TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
TIKVAH-MAGAZINE
#Update: ሂዝቦላህ መሪው ሀሰን ነስረላህ መሞቱን አረጋግጧል ሂዝቦላህ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በለቀቀው መግለጫ መሪው ሀሰን ነስረላህ መሞቱን አስታውቋል። ቀደም ሲል የእስራኤል ጦር በኢራን የሚደገፈውን የሂዝቦላ ታጣበቂ ቡድን መሪ በትላንትናው ዕለት በቤሩት በፈጸመው ጥቃት መግደሉን መግለጹ ይታወሳል። @tikvahethmagazine
#Update: ሂዝቦላ ምክትል መሪው የነበሩትን ናይም ቃሲምን አዲሱ አለቃ አድርጎ መሾሙን አስታውቋል። የታጣቂ ቡድኑ መሪ ሀሰን ነስረላህ በቅርቡ በእስራኤል ጥቃት መገደሉ ይታወሳል።

እስራኤል የጥቃት አቅጣጫዋን በሊባኖስ ቡድን ላይ ካደረገች በኋላ በርካታ የሂዝቦላህ ከፍተኛ ባለስልጣናት መግደሏን አስታውቃለች።

@tikvahethmagazine
#Update

በቦሌ ክፍለ ከተማ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አጋጥሞ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤ እና የውድመት መጠኑ እየተጣራ መሆኑን አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

አደጋው በቆርቆሮ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች እና ሁለት የውኃ ቦቴ ከ70 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሰማራታቸውንም ተነግሯል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
በኢትዮጵያ የሚገኙ ናይጄሪያውያን እስረኞችን ሁኔታ ሊያጣራ እንደሆነ የናይጄሪያ ምክር ቤት አስታወቀ። በኢትዮጵያ ከ250 በላይ የሆኑ እስረኞችን ሁኔታ ለማጣራት የናይጄሪያ ምክር ቤት አባላት ያቀረቡትን የውሳኔ ሃሳብ ተከትሎ ፥ ኢትዮጵያ ውስጥ በናይጄሪያውያን እስረኞች ላይ ተፈፀመ ስለተባለ ህገወጥ ድርጊት ሊጣራ መሆኑ ተገልጿል። የናይጄሪያ መንግስት ባለፈው ሳምንት ዶ/ር ፖል ኢዚኬ የተባለ ግለሰብ…
#Update: በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙ 270 ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ ተሰጠ

የናይጄሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያሉ ከ270 ያላነሱ ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ይህንን ትእዛዝ እንዲያስፈፅሙ ትእዛዝ የሰጠው ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን እንደሆነ የናይጄሪያ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።

ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን ያስተላለፈው ኢትዮጵያ  ለእስረኞቹ የሚሆን ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች ግብአቶችን ለመሸፈን የሚያስችል በጀት እንደሌላት በመግለጿ መሆኑ ተነግሯል።

የናይጄሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም በአደገኛ እፅ ዝውውርና ሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናይጀሪያዊያን በቃሊቲ እስር ቤት  እንደሚገኙ ገልጾ ነበር።

ከ250 በላይ ናይጀሪያዊያን እስረኞች ኢትዮጵያ ውስጥ አግባብ ባለሆነ መንገድ መያዛቸውን የሀገሪቱ የመብት ተከራካሪዎች ገልፀው የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ያሉ ናይጄራዊያን እስረኞችን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩም አይዘነጋም።

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን በላይ ፍልሰተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን ሰባ አንድ ሺ በላይ ፍልሰተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እያስተናገደች ያለች መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው ሲገለጽ 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እድሜያቸው 0-…
#Update

° "ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም" - የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይና አፋር ክልል በኩል ከኤርትራ የሚገቡ ስደተኞች ጥበቃ እና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ሲል በሪፖርቱ ጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

ቢቢሲ በሰራው ዘገባም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች መጠነ ሰፊ እስራት እየተፈጸመባቸው ፖሊስ የሚወስደው ርምጃ እየተጠናከረ መምጣቱን ዘግቦ ነበር።

ይህን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጉዳዩ ላይ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥቷል።

አገልግሎቱ በመግለጫው፥ የሚዲያዎቹን ዘገባ ተከትሎ አደረኩት ባለው ማጣራት፣ ሕጋዊ የስደተኝነት ዕውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች በሀገሪቱ አለመኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በዚህም በሀገሪቱ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስርና እንግልት እየተከናወነ ነው በሚል በሀገር ውስጥና በውጭ ሚዲያ አውታሮች የተሰሩ ዘገባዎችን ተቋሙ "መሠረተ ቢስ" ሲል አጣጥሎታል።

አክሎም፥ ስደተኞች የሀገሪቱን ሕግና ሥርዓት ጥሰው ለእስር የተዳረጉበት ሁኔታ የሚኖር ከሆነ፣ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የሚከታተለው ይሆናል ሲል አክሎ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የስደተኞች ምዝገባ ቆሟል በሚል ሚዲያው የሚያሰራጨው መረጃም ከእውነት የራቀ ነው ያለው አገልግሎቱ፥ "የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኝነት መስፈርትን ለሚያሟሉ አካላት ምንም ልዩነት ሳያደርግ የምዝገባ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ እየሰጠም ይገኛል" ብሏል፡፡

የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የምስክር ወረቀት አገልግሎትን ጨምሮ የስደተኝነት መታወቂያ የመስጠት ተግባር ከበፊቱ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት ከለላና ጥበቃ ፈልገው ለመጡ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከለላና ጥበቃ እየሰጠች ትገኛለች፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ኤርትራ የሚመጡ ስደተኞች ናቸው፡፡

#Ethiopia
#Eritrea
#Refugees

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Update ° "ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም" - የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይና አፋር ክልል በኩል ከኤርትራ የሚገቡ ስደተኞች ጥበቃ እና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ሲል በሪፖርቱ ጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል። ቢቢሲ…
#Update

° "ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ አገር ሰዎች ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክ ተሰማርተው ይገኛሉ"

° "ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የአገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል" -
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የተሰሩ ዘገባዎችን አስመልክቶ በትላንትናው ዕለት የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት "ሕጋዊ የስደተኝነት ዕውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች በሀገሪቱ የሉም" የሚል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በበኩሉ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ የህግ ጥሰት የፈፀሙ የውጭ ዜጎችን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ከጎረቤት አገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎች ለ9ዐ ቀናት ያለ ቪዛ ክፍያ በቀን ማህተም ገብተው እንዲቆዩ መፈቀዱን አስታውሷል።

ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የውጭ አገር ሰዎች የስራ ፈቃድና መኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸው ባልተፈቀደላቸው የሥራ መስክና ህገወጥ የማዕድን፣ የገንዘብ፣ አደገኛ እፅ፣ የሰዎች ዝውውርና መሰል ህገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ብሏል።

በተለይ በርካታ ኤርትራዊያን ወደ ሀገር የሚገቡት በህገወጥ መንገድ ነው ያለው መግለጫው ከተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ በላይ በመቆየት በህገ-ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ሲል ከሷል።

በዚህም

- ለውጭ አገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች በመሰማራት በህገወጥ መንገድ ከትንሸ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ያልተፈቀዱ ትላልቅ ስራዎች ተሰማርተው ሳለ፤

- በርካታ የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸው ዘመድ ለመጠየቅ በማስመስል ከዱባይ፣ ከኤርትራ፣ ከኡጋንዳ በመመላለስ የኮንትሮባንድ እና ሌሎች ህገወጥ ተግባራት ሲያከናውኑ፤

- በተለያዩ አገራት ከሚገኙ ሌሎች ህገ-ወጥ ደላሎች ጋር በመተሳሰር ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሲሳተፉ፤

- ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የሚያገለገሉ ሐሰተኛና የተጭበረበሩ የጉዞና የይለፍ ሰነዶች፣ ማህተሞች፣ የባንክ ቡኮች በማዘጋጀትና በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራት ሲፈጽሙ ተገኝተዋል ብሏል።

መግለጫው አክሎም ማንኛውም የውጭ አገር ዜጋ የአገራችንን ህግ ተላልፎ ከተገኘ በህግ ተጠያቂ ይሆናል። ይህ ግን በአንድ ሀገር ዜጋ ብቻ ተፈጻሚ የሚደርግ አሰራር ተደርጎ በአንድ አንድ ሚድያዎች መዘገቡ ስህተት ነው ብሏል።

በተጨማሪም በስደተኝነት የተመዘገበ ማንኛውም የኤርትራዊ ዜግነት ያለው ሰው ያለ ፈቃዱ ከአገር እንዲወጣ እና ተገቢነት የሌለው ክፍያ እንዲክፍል የተደርግ ሰው የለም ብሏል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ እንዲሁም ከዚያ በፊት ወደ አገር ለመመለስ ጠይቀው የመውጫ ቪዛ ሲጠባበቁ የነበሩ 316 ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በቤይሩት-ሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጀነራል ጽ/ቤት አስታውቋል።

ከተመለሱት ዜጎች ውስጥ 167 ዜጎች  በሊባኖስ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉና በሊባኖስ ከአለም አቀፉ የስደተኞች  ድርጅት(IOM) ጋር በመተባበር ረቡዕ ታህሳስ 2 ቀን ወደ አገር እንዲመለሱ የተደረጉ ሲሆኑ 17 እናቶችና 22 ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሊባኖስ ረዥም ዓመታት ሲኖሩ የነበሩ ሰነድ አልባ ዜጎቻችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ባቀረቡት በጥያቄያቸው መሠረትት ደግሞ 149 የሚሆኑት ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል።

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

በትላንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ "ጎቱ ኦኖማ" በተባለው አከባቢ ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ በተራሮች ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ መገለጹ ይታወሳል።

ወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ መሰረት አደጋው በመንግስትና በህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቋል።

ቢሮው እንዳስታወቀው ባጋጠመው የእሳት አደጋ ​​በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አለመድረሱን ገልጿል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ስለሚፈጸሙ የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀሎች መግለጫ ሰጠ ° "በርካታ ግለሰቦች የዚህ ድርጊት ሰለባ በመሆናቸው ተግባሩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል" - ፖሊስ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ከሰሞኑ የአንዳንድ የግለሰቦችን የማህበራዊ ሚዲያ አካውንት "በመጥለፍ /ሀክ በማድረግ /" የቅርብ ከሚሏቸው ሰዎችን በማውራት ገንዘብ እንዲልኩላቸው በማድረግ የማጭበርበር…
#Update: በቴሌግራም የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የግለሰቦችን የቴሌግራም አድራሻ በተለያዬ ዘዴ በመጥለፍ በስማቸው ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከሰሞኑ የግለሰቦችን የቴሌግራም አካውንትን በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል ስለሚፈጽሙ ወንጀለኞች መበራከት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም አንድ ወንጀለኛ የአንድ ግለሰብን የቴሌግራም አካውንት በመጥለፍ የተቸገረ በማስመሰል ገንዘብ ጠይቆ በማስላክ ለግል ጥቅሙ ሊያውል የነበረው ተጠርጣሪ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር መሀመድ ይማም እንዳሉት ከሰሞኑ አንድ የግል ተበዳይ የቅርብ ቤተሰቡ የሆነች ልጅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለችና ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት በቴሌግራም አድራሻዋ 340 ሽህ ጠየቀችው ያለውን 180 ሺህ ብር ከላከ በኋላ ሲያጣራ አድራሻዋ መጠለፉ ተረጋገጠ ብለዋል።

በዚህ መነሻነት ፖሊስ ተከታትሎ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀው አሁን አሁን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማጭበርበር ስራዎች እየጨመሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

በመጨረሻም ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሂደት ማህበረሰቡ ላደረገላቸው ጥቆማ ያመሰገኑት ም/ኢንስፔክር መሀመድ ይማም  ወደ ፊትም ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@tikvahethmagazine
🚨 #Alert

"ማዜ ብሔራዊ ፓርክ ትላንትና ማታ አካባቢ በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በማሻ ሞርካ ቀበሌ እርሻ ማሳ የተነሳው ሰደድ እሳት ከቁጥጥር በላይ እየሆነ ስለሆነ የሚመለከተው ኢትዮጵያዊ እገዛ እንድታደርጉ እንጠይቃለን።" - ማዜ ብሔራዊ ፓርክ

#Update : በማዜ ብሔራዊ ፓርክ የተነሳው ሰደድ እሳት ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፓርኩ ገልጿል። የእሳቱ መነሻም በመጠራት ላይ ይገኛል ብሏል።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ "ኢፋ ቢያ" በተባለው ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሟቾች ቁጥር 26 አልፏል ሲል ኤፍ ኤም ሲ አፋን ኦሮሞ ዘግቧል።

የዞኑን የትራፊክ ቢሮ ጠይቆ በሰራው ዘገባ 42 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ጠቅሷል።

የቢሮው ኃላፊ ኢኒስፔክተር አስናቀ መስፍን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል አስረድተዋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

"እስካሁን የተገኘ አስከሬን የለም" - አይ ኦ ኤም

181 ስደተኞችን ጨምሮ የጀልባ ሰራተኞችን ጭኖ ወደ የመን ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በየመን ባህር ዳርቻ ከሰጠመ በኋላ ቀድሞ እንደተረፉ ከተገለጸው ሁለት የጀልባው ሠራተኞች ውጪ የአንድም ስደተኛ አስክሬን ማግኘት አልተቻለም ተብሏል።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ስደተኞቹ ከጅቡቲ መነሳታቸውን በይፋ ባይገልጽም አሶሺየትድ ፕሬስ (ኤፒ) ግን አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ዘግቧል።

በሁለቱ ጀልባዎች ተሳፍረው ከነበሩ ስደተኞች 57 ሴቶች እንደሆኑ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ገልጿል።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን በይፋ የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update: በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳንዲ ወረዳ በደረሰ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ የሆነውና ከግንደበረት ወደ ጊንጪ ከተማ ሲጓዝ የነበረው የሰሌዳ ቁጥሩ ኦሮ 64318 የሆነ ተሽከርካሪ ጊንጪ ከተማ መግቢያ ላይ ልዩ ስሙ "አናኖ" በተባለው ቦታ ተገልብጦ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ሌሎች 16 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጊንጪ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በጊንጪ ጤና ጣቢያ ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው ምክንያት በመጣራት ላይ እንደሚገኝም የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
ዲጅታል የትራፊክ አደጋ መረጃ መሰብሰቢያ ሥርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ። የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከፌድራል ፖሊስ ጋር ያለሙት ዲጅታል የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ መመዝገቢያ ስርዓት የሙከራ ትግበራ ተጠናቆ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊተገበር መሆኑ ተገልጿል። ይህንን አስመልክቶ የአገልግሎቱ የተቋም ሪፎርም ሥራ አስፈፃሚና የትራፊክ መቆጣጠር ማዕከል ኃላፊ አቶ ባዩ ሙሉጌታን ተጨማሪ…
#Update

የትራፊክ አደጋ መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓት የሚያዘምን ሶፍትዌር ከስድስት ወራት የሙከራ ጊዜ በኋላ በዛሬ ዕለት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱ ተገለጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና የመንገድ ደኅንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ሶፍትዌሩ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጀማል አባሶ ሶፍትዌሩ ከሁለት ዓመት የዝግጅት እና 6 ወራት ከቆየ የሙከራ ጊዜ በኋላ ወደ ሥራ መግባቱን አብስረዋል።

አክለውም ከዚህ በፊት የነበረውን ማንዋል የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ወደ ዲጂታል ሶፍትዌር በመቀየር የተሟላ መረጃ በቀጥታ አደጋ ከደረሰበት ቦታ እስከ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሰርቨር እንደሚደርስ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኢንተለጀንስ ዋና መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ሀብታሙ ካሣ በበኩላቸው  የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ ማሰባሰቢያ ሥርዓቱ  ከደህንነት አንፃር በተደጋጋሚ ተፈትሾ የተፈለገውን አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የተረጋገጠ ነው ብለዋል።

የዲጂታል ሶፍትዌሩ መረጃ መንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂን እንዲቀርፅ፣ የመንገድ መሰረት ልማቶች በሚሰሩበት ወቅት ግብዓት እንደሚሆን፣ መረጃው ለጥናትና ምርምር ጥቅም ላይ እንደሚውል፣ ህብረተሰቡ ከትራፊክ አደጋ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በትክክል እንዲረዳ ለማስተማሪያነትም እንደሚውልም  በመግለጫው ተነስቷል።

መረጃው የፌደራል ፖሊስ ነው።

@tikvahethmagazine