#ፋይዳ
ስለ " ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጥያቄ አለዎት ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰብ አባላቱ ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥያቄዎች ይደርሱታል።
በዚህም የሚነሱ ጥያቄዎችን በቀጥታ እንዲመልሱ የሚመለከታቸው አካላትን ለማግኘት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምላሽ እሰጣለሁ በማለት ማረጋገጫ ልኳል።
ቤተሰቦቻችን በ "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ላይ ያላችሁን ጥያቄ ከዛሬ ጀምሮ ባሉ ሁለት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በ @tikvahmagbot ላይ መላክ ትችላላችሁ።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine

TIKVAH-MAGAZINE
በኢትዮጵያ የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት በቀይ መስቀል አማካኝነት ተቋቋመ። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰላም፣ የግጭት-አልባ እና ሰብዓዊነት መርህዎች ላይ አተኩሮ ትምርት የሚሰጥ የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት አቋቁሟል። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ለተመረጡ ሰልጣኞች ትምህርት ለመስጠት የተዘጋጀው ትምህርት ቤቱ የሥነ-ምግባር እና ሰብዓዊነት ላይ ያተኮሩ ኮርሶች ተቀርጸውለታል ተብሏል። ትምህርት ቤቱ ለጊዜው…
#እንድታውቁት
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ በመሰረተው የሰብአዊነት ትምህርት ቤት አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቀበል አስቸኳይ ማስታወቂያ አውጥቷል።
ማኅበሩ ከደቂቃዎች በፊት በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው ትምህርቱ ለ 1 ዓመት የሚቆይና በልዩ ዲፕሎማ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
የተቀመጡት መስፈርቶች ምንድን ናቸው ?
1. በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ ቢያንስ የቢኤ ዲግሪ (የመጀመሪያ ዲግሪ) ያለው/ያላት፤
2. በሰብአዊ አገልግሎት ዘርፍ ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ ያላት፤
3. ወጣት አመልካቾች፤ በተለይም ከ20-40 አመት ክልል ውስጥ ያሉ ይበረታታሉ፤
4. በተቋሙ የተዘጋጀውን ጹሑፍ መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፤
ተቋሙ ባወጣው አስቸኳይ ማስታወቂያ ተጨማሪ ምን ጠቀሰ?
🟢 ማመልከቻ ቦታው ሳሪስ አደይ አበባ አከባቢ ባለው የቀይ መስቀል ግቢ መሆኑን፤
🟢 የማመልከቻ ቀኑ ከነገ ጥር 22 ጀምሮ እስከ ጥር 30 ባለው ቀናት እንደሆነ፤
🟢 ሁሉም አመልካቾች በአካል ቀርበው ማመልከት እንደሚጠበቅባቸው፤
🟢 አመልካቾች ኦርጅናል ዲግሪ ከሁለት ተጨማሪ ቅጂዎች ጋር ይዘው እንዲገኙ፤
🟢 ዋናውን Student Copy ከሁለት ተጨማሪ ቅጂዎች ጋር ይዘው እንዲመጡ፤
🟢 2 ፎቶግራፎች፤ መጠኑ (2x3) የሆነ ይዘው እንዲገኙ ሲል ገልጿል።
🔸 በተጨማሪም ክፍያን በተመለከተ አመልካቾች አደይ አበባ ካምፓስ በአካል ሲገኙ በምዝገባ ወቅት የሚገለጽላቸው ይሆናል ሲል አስታውቋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አዲስ በመሰረተው የሰብአዊነት ትምህርት ቤት አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቀበል አስቸኳይ ማስታወቂያ አውጥቷል።
ማኅበሩ ከደቂቃዎች በፊት በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው ትምህርቱ ለ 1 ዓመት የሚቆይና በልዩ ዲፕሎማ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
የተቀመጡት መስፈርቶች ምንድን ናቸው ?
1. በየትኛውም የትምህርት ዘርፍ ቢያንስ የቢኤ ዲግሪ (የመጀመሪያ ዲግሪ) ያለው/ያላት፤
2. በሰብአዊ አገልግሎት ዘርፍ ለማገልገል ፍላጎት ያለው/ ያላት፤
3. ወጣት አመልካቾች፤ በተለይም ከ20-40 አመት ክልል ውስጥ ያሉ ይበረታታሉ፤
4. በተቋሙ የተዘጋጀውን ጹሑፍ መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፤
ተቋሙ ባወጣው አስቸኳይ ማስታወቂያ ተጨማሪ ምን ጠቀሰ?
🔸 በተጨማሪም ክፍያን በተመለከተ አመልካቾች አደይ አበባ ካምፓስ በአካል ሲገኙ በምዝገባ ወቅት የሚገለጽላቸው ይሆናል ሲል አስታውቋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የቅድመ ክፍያ ስማርት ቆጣሪዎች ትግበራ መጀመሩ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች በዩኒፋይድ ፕሪፔይመንት ፕሮጀክት የኤስ ቲ ኤስ ስማርት ነጠላ ፈዝ ቆጣሪዎችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
አሁን ላይ ለፕሮጀክቱ ትግበራ የሚያበቁ ሁሉም አስፈላጊ ዕቅዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውንና 2 ሺህ 55 አዲስ ስማርት ነጣላ ፌዝ ቆጣሪዎች የመግጠም ስራ መከናወኑን አገልግሎቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።
በዚህም ደንበኞች ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም ካሉበት ቦታ ሆነው የቶከን ቁጥር በቴሌ ብር እና በሌሎች የክፍያ አማራጮች በመግዛት ኤሌክትሪክ መጠቀም እንዲችሉ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።
በአዲስ አበባ ቆጣሪ የተገጠመባቸው አካባቢዎች፦
- ባልደራስ ኮንዶሚኒየም፣ ፈረስ ቤት እና የካ ሳይት 100 ቆጣሪዎች፣
- ባቱ እና መካኒሳ ኮንዶሚኒየም 1 ሺህ 432 ቆጣሪዎች፤
- ሲ ኤም ሲ ልዩ ቤቶች ጀርባ የመከላከያ ቤቶች 523 ቆጣሪዎች ናቸው፡፡
አገልግሎቱ እንዳስታወቀው በአጠቃላይ በዩኒፋይድ ፕሪፔይመንት ፕሮጀክት 500 ሺህ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን በዘመናዊ ቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎች ለመቀየር ታቅዷል።
አሁን ላይ ከ500 ሺህ ቆጣሪዎች ውስጥ 125 ሺህ በመላው ሀገሪቱ ለሚገኙ ለሶስት ፌዝ ቆጣሪ ተጠቃሚ ደንበኞች ሙሉ በሙሉ ለመቀየር ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፤ 25 ሺህ ነጠላ ፌዝ ስማርት ቆጣሪዎች ደግሞ አዲስ አበባ ለሚገኙ ደንበኞች እየተቀየረ ይገኛልም ብሏል፡፡
#TikvahEthiopia
#EEU

በወንድሟ ጓደኛ ታግታ የነበረችው ታዳጊ ከ14 ቀን በኋላ ማስለቀቁን ፖሊስ አስታወቀ።
በኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የነበረችው መቅደስ ሀይሌ፥ የወንድሟ ጓደኛ በሆነው ግለሰብ ተጠልፏ ከነበረችበት ከ14 ቀን በኋላ ማስለቀቁን የወረዳው የፖሊስ ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የግል ተበዳይ መቅደስ ኃይሌን ያገታት ግለሰብ የወንድሟ ጓደኛ ስለነበር ፎቶዋን ከወንድሟ ስልክ ካየ በኋላ ለሷ መደወል እንደጀመረና ልጅቱ ግን እንደማትፈልገው እንደገለጸችለት የጽ/ቤቱ አዛዥ ተወካይ ረዳት ኢንስፔክተር ደረሰ ቡና ተናግረዋል።
ከዚህም በኋላ ወንጀለኛው ከ6 ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከትምህርት ቤት ስትወጣ ጠብቆ እንዳገታት፤ ከዛም በሳርማሌ ወረዳ ጉምሬ በሚባል ሥፍራ ሰው በሌለበት ጫካ ውስጥ ወስዶ ለ14 ቀን ማገቱን ያግታታል።
ረዳት ኢንስፔክተር ደረሰ ልጅቱ በታገተችበት ወቅት ለ3 ጊዜ ያክል ለማምለጥ ሙከራ ብታደርግም በተደጋጋሚ እየተያዘች ማምለጥ አለመቻሏን ተናግረዋል።
"ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ልጅቱ ታማለች ወደ ጤና ጣቢያ ሊወስዳት ነው ተብለን ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ክትትል ብናረግም ልጅቱን የጤና ባለሙያ ዘመዱ ጋር ወስዷት ስለነበር ምንም ነገር አላገኘም" ሲሉ ነው የተናገሩት።
አክለውም፥ "ዛሬ ጠዋት 2:30 ሰዓት አካባቢ በሞተር በሌላ መንገድ ሊያመልጥ ሲል ክትትል አድርገ ጎሞሮ ቀበሌ ወንዝ ላይ ሲደርስ ወደ ሰማይ 4 ጊዜ ጥይት ተኩሰን ልጅቱን ከእገታው ከ14 ቀን በኋላ ማስለቀቅ ችለናል አጋቹ ግን አምልጧል" ነው ያሉት።
ልጅቱ ከአገቷት 6 ልጆች 3 ብቻ እንደመታቅ ለፖሊስ መረጃ በሰጠችው መሰረት ክትትል እያደረገ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ዋናው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አለመዋሉን አስታውቋል። ለፖሊስ በጥቆማ ከደረሰው መካከል አንዱን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉንም አስረድቷል።
አሁን ላይ ልጅቱ ጤናዋና አካሏ ላይ ጉዳት እንደረሰባት ወይም እንዳልደረሰባት ለማወቅ ምርመራ አድርጋ ውጤት እየጠበቅን ነው ሲሉ ረዳት ኢንስፔክተር ደረሰ ቡና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ተማሪዎችን በነፃ አስተምሮ ሥራ እያስቀጠረ ያለው ኮሌጅ
በኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ በምስራቅ አፍሪካ አዲስ የተሾሙት ፕረዚዳንት ዶንግሁን ሊ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ኤልጂ ኮይካ ሆፕ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በመገኘት ጀምረዋል።
በትላንትናው ዕለት ጉብኝታቸውን በኮሌጁ ያደረጉት ፕረዝዳንቱ የኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ምርት የሆኑ150 እስክሪኖችን በስጦታ መልክ አበርክተዋል።
ኤልጂ ኮይካ ሆፕ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በየአመቱ 100 ብቁ የሆኑ የሙያና ተግባር ተማሪዎች በነፃ ኮሌጁ እያስተማረ ስራ እያስቀጠረ መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ታሪኩ ገብረ መድህን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ባለፉ 10 ዓመታት ከ6 መቶ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቅ የቻለው ኮሌጁ ካለፈው ዓመት ተመራቂዎች ውስጥ 90 በመቶ፣ ከ2 ዓመት በፊት ከተመረቁት ደሞ 100 ፐርሰንት የሥራ እድል እንዲያገኙ ማስቻሉን ተናግረዋል።
የሥራ ዕድል በዋነኝነት ለተማሪዎቹ በሦስት መንገድ እንዲያገኙ እየተመቻቸ መሆኑን የገለጹት አቶ ታሪኩ፥ እንደ ዱባይ፣ ኬንያ፣ ጂቡቲ፣ ሳውዲ አረቢያና ሞሪሼስ ላይ የስራ እድል በማመቻቸት እንዲሁም በራሳቸው ሥራ ፈጥራው እንዲሰሩ እንዲሁም የሀገር ውስጥ ድርጅቶች ውስጥ እንዲቀጠሩ እያረገ መሆኑን ገልፀውልናል።
ቀደም ሲል በኮሌጁ በተማሪነት አሁን ደግሞ በሾፕ ቴክኒሻን ሥራ መደብ እያገለገለች የምትገኘው በረከት ደርብ ኮሌጁ ተማሪ የመሆን እድል ያገኘችው የኮሪያ ዘማች ቤተሰብ ስለሆነች እንደሆነ ትገልጻለች።
ተማሪ በነበረችበት ጊዜም ትምህርት፣ ምሳና ትራንስፖርት በነፃ እንዳገኘች፣ ክላስ የተማሩትን ባሉት የተለያዩ መሳሪያዎች በተግባር እንደሚማሩ፣ ሲመረቁ ሙሉ ወጭ ተሸፍኖ ፕሮጀክት እንደሚሰሩ እንዲሁም ጥሩ ውጤት ላለው ተማሪ ደሞ ከሀገር ውስጥ እስከ ሀገር ውጭ ስራ ኮሌጁ አመቻችቶልናል ብላለች።
ኮሌጁ በአሁኑ ሰአት በ2 ትምህርት አይነቶች ከ250 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ሲሆን ከ20 በላይ ስታፍ ሰራተኞችና ከ25 በላይ አሰልጣኞች አሉት።

'' በታክስ ኦዲት የሚወሰኑ ውሳኔዎች በድጋሜ ኦዲት ይደረጋሉ '' የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ በታክስ ኦዲት የሚወሰኑ ውሳኔዎችን በድጋሜ ኦዲት በማድረግ የውሳኔዎችን ጥራት ለማረጋገጥ በማሰብ አዲስ የሥራ ክፍል ማቋቋሙን አስታውቋል።
በሁሉም ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች በታክስ ኦዲተሮች የሚወሰኑ የግብር ውሳኔዎች በአዲሱ የስራ ክፍል ዳግም የሚረጋገጡ መሆኑን ነው የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ኮምኒኬሽን ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ የተናገሩት።
አዲስ የተቋቋመው የሥራ ክፍል ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በኦዲተር የተወሰኑ ውሳኔዎችን ዳግሞ ጥራታቸውን የማረጋገጥ ሥራ እንደሚሰራ ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል።
አዲስ ስለተቋቋመው የሥራ ክፍል የጠየቅናቸው አቶ ሰውነት አየለ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተውናል፦
"በዋናነት በሁሉም ቅርንጫፍ ኦድተሮች የተወሰኑ ውሳኔዎችን በድጋሜ የማረጋገጥ ስራዎችን ይሰራል፤
እንደየአስፈላጊነቱ ደግሞ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ላይ ትኩረት በማድረግ የተወሰኑት ውሳኔዎች በትክክልም ውሳኔ ስለመሆናቸው የማረጋገጥ ስራ ይሰራል ፤
በልዩት የተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ በዳግም ማጣራት ልዩነት ካለ እንዲከፍሉ የሚያደርግ እና ውሳኔውን በወሰነው ኦዲተር ላይም ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ ነው'' በማለት አስረድተዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም አድሱ የሥራ ክፍል ከኦዲት ስራዎች ጋር በተያያዘ የሚነሱ ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት ያለመ መሆኑን እና ግብር ከፋዩ በአቋራጭ ከግብር ኦዲተሮች ጋር በመደራደር የሚፈፅሟቸውን ወንጀሎች ለማስቀረት የታሰበ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ቢሮው በዘንድሮው ግማሽ በጀት አመት ብቻ ለቢሮው ከቀረቡት ቅሬታወች መካከል ከ55 በመቶ እስከ 60 በመቶ የሚሆኑ ውሳኔዎች መሻሻላቸውን አስታውቋል።
በተጨማሪም ከአራት ወር ዕቅድ ላይ ያልተሰበሰበ 4.2 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ወራት ትልቅ ስራዎች ይጠበቁብናል በማለት አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ዛሬ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ በግማሽ በጀት አመቱ 74 አመራሮችና ፈፃሚዎች ላይ እርምጃዎች መውሰዱን አስታውቋል።
እርምጃዎቹ በተለያዩ ጥፋቶች፣ በብልሹ አሰራር፣ ባለጉዳዮችን በማመናጨቅና በተገቢው ጊዜ ስራን ባለመስራት እና በመሳሰሉት የተወሰዱ እርምጃዎች ናቸው ተብሏል።
ስለ ውሳኔው ማብራሪያ የጠየቅናቸው አቶ ሰውነት አየለ ውሳኔው ከተላለፈባቸው መካከል 8 የሚሆኑት በአመራርነት ደረጃ ላይ የሚገኙ የነበሩ ናቸው ብለዋል።
የተወሰደውም እርምጃ "ከቃል እስከ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ፣ ከስራ እስከ መሰናበት እንዲሁም ከደረጃ ዝቅ እስከ ማድረግ" የሚደርሱ ናቸው ብለዋል።
"ያልተገባ ብልሹ አሰራር ሲፈፅሙ የነበሩም እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው '' ሲሉ አስረድተዋል።

#GlobalBank
🟢 "የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል አገልግሎት አስጀምሪያለሁ" - ግሎባል ባንክ
🟢 "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እናሳካለን" - ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የዲጅታል ባንኪንግ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።
አገልግሎት መስጠት የጀመረው የዲጂታል ባንኪንግ ማዕከል የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ገንዘብ ገቢ ማድረግና ወጪ ማድረግ፣ ቀሪ ሂሳብና የሂሳብ መግለጫ ማሳየት፣ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን መመንዘር፣ የተለያዩ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል ተብሏል።
በተጨማሪም ያለ ኤቲኤም ካርድ አገልግሎት ማግኘት፣ ቼክ መመንዘርና ገቢ ማድረግን ጨምሮ ደንበኞች የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት መጠቀም በሚፈልጉበት ወቅት በማዕከሉ በመገኘት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጁ ታብሌቶች መጠቀም እንደሚችሉም ገልጿል፡፡
ባንኩ በመግለጫው ማዕከሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ክፍል ያለው መሆኑንና ተቀዳሚ (corporate) ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የቪዲዮ ባንኪንግ አገልግሎት ማገኝት የሚያስችላቸው አገልግሎትም እንደሚሰጥ ጠቅሷል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ይህ ማዕከል ሥራ መጀመሩ ባንኩ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረጉም ባሻገር የባለአክሲዮኖችን ጥቅም ከፍ ከማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።
ባንኩ በዘንድሮው አመትም ከታክስ በፊት ብር 757.6 ሚሊዮን ማትረፉን የገለጸ ሲሆን የቅርንጫፍ ብዛቱንም ወደ 238( ሁለት መቶ ሰላሳ ስምንት ) ከፍ ማድረግ ችሏል። በአሁን ሰዓትም ባንኩ ከ 1.7 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አሳውቋል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደ/ር ተስፋዬ ቦሩ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የባንክ ካፒታል ዕድገት ዝቅተኛ ጣሪያ በቀረው ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳካ ገልጸዋል።
ባንኩ የተቀማጭ ሂሳቡን ከ 20.6 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ መሆኑንና የባንኩ ጠቅላላ ሃብት ደግሞ ከ 26.6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንም አስታውቋል።
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሜክሲኮ አካባቢ ለዋና መ/ቤት ግንባታ በተረከበው 5,550 ካ.ሜ ቦታ ላይ የወደፊት የዋና መ/ቤት ህንፃ ለመገንባት በሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እየሰራ እንደሆነም ለማወቅ በላከልን መግለጫ ጠቅሷል።

ከ600 በላይ የሚሆኑ ማኅበራት እና ኮንተራክተሮች የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰራንበትን ክፍያ በተባለው ቀን ውስጥ አልከፈለንም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
"እያንዳንዱ ማህበር እና ኮንተራክተር ከ 3 እስከ 40 ሚሊየን ብር ወጪ አድርጓል፤ ቤቶቹም አልቀው ነዋሪ ገብቶባቸዋል። ሆኖም ግን ክፍያ እስከአሁን አልተከፈለንም" ሲሉ ነው ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት።
በተጨማሪም ቅሬታ አቅራቢዎቹ "ሥራውን በሁለት ሳምንት ውስጥ ካጠናቀቃችሁ በአንድ ሳምንት ውስጥ ክፍያችሁን እንፈፅማለን የሚል ቃል ገብተውልን ነበር" ሲሉ ክፍያቸው በጊዜ አለመፈጸሙን አስረድተዋል።
አያይዘውም፥ ''ሥራውን ካጠናቀቅን ከአንድ ወር በላይ ሆኖናል ከስራው አስቸኳይነት አንፃር በብድር ጭምር ነው የሰራነው" በማለት ክፍያው መዘግየቱ ጫና እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሽመልስ ታምራትን ጠይቀናል። ዋና ዳይሬክተሩ ለሁሉም ኮንትራክተሮች እና ማህበራቶች ክፍያቸውን ለመፈፀም ጥረት እያደረግን ነው የሚል ምላሽ ሰጥተውናል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት በዝርዝር ምን አሉ ?
ዳይሬክተሩ የከተማ አስተዳደሩ በጫረታ የሚሸጡ የንግድ ቤቶችን ወደ መኖሪያ ቤት ለመቀየር የወሰነውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ የንግድ ቤቶችን በፍጥነት በመቀየር ለዜጎች ለማስረከብ የተለያዩ ማኅበራትንና ኮንተራክተሮችን ማሰማራቱን ገልፀዋል።
በዚህም ከ400 የማያንሱ ኮንትራክተሮች እና ማኅበራት እንደተሳተፉ እንዲሁም ሥራውንም ሰርቶ ለማጠናቀቅ 57 ቀናቶች መውሰዳቸውን ዳይሬክተሩ አክለዋል።
ክፍያቸውን በተመለከተ ላነሳንላቸው ጥያቄ በከተማችን በተለያዩ ቦታዎች በኮርፖሬሽኑ ስር ባሉ ቅርንጫፎች አማካኝነት እንደ አፈፃፀማቸው የክፍያ ሰነዶቻቸው በሂደት እየመጣ እየተከፈላቸው ነው ብለዋል።
"ከሁሉም ቅርንጫፎች ሂደቱን ጨርሶ የመጣውን እየከፈልን ነው እስካሁን ከ270 በላይ ለሚሆኑ ኮንተራክተሮች እና ማህበራቶች ክፍያቸው ተሰጥቷቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ክፍያ ያልተሰጣቸው ኮንትራክተሮች እና ማኅበራቶች ደግሞ አፈፃፀማቸው በቅርንጫፎች ተገምግሞ ሂደቱን ጠብቆ ባለመምጣቱ መዘግየቱን ነው ያነሱት።
በቢሮ ደረጃ ቅሬታ ያቀረቡ ኮንትራክተሮች እና ማኅበራቶች መኖራቸውን የገለጹት ዳይሬክተሩ ከቅሬታ አቅራቢዎች መካከልም ይህ ዘገባ እስከ በተጠናከረበት ድረስ የተከፈላቸው ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል።
እስካሁን ክፍያ ላልተሰጣቸው ማኅበራቶች እና ኮንተራክተሮች ክፍያቸውን ለመክፈል በቢሮ ደረጃ እየተሰራ መሆኑንም ነው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት።
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፥ "ነዋሪውን ለመታደግ ሥራው በአስቸኳይ ሌት ከቀን ነው የተሰራው፤ ክፍያቸውም ቅደም ተከተላቸውን ተከትሎ እየተፈፀመ ነው" ሲሉ አስረድተዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"በጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በመቸገራቸን ትልቅ ፈተና ውስጥ ነን" የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት
ከሌሎች ወሮች በተለየ መልኩ በየዓመቱ ጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚቸገር የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በአገልግሎቱ የደም ለጋሾች መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ዶክተር መላሽ ገላው በ2016 አ.ም እንደ ሀገር 349 ሺ ዩኒት ደም መሰብሰቡን፤ ይህም የእቅዱን 82% መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመት 6 ወራት እንደሀገር 217 ሺ ዩኒት ደም በላይ መሰብሰቡን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 55 ሺ 300 ዩኒት ደም ከአዲስ አበባ ከተማ የተሰበሰበ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የጥር ወር ፈተና
ዶክተር መላሽ፥ ''በተለይ ከሌሎች ወሮች በተለየ መልኩ በየዓመቱ ጥር ወር ደም ለመሰብሰብ በተለያዩ ምክንያቶች ስለምንቸገር ትልቅ ፈተና ውስጥ ነን '' ሲሉ ወቅቱ ደም ለመሰብሰብ አስቸጋሪ መሆኑን ያነሳሉ።
ለማሳያም፤ "ተማሪዎች ፈተና የሚፈተኑበትና ዕረፍት የሚሆኑበት ጊዜ መሆኑን፤ ስለሆነ ባለፍቱ 2 ሳምንታት ውስጥ ከትምህርት ቤቶች ምንም አይንት ደም አላገኘንም" ያሉት ዶ/ር መላሽ የበዓላት መደራረብም ተጽዕኖ እንዳለው ጠቅሰዋል።
ከበዓላት ጋር ተያይዞሞ በተለያዩ ምክንያቶች ደም መሰብሰቢያ ቦታዎች ፈቃድ ባለማግኘታቸው በጥር ወር ከታሰበው 60% በታች የሆነውን ብቻ ማሳካት መቻላቸውን ነው የገለጹት።
ያለውን ክፍተት ለመሙላትም ከበጎፈቃደኞች ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው "ሚዲያዎችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ደም ለመሰብሰብ እየሞከርን ነው "ብለዋል።
አክለውም "ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና እሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኮሪደር ልማቱን በሚመጥን መልኩ ቋሚ ወይም ተንቀሳቃሽ የደም መሰብሰቢያ ቦታዎችን ለማግኘት እየሰራን ነው" ሲሉ ነግረውናል።
በክልሎች የደም የመሰብሰብ ምጣኔን ለመጨመር ባለሙያዎችን ወደ ክልሎች በመላክ ሙያዊ ድጋፍ እንዲያረጉ እየተደረገ ነው ያሉን ዶ/ር መላሽ፥ "የየክልሎች ጤና ቢሮዎች ደም ማሰባሰብ ላይ ትኩረት ሰጠው እንዲሰሩ አቅጣጫ ተቀምጧል '' ሲሉ ገልፀዋል።
የሚመጡት ወራቶች ከዚህ የበለጠ የደም መሰብሰባችን ምጣኔ ሊቀንስ እንደሚችል ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን ለዚህም ማህበረሰቡ ደም በመለገስ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

በሰመራና ሎጊያ ከተማ ያሉ አሽከርካሪዎች በቤንዚን እጥረት መቸገራቸውን ገለጹ።
በአፋር ክልል ሰመራና ሎጊያ ከተማ በርካታ አሽከርካሪዎች ቤንዚን በከተማዋ ባሉ ማደያዎች በሕጋዊ መንገድ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ በሕገወጥ መንገድ በችርቻሮ ከሚሸጡ የጥቁር ገበያ ነጋዴዎች በሊትር እስከ 300 ብር ለመግዛት ተገደናል ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
በነዳጅ ዕጦትና በጥቁር ገበያ ችግር በአመዛኙ ተጎጂ የሆኑትና ለከተማዋ የሕዝብ የትራንስፖርት ዋነኛ አማራጭ ናቸው የሚባሉት ባለሦስት እግር ባጃጆች እና ሞተሮች ናቸው።
በመሆኑም የሰመራ ከተማ የባጃጅ አሽከርካሪ የሆኑት አቶ አብዱል ኖሮ ቤንዚን እስካሁን በብር እስከ 170 ነበር የምንገዛው አሁን ግን ቤንዚን ጠፍቷል በመባሉ ከጥቁር ገበያ በብር ከ180 እስከ 300 እየገዛን ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለቲክቫህ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም "ወደ ከተማችን ማደያዎች ቤንዚን ሲገባ እናያለን ነገር ግን ከገባ ከሁለት ቀን ቡኋላ አልቋል ነው የሚሉን" ሲሉም ተናግረዋል።
በተደጋጋሚ ለክልሉ ንግድ ቢሮ ቅሬታዎችን አቅርበናል ያሉት አቶ አብዱል ሁሌም መፍትሄ እንሰጥሀቹኋለን ከማለት የዘለለ ምንም መፍትሄ እያገኘን አይደለም ብለዋል።
የነዳጅ ስርጭቱን እና አቅርቦቱን በተመለከተ የክልሉን ንግድ ቢሮ ክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አብዱ አሊን ጠይቀናል።
በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት እጥረት መኖሩን ዳይሬክተሩ የተናገሩ ሲሆን በተለይም ሰመራ፣ ሎጊያ ፣ አዋሽ አርባ እና አዋሽ ሰባት በሚፈለገው ልክ ለአሽከርካሪዎች በቂ የሆነ ቤንዝን እያገኘን አይደለም ሲሉ ገልፀዋል።
ዳይሬክተሩ ችግሮች የተፈጠሩት በአቅርቦት ማነስ እና በከተሞች የ3 እግር ተሽከርካሪዎች ቁጥር በመጨመሩ መሆኑን አስረድተዋል።
ከተሽከርካሪዎች ቁጥር ጋር ወደ ክልላችን የሚገባው የቤንዚን አቅርቦት አይመጣጠንም ይህም ለህገወጥ ንግድ በር ከፋች ነው ብለዋል።
አክለውም ወደ ክልሉ የሚገቡት ነዳጆች በሶስት በአራት ማደያዎች ይራገፋሉ ሁሉም ማደያ የሚገባውን ያክል ያገኛል ማለት ግን አይቻልምም ። ምክንያቱም ነዳጅ በአራት በአምስት ቀን ነው የሚላክልን ብለዋል።
ቤንዚን ደግሞ በሰመራ ፣ ሎጊያ እና ጋላስ በሚወርድበት ጊዜ ሙቀት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንደሌሎቹ አካባቢዎች በሚፈለገው ስዓት መቅዳት አይቻልም፤ ይህም ለችግሩ መባባስ ዋነኛ ምክንያት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ቅሬታ አቅራቢ አሽከርካሪዎች ''በክልሉ 1 ሊትር ቤንዚን በብር ከ180 እስከ 300 እየተሸጠ ነው'' ሲሉ ላቀረቡት ቅሬታ የክልሉ የንግድ ክትትል እና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ አብዱ አሊ ምን አስተያየት ሰጡ
'' በህገወጥ መንገድ በአንዳንድ ቦታዎች ሊሸጥ ይችላል። ነገር ግን በዚህን ያክል የተጋነነ ዋጋ ይሸጣል የሚለውን እስካሁን በተጨባጭ አላየንም ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
አክለውም ህገወጥ ቸርቻሪዎች ከማደያዎች ምንም አይነት ነዳጅም ሆነ ቤንዚን አይወስዱም ብለዋል።
ዳይሬክተሩ በአዋሽ አርባ አካባቢ ህገወጥ የቤንዚን ንግድ ለማካሄድ በተለያዩ ጫካዎች ጀርካዎችን በማዘጋጀት ላይ እያሉ ግለሰቦች በፖሊስ ተይዘዋል ያሉ ሲሆን ሰመራ ከተማም ተመሳሳይ ሂደቶች ላይ የነበሩ ግለሰቦች በማህበረሰቡ ጥቆማ ተይዘዋል ብለዋል።
የክልሉ ንግድ ቢሮ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከማደያ ባለቤቶች ጋር በመነጋገር እና ግብረ ሀይል በማቋቋም እየሰራ መሆኑን አብራረተዋል።
ከዚህ በፊት በአዋሽ አርባ መሰል ችግሮች ነበሩ ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ችግሮች መቀረፋቸውን ገልፀዋል።
አያይዘው የቤንዚን እጥረት ባለባቸው ከተሞች በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ወጣቶችን በማህበር በማደራጀት ማደያዎችን በመገንባት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ክልሉ ከነዳጅ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር ችግሩን ለመቅረፍ የነዳጅ አቅርቦት እያስጨመረ ነው። ያም ሆኖ ግን አሁንም በቂ አይደለም ብለዋል።
በህገወጥ መንገድ ከዚህ በፊት ቤንዚን ጭነው ሊያከፋፍሉ የነበሩ ቦቴዎች ከተደበቁበት በክልሉ ንግድ ቢሮ እና የፀጥታ አካላት ተይዘው እርምጃዎች ተወስደዋል አሁንም እየወሰድን ነው ሲሉ አክለዋል።
ከአንድ ማደያ ጀርባ ተደብቆ 3200 ሊትር በብር ከ250 ሺህ በላይ የሚገመት ቤንዚን ሲሸጥ የነበረ ግለሰብ በክልሉ ፖሊስ ተይዞ በህጉ አግባብ እርምጃዎችን ለመውሰድ በሂደት ላይ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ማህበረሰቡ ለፀጥታ አካላት እና ለክልሉ ንግድ ቢሮ ጥቆማ በመስጠት እንድትተባበር መልዕክት አስተላልፈዋል።