2017/2024 ዓለምአቀፍ የንግድ ስራ ፈጠራ ሳምንት ህዳር 9 – 17, 2017 ዓ.ም ‹ኢንተርፕሪነርሽፕ ለሁሉም › በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

የዘንድሮው ዓለም አቀፉን የአንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር በህዳር ወር የግንዛቤ ማስጨበጫና መረጃ ሰጭ በሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ሆኖ የሚከበር ይሆናል፡፡

ቅዳሜ ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሰት የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች  እንዲሁም በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት የሙሉ ቀን የፓናል ውይይትና የመክክር መድረክ ይካሄዳል፡፡ 

እሁድ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም  ከምሽት ከ12 ፡ 00 (ስዓት) ጀምሮ ወሰን አካባቢ የእሳት ዳር ጨዋታ (ስቶሪ ቴሊንግ) ልምድ የማካፋል ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

በህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ህብርት አዳራሽ  ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ ለግማሽን ቀን የአፍሪካ ተወካዩች በተገኙበት ስለኢንተርፕረነርሽፕ እና ተያያዥ የቴክኒክና ሙያ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡

በመጨረሻም የፕሮግራሙ ማጠቃለያ በኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከስዓት በኃላ 8፡00  ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው የስነምህዳሩ ተዋንያን በተገኙበት የእውቅና ፕሮግራም እና ማጠቃለያ ይካሂዳል፡፡

በዘርፉ ያሉ ተዋንያን በዝግጅቶቹ እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታህሳስ 13 እና 14 ለሁለት ተከታታይ ቀናት ነጻ የዐይን ህክምና አገልግሎት ይሰጣል።

ህክምናው የሚሰጠው ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀበሺስታን ዴቬሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን /Habeshistan development and cooperation Association/ ጋር በመተባበር ነው።

ህክምናው ነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን  ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎትን ያካትታል።

በመሆኑም የአይን ችግር ያለባችሁ በሙሉ በተጠቀሰው ቀን ወራቤ ሆስፔታል በመገኘት  ነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ ሆስፒታሉ ገልጿል።

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ከተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ኢኖቬቲቭ የንግድ ሀሳብ እና ምርት ያላቸውን ጀማሪ እና ነባር ኢንተርፕራይዞችን የብድር ዋስትና ፈንድ የፋይናንስ አቅርቦት ድጋፍ እንዲያገኙ የማመቻቸት ስራ እየሰራ ይገኛል።

ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች (ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ያገኙታል) ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

ለበለጠ መረጃ +251941 88-37 46 // +251912166982 ይደውሉ።

ለመመዝገብ 👉 https://bit.ly/CRGF4thRoundApplication

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በስሩ ባሉ ሆስፒታሎች ጠቅላላ ሃኪሞችን አወዳድሮ በውስጥ ዝውውር ለማስራት ይፈልጋል።

መስፈርቱ ምንድን ነው ?

- ተወዳዳሪች ለምዝገባ ሲመጡ የትምሀርት ማስረጃ እና የታደሰ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባችኃል፤

- አመልካቾች ከሚሰሩበት መ/ቤት በተቋሙ ኃላፊ የተፈረመ የዝውውር ስምምነት ደብዳቤ እና የሥራ ልምድ ደረጃ እና ደመወዝ የሚጠቅስ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባችኃል፤

- ቋሚ ያልሆነ ሰራተኛ መወዳደር አይችልም፤

መቼ ማመልከት ይቻላል ?

ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 4 ቀን አየር ላይ ውሎ ለ2 ቀን ብቻ መጋቢት 05/2017 ዓ.ም እና መጋቢት 08/2017 ዓ.ም ምዝገባ ይካሄዳል።

ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን እንደማያስተናግድ ቢሮው ገልጿል።

የት ነው ማመልከት የሚቻለው?

አመልካቾች ፒያሳ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገለግሎት ጎን የመንግስት ሰራተኞች ማሀበራዊ ዋስትና ህንፃ በሚገኘው 7ተኛ ፎቅ የሰው ሃብት ስራ አመራርና ልማት ዳይሬክቶሬት ማመልከት ይችላሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine