TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
"ግብር ከፍዩ እንዳይጭበረበር የሚያረግ የዲጂታል አሰራር ወደ ሥራ አስገባለሁ" ገቢዎች ቢሮ

የግብር ግዴታቸውን ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብርከፋዮችን ለመቆጣጠር፣ ግብር ከፍዩ  እንዳይጭበረበር እሚያረጉ ሁለት ሲስተሞችን ሰርቶ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የቢሮው የሶፍትዌር ልማት ቡድን አስተባባሪ አቶ ደረጀ በርታ ለቲክቫህ እንደገለፁት '' ግብር ከፍዩ ትክክለኛ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኝ በማሰብ፣ቢሮው ገቢ አሰባሰቡን በማዘመን ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ለማስቻል ሁለቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በራስ አቅም ሰርተናቸዋል '' ሲሉ ገልፀዋል።

የመጀመሪያው ሲስተም አይዲ አይደንትፍኬሽን ሲሆን እሚሰራው ስራም የገቢዎች ባለሙያ ሳይሆኑ መስለው በመሄድ ግብር ከፍዩ እያጭበረበረ ያሉ ሰዎች በመቆጣጠር ግብር ከፍዩ እንዳይጭበረበር ለማረግ ነው ብለዋል።

''ይህ ሲስተም ለቢሮው የቁጥጥር ባለሙያዎች የደህንነት ባር ኮድ ያለው ይህን መታወቂያ በመስጠት ግብር ከፍዩ የመታወቂያውን ባር ኮድ በስልኩ ስካን በማረግ የባለሙያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ እንዲችል ያደርጋል" ሲሉ ነው የገለጹት።

አክለውም  "በስልካቸው ባር ኮዱን ማንበብ እማይችሉ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው 7075 ላይ በመደወል የባለሙያውን የመታወቂያ ቁጥር ለጥሪ ማዕከል ሰራተኞች በመናገር የባለሙያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይችላሉ
'' ብለዋል።

እንደ መጀመሪያ ዙር ከ200 እስከ 300 እሚሆኑ በተለይ መርካቶ አካባቢ የሚገኙ የቁጥጥር ባለሙያዎችን አሰልጥነን መታወቂያውን በመስጠት ወደስራ እናስገባቸዋለን ሲሉ አቶ ደረጀ ተናግረዋል።

በቀጣይም ይህ ሲስተም ከናሽናል አይዲ ጋር አብሮ በአንድ እንዲሆን ከኢንሳ ጋር በጋራ መስራት ተጀምሯል።

ሁለተኛው ሲስተም የእዳ ክትትል ሲስተም እንደሚባል ገልፀው '' ይህ ሲስተም ዋነኛ ስራው እዳ ኑሮባቸው እዳቸውን እሚሰውሩ ግብር ከፋዮችን ተከታትሎ ማግኘት እሚችል ሲስተም " መሆኑን አቶ ደረጀ ተናግረዋል።

ይህም "እዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች እዳ እንዳለባቸው በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እሚያሳውቅ፣ በምን ያህል ጊዜ እዳቸውን መክፈል እንዳለባቸው እንደሚገልፅ አጠቃላይ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለውን የእዳ ክትትል ሂደት እሚያሳይ ሲስተም ነው
'' ሲሉ አስረድተዋል።

ሁለቱም ሲስተሞች ከ15 ቀን በኋላ ወደስራ እንደሚገቡ ገልፀዋል። ለወደፊት ከኢንሳ ጋር በጋራ በመሆን የግብር አሰባሰብ ሂደቱን አንድ ደረጃ ከፍ ለማረግ እየሰሩ መሆኑን አቶ ደረጀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
200 ካሬ በሆነ የእርሻ መሬት ላይ የካናቢስ ዕጽ ሲያመርቱ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ጎርካ ወረዳ ላንቴ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ በእርሻ ማሳ ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ሲያመርቱ የነበሩ ግለሰቦችን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊሲ መምሪያ አስታዉቋል።

የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃና ኢንተለጀንስ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ሳጅን ሙሉቀን ጋሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት ተጠርጣሪዎቹ አቶ በላቸው በረሱ እና እልኩ ደፋር የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ እጹን ሲያመርቱ የተገኙትም በጎርካ ወረዳ ጎልቤ ቀበሌ ላንቴ ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ተጠርጣሪዎቹ፥ 10 በ 20 በሆነ የእርሻ መሬት ላይ ዕፁን ሲያመርቱ ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ አስፈላጊዉን  ክትትል በማድረግ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ማዋላቸዉንም ተናግረዋል።

ከምርመራና ክስ ሂደቱ ጎን ለጎን ከግሌሰቦቹ ጋር በዕፅ ዝዉዉሩም ሆነ የአቅርቦት ተስስር ግንኘነት ያላቸዉን ሰዎች የመከታተልና በሕብረተሰቡም ዘንድ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ሀይሌ በበኩላቸው አንድ ኩንታል ካናብስ በቲቢኤስ ሞተር ሳይክል ተጭኖ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ጠቅሰዋል።

እስከ እርሻ ማሣ በተደረገው ኦፕሬሽንም '' አራት ክምር በአጠቃላይ እስከ 120 ኪ.ግ  የሚመዘን ካናብስ አደገኛ ዕፅ በመያዝ የምርመራ ሂደት እየተጣራ '' መሆኑን አብራርተዋል።

የፌደራል ፖሊስ መረጃና ደህንነት፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንድሁም የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ መረጃና ኢንቴለጄንስ ዲቪዥን በጋራ በመቀናጀት አደንዛዥ ዕፁን ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ኮማንደር አሸናፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ይህ ህገ ወጥ ተግባር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ክሳራ የሚያስከትልና ወጣቶችን ወደ አላስፈላግ ወንጀል የሚመራ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንድያደርግ አሳስበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
🔊 #የሠራተኞችድምጽ

🟢 "ቅሬታችን በአስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ከየካቲት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ እናቆማለን"- የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች

🟢 "ለክልሉ መንግስት ቅሬታውን አቅርበናል። ነገር ግን ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠት አልቻለም " - የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰው ኃብት አስተዳደር

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥቅምት አንድ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጭማሪ እስካሁን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ተግባራዊ  ባለማድረጉ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሸን ለሁሉም ሲቪል ሰርቫንት የኑሮ ውድነት መደጎሚያ ያደረገውን ጭማሪ እስካሁን አልተጨመረንም ብለዋል።

ሰራተኞቹ  የተለያዩ ጥያቄዎችን ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ   ማቅረባቸውን የገለፁ ሲሆን ጥያቄያችን በቀጠሮ  የታጀበ የአመታት ችግር ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።

"የክልሉ መንግስት የተቋሙን ሰራተኞች ድካም እና መስዋዕትነት የተረዳው አይመስለንም " ። እኛ " ተስፋ ቆርጠናል ፣ የሚሰማን አካል የለም ፣ እየታገትን እና እየተገደልን ነው  ፣ከማህበራዊ ሂወት ተገለናል ብለዋል።

አክለውም "እንደሰው መቆጠር ናፍቆናል ፣ ችግሮቻችን በዝተዋል ፣  ችግሮችን የሚፈታልን የለም ፣ እባካችሁ የሚሰማን አካል ካለ የሁለት አመት ቅሬታችን ይሰማ " ሲሉ የነበሩበትን የችግር ግዝፈት ተናግረዋል።

አያይዘውም ሰራተኞቹ  መጋቢት 5 / 2015 ዓ.ም ይወክሉናል ያሏቸውን ተወካይዮች በመምረጥ ለክልሉ ገቢዎች ቢሮ ፣ ለበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ለብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አመራር እንዲሁም ለርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቅሬታቸውን እንዳቀረቡ ገልፀዋል።

ሰራተኞቹም በሰዓቱ ለአመራሮቹ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች በርካታ መሆናቸውን የገልፁ ሲሆን ከጥያቄዎቻቸው መካከል የገቢ ተቋሙ ሰራተኛ በልዩ ሁኔታ በጥናት ላይ የተመሰረተ ልዩ ጥቅማጥቅም ይደረግልን፣ የእርከን ጭማሪ በአደረጃጃትና በመመሪያ ደረጃ የወረደ ቢሆንም በአፈጻጸም ተግባራዊ ይደረግ እና የሰራተኛውን ጥቅም የሚመለከት ጥናት ሲጠና እስከ ታችኛዉ መዋቅር ያለ ባለሙያ ተሳታፊ ይደረግ የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በመሆኑም በሰዓቱ አመራሮቹ በምላሻቸው  ጥያቄው ተገቢነት ያለው የባለሙያውን ሮሮና ብሶት ያዘለ ስለሆነ በቀጣይ የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ ይህንን አካል የግድ ማትጋትና ማበረታታት አስፈላጊ ስለሆነ ጥያቄውን እንፈታለን ብለውን ነበር ብለዋል።

ይሁን እንጂ ቅሬታችንን ሰምቶ የፈታልን አካል የለም ያሉ ሲሆን አሁንም ለከፋ ችግር ተጋልጠን እንገኛለን ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሰራተኞቹ የክልሉን የገቢዎች ቢሮ የሰው ሀብት አስተዳደር ቅሬታችንን ፍቱልን ብለን ጠይቀን ነበር ያሉ ሲሆን ሀላፊውም በምላሻቸው " ቅሬታችሁ ከአቅማችን በላይ ነው። በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጣቸው ስንል ለክልሉ መንግስት ጥያቄ አቅርበናል እስካሁን ግን መልስ የለም " የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

አክለውም እንደተቋም በቀን እስከ 200 ሚሊየን ገቢ የሚሰበስብ ሰራተኛ አንድ ቀን ስራ ቢያቆም እንኳ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት ቀላል መሆኑን ጠቁመዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ?

ከደሴ ኮምቦልቻ የደወለልን ባለሙያ " ስራችን ከማህበረሰቡ ሂወት ነጥሎናል፣ ከነጋዴዎች አራርቆናል፣ ደመወዝ ሲያልቅብን እንኳ ከነጋዴዎች መበደር አንችልም፣ ቤት ለመከራየት ስንጠይቅ ገቢዎች ቢሮ ከሆነ የምትሰሩት አናከራይም እያሉን ነው፣ አሁን ላይ ችግሮችን መቋቋም አቅቶናል "  ሲል ተናግሯል።


ስሙን መጥቀስ ያልፈለገው የደባርቅ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኛ ደግሞ " የደረጃ እርከን እየተሰራልን አይደለም " 2012 ዓ.ም የደመወዝ ጭማሪ እንደተደረገ እስካሁን አልተጨመረንም " በስራ አጋጣሚ ሂወታቸውን የገበሩ ጓዶች  አሉ " የክልሉን መንግስት ታግሰናል" አሁን ላይ ግን ኑሮ ከብዶናል " ሲል ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም የሰራተኞቹን ቅሬታ በመቀበል ለአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የሰው ሃብት አስተዳደር ሀላፊ ለአቶ ሽመልስ አዱኛ ቅሬታቸውን ያቀረበ ሲሆን እርሳቸውም በምላሻቸው እንድህ ብለዋል።

" የሰራተኞቹ ቅሬታ ተገቢ ነው። በኛ በኩል ቅሬታውን እናውቃለን ። ለክልሉ መንግስት ቅሬታውን አቅርበናል። ነገር ግን ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ መስጠት አልቻለም "በዚህ ጉዳይ የተለየ መረጃ ልሰጥ አልችልም " ብለዋል።

ቲክቫህ የባለሙያዎችን ቅሬታ በተመለከተ የክልሉን መንግስት እና የኮሚኒኬሽን ባለሙያ እንዲሁም የክልሉን ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ በስልክ አግኝቶ ምላሻቸውን ለማካተት ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት አልተቻለም።

በመጨረሻም ሰራተኞቹ ቅሬታችን በአስቸኳይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ከየካቲት 15/2017 ዓ.ም ጀምሮ  ስራ የምናቆም መሆኑን እንገልፃለን ብለዋል።

( ቲክቫህ ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ መረጃውን የሚያደርሳችሁ ይሆናል )

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

🟢  ''ለፈረሰው ቤታችን ግብር ክፈሉ እየተባልን የቴክስት መልዕክት እየተላከልን ነው'' ቅሬታ አቅራቢዎች

🟢 '' አቅራቢያው ወደሚገኙ ወረዳ ላይ ባሉ ቢሮዎቻችን ጉዳዩን በማስረዳት ችግሩን መፍታት ይችላል '' ገቢዎች ቢሮ


የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቤታችን ፈርሶብን ወደሌላ ቦታ የተዘዋወርን ሰዎችን በፈረሰው ቤት ስም የቤት ግብር እንድንከፍል የቴክስት መልዕክት እየላከላቸው መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎች በጉዳዩ ዙሪያ እንደተናገሩት:-

"ቤቴ ካዛንችስ ነበር፣ ቤቴም ሰፈሩም ከፈረሰ 3 ወራት አልፎታል በፈረሰው ቤት ስም የቤት ግብር እንድንከፍል የቴክስት መልዕክት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እየላከልን'' ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም '' በአሁን ሰአት ከነቤተሰቤ ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ተከራይተን እየኖርን ሳለ ታድያ ላፈረሱት ቤቴ እንዴት ግብር ክፈል እንባላለን''
ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለን ጠይቀናቸው በሰጡን ምላሽ:-

እንደሚታወቀው '' የቤትና ቦታ ግብር ያለ ቅጣት እሚከፈልበት ጊዜ እስከ የካቲት 30 ድረስ''ነው።

ግብር ከፍዩ ከዚህ አንፃር እንዳይዘናጋ በየጊዜው በኤስ ኤም ኤስ በመጠቀም መረጃ የማድረስ ስራ እንሰራለን
ብለዋል

ምናልባት '' በመጀመሪያ ይኖሩበት በነበረው አካባቢ ቀደም ብሎ ተመዝግቦ ባለ ስልክ ቁጥር ግብር ክፈሉ የሚል የፅሁፍ መልዕክት ለግብር ከፍዩ ደርሶ ሊሆን'' ይችላል።

ግብር ከፋዩም '' ቤቱ ፈረሶበት በማይኖርበት ቤት ግብር ክፈል እሚል የአጭር የፁሁፍ መልዕክት ደርሶት ከሆነ አቅራቢያው ወደሚገኙ ወረዳ ላይ ባሉ ቢሮዎቻችን ጉዳዩን በማስረዳት ችግሩን መፍታት ይችላል'' ሲሉ አቶ ሰውነት አስረድተዋል።

በተለይ ከቤትና ቦታ ግብር ጋር በተያያዘ ግብር ከፍዮች በተለያየ ምክንያት እንዳይዘናጉ፣ ቅጣት፣ ወለድ እንዳያጋጥማቸው ከማሰብ አንፃር አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ግብር ከፍዩን የማስታወስ ስራ ቢሯቸው እየሰራ መሆኑን አቶ ሰውነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ጥቆማዎችን በ @tikvahmagbot ላይ ማድረስ ይችላሉ

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በባህርዳር 2 ህጻናት ተጣብቀው ቢወለዱም ህይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም።

በአማራ ክልል በባህርዳር ከተማ በጥበበ ግዮን እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካቲት 5/ 2017 ዓ.ም ተጣብቀው የተወለዱት ህፃናት በትናንትናው እለት ሂወታቸው ማለፉን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል።

የተወለዱት ሕጻናት ከደረታቸው በላይ ሁለት ሰው፤ ከደረታቸው በታች ደግሞ የአንድ ሰው አካል ይዘው እንደተወለዱ ለማወቅ ተችሏል።

ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለፁት ከሆነ እናቲቱ ከመውለዷ በፊት የእርግዝና ክትልል በዱርቤቴ ጤና ጣቢያ ስታደርግ እስከ ሰባት ወሯ  መቆቷ ተገልጿል።

በክትትሉ ወቅት ነፍሰ ጡሯ ከዚህ በፊት በእርግዝና ወቅት አይታው የማታውቀው ነገር ስለገጠማት የህክምና ባለሙያዎችን በማናገር ወደ ጥበበ ግዮን እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመምጣት ምርመራ ያካሄደች ሲሆን ፅንሱ ትክክል እንዳልሆነ ተረጋግጦ ነበር ተብሏል።

ይሁን እንጂ ፅንሱ ሰባት ወር ስለሞላው ግደታ የመወለጃቸው ቀን መድረስ ስለነበረበት በቀኑ በኦፕራሲዎን እንድትወልድ ተደርጓል ብለዋል።

በመሆኑም በአገራችን እንደዚህ አይነት አፈጣጠር በስፋት ታይቶ የማይታወቅ እና ያልተለመደ ነገር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ልጆቹ ከተወለዱ በኋላ ወላጅ እናትን ጨምሮ ቤተሰቦችም ልጆቹን ለማየት እንኳ ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ልጆችን በሂወት ለማቆየት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ እንደቀረ ምንጮቹ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉ የሚስተዋለው ግጭት የጥበበ ግዮን እስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ክፉኛ በመጎዳቱ አሁን ላይ 10 በመቶ ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም ተጣብቀው ለተወለዱት ህፃናት እጥጋቢ ወይም በቂ የህክምና አገልግሎት በሆስፒታሉ በኩል ማግኘት እንዳልቻሉ  ተጠቁሟል።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሂርና ከተማ በ2014 ዓ.ም ከደረታቸው በታች የተጣብቁ  ህፃናት መወለዳቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

° በዚህ ሳምንት በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ተችሏል።

° የመርሳ ከተማ ነዋሪዎች የዋጋ ንረቱን በተመለከተ ከሰሞኑ ቅሬታ አቅርበዋል

በአዲስ አበባ ከተማ እና በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በዚህ ሳምንት በሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ባደረግነው ምልከታ ለመረዳት ተችሏል።

በአዲስ አበባ ፣ በደሴ እና በመርሳ ከተማ እንዲሁም በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዚህ ቀደም 1300  ብር  ይሸጥ የነበረው አምስት ሊትር የምግብ ዘይት አሁን ላይ 1600 ብር እየተሸጠ ሲሆን ከዚህ በፊት ከነበረው የመሸጫ ዋጋ  ከ200 መቶ እስከ 300 ብር  ጭማሪ አሳይቷል።

እንዲሁም 1 ኪሎ ምስር ከ200 ወደ 280 ፣ እንቁላል ከብር 11 ወደ 19 ፣ 1 ሊትር ዘይት ከ285 ወደ 310 ብር  ከፍ ያለ ሲሆን ሌሎች ምርቶች ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተጋነነ የዋጋ ጭማሬ መኖሩን በምልከታችን ወቅት ለማየት ችለናል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ክልል ደሴ ከተማ  3 ሊትር ዘይት ከ 700 ወደ 900 ብር፣ 5 ሊትር ዘይት ከ 1300 ወደ 1550 ብር፣  አንድ ኪሎ ድንች ከ 40 ወደ 80 ብር በእጥፍ መጨሩን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከሰሞኑ የሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ነዋሪዎች በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ የሚታየውን የዋጋ ጭማሪ መቋቋም አልቻልንም ሲሉ ቅሬታ አቅረበዋል።

በተጨማሪም  ቅሬታ አቅራቢዎች በከተማዋ ያለውን የዋጋ ንረት በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን " እስካሁን 5 ሊትር ኡመር ዘይት 1300 ብር ነበር የምንገዛው አሁን ግን 1600 ብር ነው ፣ አንድ ሊትር ዘይት 225 ብር እስካሁን እንገዛ የነበረው አሁን ላይ 330 ብር  ደርሷል " ብለዋል።

አክለውም 50 ኪሎ ነጭ ዱቄት እስካሁን 4ሺህ 200 ብር እንገዛ ነበር ያሉት ነዋሪዎች አሁን ላይ ግን 4 ሺህ 600 ብር እየገዛን ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ያቀረቡት የመርሳ ከተማ ነዋሪዎች በየጊዜው በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ  ኑሮአቸውን ፈታኝ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ መፍትሄ የሚሰጠን አካል ካለ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ በፍጥነት እርምጃ ይወሰድልን ሲሉ ጥሪም አቅርበዋል።


የመርሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊን አቶ አራጋው ተስፉ ምን አሉ?

የመርሳ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት  ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አራጋው ተስፉ ማህበረሰቡ የቀረበው ቅሬታ አግባብነት ቢኖረውም በዚህን ያክል የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የለም ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም በከተማዋ
እስካሁን የነበረው የዋጋ ንረት አሁን ላይ በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ብለዋል።

በተጨማሪም በዚህ ወር በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የዋጋ ጭማሪ መኖሩን ያነሱት ሃላፊው በመርሳ ከተማም በአንዳንድ ምርቶች ላይ ጭማሪ መኖሩን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ይሄ የዋጋ ጭማሪ በነጋዴዎች የመጣ ሳይሆን ምርቶችን ከሚያመርቱት ድርጅቶች ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ሃላፊው ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የዋጋ ጭማሪ የሚታይባቸውን መሰረታዊ ፍጆታዎች ለምሳሌ ጤፍ፣ ማሽላ ፣ ነጭ ዱቄት፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ፖስታ፣ መኮረኒ እና የመሳሰሉትን የእለት ከእለት ፍጆታዎች  ከተለያዩ ፋብሪካዎች በማስመጣት ለማህበረሰቡ በቀጥታ በማድረስ የገበያ ሥርዓቱን አረጋግተነዋል ብለዋል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት የ1 ኪሎ ጤፍ ዋጋ ከ185 ብር በላይ ነበር፣  ከጥር ወር ጀምሮ ከ130 እስከ 140 ብር እየተሸጠ ነው። 50 ኪሎ ዱቄት ከፋብሪካው  የሚወጣው  በ4500 ብር ነው እኛ ጋር እየተሸጠ ያለው የትራንስፖርት ተጨምሮ ከ4550 እስከ 4600 ብር ነው።

ከዚህ በፊት የአንድ ኪሎ ማሽላ ዋጋ ከ 130 እስከ 150 ብር ነበር ያሉት ሃላፊው አሁን ላይ ከ60 እስከ 120 ብር እየተሸጠ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ሃላፊው በመርሳ ከተማ አሁን ላይ ከሁሉም የአማራ ክልል ከተሞች በተለየ ታላቅ የሆነ የዋጋ ቅናሽ መኖሩን አመላክተዋል።


ከሰሞኑ በሸቀጦች ላይ የታየው ጭማሪ በእናንተስ አከባቢ እንዴት ነው ?

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢 "ቤንዚን በ8 ቀን አንደዬ ብቻ ነው የምንሞላው፣ የባንክ ብድራችንን መክፈል አልቻልንም፣ ቤተሰቦቻችን ችግር ላይ ናቸው " - የደሴ ከተማ የቤንዚን ተጠቃሚ ታክሲ አሽከርካሪዎች

🟢 "ተራ አስከባሪዎችን በከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰሩ ታግደዋል" - የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ

የከተማ አስተዳደሩ የቤንዚል ተጠቃሚ ታክሲዎች በስምንት ቀን አንድ ቀን ብቻ ያውም 50 ሌትር እንድንሞላ በማድረጉ ቤተሰቦቻችን ችግር ውስጥ ናቸው ሲሉ የደሴ ከተማ  አሽከርካሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

የቤንዚን እና የነዳጅ አቅርቦት ችግር በአገር አቀፍ ደረጃ መኖሩ የሚታወቅ ነው ያሉት የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ ሃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በደሴ ከተማም የአቅርቦት ችግር መኖሩን ገልፀዋል።


ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ?

"እኛ የቤንዚል ተጠቃሚ ታክሲ አሽከርካሪዎች በደሴ ከተማ 18 ነን የከተማ አስተዳደሩ በ8 ቀን አንድ ቀን ብቻ ቤንዚን መሙላት እንድንችል በማድረጉ በወር ውስጥ ለ4 ቀን ነው መስራት የምንችለው" ብለዋል።

በተጨማሪም "ለከተማው ንግድ ቢሮ ቅሬታ ስናቀርብ 'የቤንዚል እጥረት አለ ይለናል' ነገር ግን በከተማችን በየመንገዱ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸረቸር በስፋት ይስተዋላል" ሲሉ አብራርተዋል።

"መኪኖችን የገዛነው በባንክ ብድር ነው፤ አሁን ላይ በየወሩ ለባንክ የምንከፍለውን ብድር መክፈል ባለመቻላችን ባንኮች ማስጠንቀቂያ እየሰጡን ነው ሲሉም" አክለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ፥ በተደጋጋሚ ለከተማ አስተዳደሩ፣ ለንግድ ቢሮ እና ለብልፅግና ፅህፈት ቤት ቅሬታችንን አቅርበናል፤ ምላሽ የሰጠን አካል ግን የለም ሲሉ ያሉበትን ችግር አስረድዋል።

ስሙን መግለፅ ያልፈለገው አሽከርካሪ ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስካሁን ቤንዚል በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ከማደያዎች መቅዳት እንድንችል ተደርገናል ሲል ተናግሯል።

አያይዞም ፥"እኔ መኪናውን የገዛሁት 280 ሺ ብር ከባንክ ተበድሬ ነው እሱን የምከፍለው እየሰራሁ በየወሩ ነበር አሁን ግን ያበደረኝ ባንክ ብድርህን በየወሩ መክፈል አልቻልክም ብሎ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶኛል" ሲል ገልጿል።


የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ በጉዳዩ ላይ ምን አለ ?

የደሴ ከተማ ንግድ ቢሮ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዮናስ እንዳለ በምላሻቸው ተሽከርካሪዎች ለከተማችን ማህበረሰብ የሚሰጡትን የትራንስፖርት አገልግሎት ታሳቢ በማድረግ የከተማ እና የኤርፖርት ታክሲዎች በ 8 ቀን አንድ ቀን እና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ደግሞ በየቀኑ መሙላት እንድችሉ አድርገናል ብለዋል።

ይህም የሆነበት ምክንያት አንዳንድ አሽከርካሪዎች የሚሞሉትን ቤንዚን ለትራንስፖርት አገልግሎት ከማዋል ይልቅ በህገወጥ መንገድ እየቸረቸሩ ስላስቸገሩን እንደ ከተማ አስተዳደር ጥናት በማድግ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር በተላከልን መመሪያ መሰረት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

አሽከርካሪዎች መመሪያው ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ  የተለያዩ ቅሬታዎችን እያቀረቡ ነው ያሉት ሃላፊው እኛም ቅሬታቸውን ተቀብለን ለክልሉ ንግድ ቢሮ አሳውቀናል፣ ነገር ግን ከክልሉ ቢሮ የተሰጠን አቅጣጫም ሆነ መመሪያ
#የለም ብለዋል።

አያይዘውም በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ስላቀረብን በቅርቡ መመሪያ ይሰጡናል ብለን እንጠብቃለን። ካልሆነ ግን እንደ ከተማ ክልሉን አሳውቀን የምንወስደው አሰራር ካለ እንወስዳለን " ሲሉ አስረድተዋል።

በከተማችን የቤንዚን አቅርቦት መሰረታዊ ችግር ነው ያሉት ኃላፊው በየማደያዎች የሚሰሩ ተራ አስከባሪዎች ግር ግር በመፍጠር ያለአግባብ ገንዘብ እየተቀበሉ ችግር እየፈጠሩ ነበር ብለዋል።

ስለሆነም ለህገወጥ ችርቻሮ መስፋፋት ቁልፍ ሚኒ ስለነበራቸው አሁን ላይ ተራ አስከባሪዎችን በከተማዋ ሙሉ በሙሉ እንዳይሰሩ ታግደዋል ሲሉ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከከተማ አስተዳደር እና ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመሆን በባለፈው ሳምንት በህገወጥ መንገድ ሊቸረቸር የነበረ ከ 620 ሊትር በላይ ቤንዚን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አሽከርካሪዎቹ ቤተሰብ አስተዳዳሪ በመሆናችን የሚመለከተው አካል ችግራችንን ሰምቶ በአስቸኳይ ምላሽ ይሰጠን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።


#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ከፍተኛ የመድኃኒት፣ የሳሙና እና የተለያዩ ግብአቶች እጥረት ገጥሞኛል " ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል

ከተቋቋመ 11 ዓመታት ያለፉት ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል ሥራውን የጀመረው
በ2005 ዓ.ም ነበር።

ተቋሙ አሁን ላይ ከአዲስአበባ ውጭ በተለያዩ የክልል ከተሞች በጅማ፣ ጎንደር እና በትግራይ  እየተንቀሳቀሰ ይሰራል።

ዋና ዓላማውም አቅም የሌላቸው በካንሰር በሽታ የተያዙ ህፃናትን ሙሉ ወጫቸውን እስከ አስታማሚ ቤተሰቦቻቸው በመሸፈን ማገዝ ሲሆን ላለፉት ዓመታትም ለብዙ ህጻናት እንደደረሰ ይገልጻል።

አሁን ላይ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የሆነ የመድኃኒት እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሦስት ሺሕ ገደማ የሚሆኑ የካንሰር ታካሚ ሕፃናትን ታድጓል ሲሉ ዋና ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ደግሞ ባሉት የአዲስ አበባ፤ የጅማ፤ ጎንደር እና መቐሌ ማዕከላት ለ260 ህፃናት እና ቤተሰቦች ሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በተጨማሪም በተመላላሽ እና በቋሚ የህክምና አገልግሎት ደግሞ ከ1140 በላይ ለሚሆኑ ማዕከሉ እየሰጠ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ገልፀዋል።

አያይዘውም ህፃናት ሕክምናቸውን እንዳያቋርጡ  ከማደሪያ እስከ ምግብና መድኃኒት፣ የሥነ ልቦና ትምህርት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠን ነው ሲሉ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

እስካሁን ለማዕከላቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጆቶች ድጋፋቸውን ባያቋርጡም ድጋፉ ግን በቂ ባለመሆኑ በማዕከሉ ከፍተኛ የሆነ የመድሀኒት እና የሳሙና እጥረት መከሰቱን ወ/ሮ ሳራ ጠቁመዋል።

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሳሙና፣ ዱቄት ወተት፣ ስኳር፣ ዘይት እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን በመግለጽ አሁን ላይ ግን ድጋፉ መቀዛቀዙን አክለዋል።

የካንሰር በሽታ ረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ስለሚወስድ ማዕከሉ ለታካሚዎች እና ላስታማሚዎች ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ለመቀጠል የግብአት አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ ማኅበረሰቡ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ማዕከሉን ማግኘት እና ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ

📌አዲስአበባ :- ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም
ስልክ:- 0911725455
📌ጅማ :- ወ/ሮ ብርቱካን
ስልክ:- 0935071136
📌ጎንደር:- አቶ ወንድሙ
ስልክ:- 0928503970
📌መቀሌ:- ወ/ሮ ጺዮን
ስልክ:- 0904231532

እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Tesfa Addis Parents Childhood Cancer Organization (TAPCCO) 1000036686492

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በጂንካ ከተማ አንዲት እናት 4 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች።

° ''ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም ፤እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ'' ወላጅ አባት


በጂንካ ከተማ  በትላንትናው ዕለት የካቲት 18 አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታውቆ ነበር።

እናት ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ መውለዷን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሚስጥሩ ሀምዴክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።


ህጻናቱ አሁን በምን ጤንነት ላይ ይገኛሉ ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ከአራቱ አንዷ ጨቅላ ትንሽ ኪሎዋ አነስ ስላል በአይ.ሲ ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከመሆኑ ወጭ ሌሎች ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ ናቸው ሲሉ ነግረውናል።

ዶ/ር ሚሥጢሩ አክለውም፥ እናትም በጥሩ ጤንነት ላይ ናት እንደምትገኝ እና ልጆቿን በኦፕራሲዮን በመወልዷ በትንሹ እስከ 3 ቀን በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላት እንደምትቆይ አስረድተዋል።

ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑንም የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

የልጆቹ ወላጅ አባት ምን አሉ?

የእነዚህ አራት ልጆች አባት አቶ አንጁሎ አዲስ ይባላል። ባለቤቱ 4 ልጆች ስለተገላገለችበት፤ እሱም የአራት ልጆች አባት ስለሆነበት አጋጣሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ባለቤቱ አራት ልጆች እንዳረገዘች እስክትወልድ ድረስ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና አራት ልጅ መሆኑን ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ መስማታቸውን ነው የነገረን። ይህንን ሲያቅም ደስታ እና ድንጋጤ የተቀላቀለበት ስሜት ተሰማኝ ብሏል።

ከጂንካ ራቅ ብሎ በሚገኝ በቦታ እንደሚኖሩ የገለጸው አቶ አንጁሎ፤
ወደ ጂንካ የመጡትም ለህክምና ክትትል እንደሆነ ነው የገለጸው።

በትዳራቸው እነዚህ አራት ልጆች የመጀመሪያ እንዳልዎኑ የሚናገረው አባት ከዚህ በፊት አንድ ልጅ መውለዳቸውንና እድሜውም አሁን ላይ የ4 ዓመት እንደሆነው ጠቅሷል።

"ልጆቹ ትንሽ ሰውነታቸው ቀጫጫ ከመሆኑ ውጭ ደህና ናቸው። እናታቸው ማርታ ታከለም ጡቷ ወተት እንደፈለገ አሁን ላይ አይወጣትም እንጂ እሷም ጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች" ሲል አሁን ስላሉበት ሁኔታ አስረድቶናል።

"እኔ አሁን ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም፤ እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን" ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

በተፈጥሮ በአንድ ጊዜ አራት ህጻናትን መጸነስ የሚከሰተው ከ700ሺ እርግዝናዎች በአንዱ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
ዲጅታል የትራፊክ አደጋ መረጃ መሰብሰቢያ ሥርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።

የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከፌድራል ፖሊስ ጋር ያለሙት ዲጅታል የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ መመዝገቢያ ስርዓት የሙከራ ትግበራ ተጠናቆ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊተገበር መሆኑ ተገልጿል።

ይህንን አስመልክቶ የአገልግሎቱ የተቋም ሪፎርም ሥራ አስፈፃሚና የትራፊክ መቆጣጠር ማዕከል ኃላፊ አቶ ባዩ ሙሉጌታን ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀናል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ የመረጃ ሥርዓቱ ቀልጣፍ፣ ውጤታማ እና ታማኝነት ያለው የትራፊክ አደጋ መረጃ ለመሰብሰብ ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ ነው።

ይኽም የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ተቋማት የትራፊክ አደጋ መረጃዎች ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችንም ይቀርፍል ብለዋል።

አቶ ባዩ አክለውም፥ ትራፊክ አደጋው የት ደረሰ፣ በምን ምክንያት፣ ማን አደረሰው፣ ምን ያህል ሰው ጉዳት ደረሰበትና ሌሎች መሰል የትራፊክ አደጋ መረጃዎችን በዲጂታል መልኩ ለመመዝገብ ያግዛል ብለዋል።

በዚህም ተጎጂ አካላት ከካሳ ክፍያ፣ ከህክምና ጋር በተያያዘ መረጃ ለማግኘት ያለውን  መጉላላት በመቅረፍ በቀላሉ እስከ ፍርድ ቤት ላሉ ጉዳዮች ጭምር ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም አደጋ በተደጋጋሚ እሚደርስባቸውን ቦታዎች በመለየት አደጋን ለመቀነስ፣ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ላይ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚጠቀምም ተናግረዋል።

አሁን ላይ የመረጃ ሥርዓቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ወደስራ እንድንገባ የሚያስችል እውቅና ማግኘቱን ገልጸው በሙከራ ትግበራውንም ተጠናቋል ብለዋል።

ኃላፊው የሙከራ ትግበራው በአዲስ አበባ ተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ በሚደርስባቸው 3 ክፍለ ከተሞች ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና የካ እንዲሁም በድሬዳዋ፤ ባህርዳር፤ ጅማን ጨምሮ በኦላይን እንዲሁም በኦፍላይን እንደሚሰራ መሞከሩን አስረድተዋል።

በሙከራ ትግበራውም ጥሩ ውጤት በመገኘቱ ሲስተሙን ወደ ሥራ ለማስገባት በአሁኑ ሰዓት ከታች ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና በየክልሉ እየሰጠን ነው ሲሉ አቶ ባዩ ሙሉጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ሲስተሙም ሙሉ በሙሉ ወደስራ ሲገባ በቅርቡ ለማህበረሰቡ የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራም አክለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
🔉 #የነዋሪዎችድምጽ

" የ50 ብር መንገድ ከ150 እስከ 200 እየከፈልን ነው፣ የኑሮ ውድነቱን አልቻልነውም፣ አሽከርካሪዎችን የሚቆጣጠራቸው የለም " በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ደብረዘይት ከተማ  ነዋሪዎች

" እኛ ምን እናድርግ ነጋዴዎች የሥራ ቦታቸውን ዘግተዋል፣ ከጥቁር ገበያ ደግሞ 1ሊትር እስከ 400 ብር ነው የምንገዛው "አሽከርካሪዎቹ

" ችግሩ አለ፣ ማህበረሰቡ እየተባበረን ስላልሆነ ቁጥጥሩን ትተነዋል " የወንበራ ወረዳ ትራንስፖርት ሃላፊ

የመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ደብረዘይት ከተማ እና የሰንኮራ ቀበሌ ነዋሪዎች የ9 ኪሎሜትር መንገድ ለባጃጅ ከ150 እስከ 200 ብር ለባለ ሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከ300 እስከ 400 እየከፈልን ስለሆነ ችግር ውስጥ ወድቀናል ሲሉ ለቲክቫህ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ነዋሪዎቹ የከተማዋ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ እና የትራፊክ ፖሊሶች ችግሩን ሊቀርፉልን ባለመቻላቸው ትልቅ አደጋ ውስጥ ወድቀናል ሲሉ ተናግረዋል።


ነዋሪዎቹ ያሉበትን ችግር ለቲክቫህ እንደሚከተለው ገልፀዋል፦

ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉት የሰንኮራ ቀበሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር  "አሁን ላይ ችግሮቹ ከአቅማችን በላይ ሆነዋል፣ የባጃጅ እና የባለ ሁለት እግር አሽከርካሪዎች የመንግስት ሰራተኛ አይከፍልም " ቢከፍልም መረጃ አሳልፎ ይሰጣል " በማለት የትራንስፖርት አገልግሎት እየከለከሉን ነው " ብለዋል።

አክለውም ባጃጆች ከ200 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን እቃ ከጫኑ በኋላ 7 ሰው ደግሞ ያሳፍራሉ፣ ይህ ደግሞ ለአደጋ ያጋልጣል። ትራፊክ ፖሊሶችም እየተቆጣጠሩልን አይደለም።

ሀብታም ያልሆነ ሰው በከተማዋ መኖር ከብዶታል፣ እኔ ቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ ፣ የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ ነው፣ የትራንስፖርት ብር ሳወጣ ቤተሰቦቸን ችግር ላይ ጥያቼዋለሁ ፣ የሚሰማን አካል ካለ " ኡኡ
" እያልን ነው። እባካችሁ ስሙን ሲሉ ያሉበትን ጭንቀት እና ችግር አስረድተዋል።

የባጃጅ አሽከርካሪዎች ምን አሉ?

" በየጊዜው የቤንዚን ዋጋ ይጨምራል፣ የምንገዛው ከጥቁር ገበያ 2ቱን ሊትር በ800 ብር ነው፣ መንገዱ አይመችም፣ የምናወጣው ወጪ ከምንሰራው በላይ ሆኖብናል " ሲሉ ገልፀዋል።

አያይዘውም  "በከተማችን ማደያ የለም፣ ፍቃድ አላቸው የሚባሉ ነጋዴዎችም ቤንዚን የለም ነው የሚሉን፣ ከዛም አልፎ ሥራ ቦታቸውን ዘግተዋል፣ ቤንዚን ሲመጣላቸውም 2 ሊትር በ450 ብር ነው የሚሸጡልን " ብለዋል።

በተጨማሪም " ቤንዚን በጥቁር ገበያ ሲቸበቸብ እንመለከታለን፣ አብዛኛው አሽከርካሪ ቤንዚን ሲመጣ በበርሜል ገዝቶ ያስቀምጣል፣ ብዙ መግዛት ያልቻለ ከጥቁር ገበያ ነው የሚገዛው፣ ትክክለኛ ታሪፉ 50 ብር ነው፣ ነገርግን ስለማያዋጣ ሞተረኞች አሁን ላይ ከ300 እስከ 400 ብር ሲያስከፍሉ እየተመለከትን ነው፣ እኛም እንደየሰው አቅም ከ100 እስከ 200 ብር እናስከፍላለን "  ሲሉ አስረድተዋል።


በጉዳዩ ላይ የወንበራ ወረዳ ትራንስፖርት ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጉርሜሳ ምን አሉ?

ኃላፊው ችግሩ እንዳለ እናውቃለን ሲሉ የገለጹ ሲሆን ማኅበረሰቡን ባወያዩበት ወቅትም "ተውን እየከፈልን ትራንስፖርት እናግኝ" የሚል ምላሽ ከተሰብሳቢው ማግኘታቸውን በመጥቀስ ችግሩ ለእነሱም አስቸጋሪ እንደሆነባቸው ይገልጻሉ።

"ቁጥጥር በምናደርግበት ሰዓትም 150 እና ከዚያ በላይ ከፍለው ስንጠይቃቸው 50 ብር ነው የከፈልነው እያሉ ህገወጦችን እየደበቁብን ነው፣ እኛም ስራችንን ለመስራት እየተባበሩን ስላልሆነ ቁጥጥሩን #ትተነዋል" ሲሉ ነው የተናገሩት።

ኃላፊው ቤንዚን በከተማው አለመኖሩንና ነጋዴዎች ከአማራ ክልል ከጥቁር ገበያ ነው በማምጣት እንደሚሸጡ ተናግረዋል። አክለውም በከተማችን ለሚስተዋለው የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር መባባስ አማራጭ ተሽከርካሪዎች ባለመኖራቸው ነው ብለዋል።


#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine