#Telegram
የቴሌግራም መተግበሪያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓቬል ዱሮቭ የቴሌግራም ቻናል ተጠቅመው መልዕክታቸውን የሚያጋሩ ያላቸውን የሀገራት መሪዎች ዝርዝር አጋርቷል። በዚህም የማረጋገጫ ምልክት ካገኙ የሀገራት መሪዎች መካከል ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ተጠቅሰዋል።
የብራዚል፣ የቱርክ፣ የሜክሲኮ፣ የፈረንሳይ፣ የሲንጋፖር፣ የእስራኤል፣ የታይዋን፣ ዩክሬንና የኡዝቤክስታን ሀገራት መሪዎችም የማረጋገጫ ምልክት አግኝተው ኃሳባቸውን በቴሌግራም የሚያጋሩ ናቸው ተብሏል።
የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ መሆኑንና የመደበኛ ተጠቃሚዎች ቁጥርም ከ500 ሚሊዮን ማለፉን የድርጅቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓቬል ዱሮቭ አስታውቋል።
@tikvahethmagazine @tikvahmagBot

#Telegram ✅️
ቴሌግራም በየጊዜው የተለያዩ ማዘመኛዎችን እንደሚያወጣ ይታወቃል። በቅርቡም ተጠቃሚዎች ፎልደር ለሌሎች እንዲያጋሩ የሚያስችላቸውን አሰራር ዘርግቷል።
ይኽም አዲስ ፎልደር በመክፈት፤ ለፎልደሩ ርዕስ በመስጠት፤ በፎልደሩ ውስጥም ቻናሎችን፣ ግሩፖችን በማካተት ያንን ፎልደር ለሌሎች ማጋራት የሚችሉበት አሰራር ነው።
ለምሳሌ፥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቤተሰቦቹ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያደርስበት 5 የቴሌግራም ቻናሎች አሉት፤ እኚህን ቻናሎች "TIKVAH-ETH" በሚል ፎልደር በልዩነት ለብቻቸው በአንድ ላይ https://yangx.top/addlist/xqDa5E_XS9M4NTJk ላይ ማግኘት ይችላሉ።
#ማስታወሻ: ከላይ የተጠቀሰው ሊንክ የማይከፍትሎ ከሆነ ኦፊሴላዊውን ቴሌግራም (የቴሌግራም ዋናውን መተግበሪያ) ይጠቀሙ ወይም ቴሌግራሞን ያዘምኑ።
@tikvahethmagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#TelegramTips
ቴሌግራም በቅርቡ "ቴሌግራም ስታርስ/Telegram Stars" የተሰኘ አዲስ ምናባዊ ገንዘብ (virtual currency) ማስተዋወቁ ይታወሳል።
ይህን ሥርዓት በመጠቀም ቴሌግራም ለይዘት ፈጣሪዎች እና ለቻናል ባለቤቶች አዲስ ነገር አስተዋውቋል።
አንደኛው ቀጥታ ከቻናሉ አባላት የሚሰጥ የስታር ሥጦታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ተከታዮች በክፍያ ይዘቶችን እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ነው።
1. ሥጦታ
የቻናል ባለቤቶች ሥጦታዎችን ከአባሎቻቸው መቀበል ከፈለጉ በመጀመሪያ የቻናላቸውን ገጽ ማስተካከያ ላይ በመግባት Reaction የሚለው ውስጥ Enable Paid Reaction የሚለውን መፍቀድ/ማብራት ይጠበቅባቸዋል።
ተጠቃሚዎች በበኩላቸው የሚፈልጉትን ይዘት ለመደገፍ ሲፈልጉ ወይም የወደዱት ልጥፍ ካለ የስታር ሥጦታ ልክ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ኢሞጂዎችን ሪአክት በሚያደርጉበት መንገድ የሚፈልጉትን ያክል መጠን መስጠት ይችላሉ።
2. በክፍያ የሚቀርብ ይዘት (Subscription)
ይዘት አቅራቢዎች በክፍያ ለሚያቀርቡት ይዘት ወርኃዊ ክፍያ ማስከፈል የሚያስችላቸው ሲሆን ይህንም ተጠቃሚዎች ለየት ያሉ ይዘቶችን ቀድመው ወይም በልዩነት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው። (ይህ አገልግሎት አሁን ላይ አልጀመረም)
ቴሌግራም ለተጠቃሚዎች ከደረሰ 11 ዓመት ሞልቶታል። እስካሁን 950 ሚሊዮን ንቁ ተሳታፊዎች እንዳሉት የገለጸ ሲሆን በ2024 1 ቢሊዮን ለመገንባት እቅድ አለው።
የቴሌግራም ስታር እንዴት ማግኘት ይቻላል 👉 https://yangx.top/tikvahethmagazine/22673
#TikvahTechTeam #Telegram

#Telegram ❤ 🇺🇦
ዩክሬን የቴሌግራም የመልእክት መላላኪያ መድረክን ለመንግስት እና ወታደራዊ ሰራተኞች እንዲሁም ለመከላከያ ሴክተር እና ወሳኝ የመሠረተ ልማት ሰራተኞች በተሰጡ ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች ላይ አገልግሎት ላይ እንዳይውል አግዳለች።
እገዳው የግል የሞባይል ስልኮችን አያካትትም ተብሏል።
እግዱ የወጣው በ2022 በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ በጀመረችው ሩሲያ የሚፈጠረውን ስጋት “ለመቀነስ” ነው ሲል የሀገሪቱ ኃያል የብሄራዊ ደህንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ተናግሯል።
የደህንነት ምክር ቤቱ "ጠላት ቴሌግራምን ለሳይበር ጥቃት፣ለተንኮል አዘል ሶፍትዌሮች ስርጭት፣ለሚሳኤል ጥቃት ቦታ ጥቆማ በንቃት ይጠቀማል" ሲል ለእገዳው ምክንያቱን አስቀምጧል።
ቴሌግራም የዩክሬን እና የሩሲያ የመንግስት እና የጦር ባለስልጣናት በስፋት የሚጠቀሙት የመረጃ መለዋወጫ መተግበሪያ ነው።
እገዳው ተግባራዊ እንዲሆን በዩክሬን ከፍተኛ የመረጃ ደኅንነት ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ እና የህግ አውጭዎች ባደረጉት ስብሰባ ከስምምነት ላይ መደረሱን ምክር ቤቱ በሰጠው መግለጫ ተናግሯል።
የወታደራዊ መረጃ ሃላፊው ኪሪሎ ቡዳኖቭ እንደገለጹት የተሰረዙ መልእክቶችን እና የተጠቃሚዎችን ግላዊ የመልእክት ልውውጦችን የሩስያ ሃይሎች ማግኘት መቻላቸውን የሚያሳዩ ተአማኒ ማስረጃዎች አሉ ብሏል።
"የመናገር ነፃነትን ሁሌም እደግፋለሁ ነገር ግን የቴሌግራም ጉዳይ የመናገር ነፃነት ጉዳይ አይደለም፣ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳይ ነው" ሲል ቡዳኖቭ ተናግሯል።
ቴሌግራም መጠቀም የስራቸው አካል የሆኑ ባለስልጣናት ከእገዳው ነፃ ይሆናሉ ተብሏል።
ቴሌግራም ለቢቢሲ በሰጠው መግለጫ "ሩሲያን ጨምሮ ለየትኛውም ሀገር ምንም አይነት የመልዕክት መረጃ አላቀረበም" ብሏል።
አክሎም አንድ ጊዜ የተሰረዙ መልእክቶች ከተሰረዙ በኋላ ዳግም የሚታዩበት በቴክኒክ ደረጃ ምንም አይነት መንገድ የለም ሲልም ገልጿል።