#NaturalDisaster
" በቀጣይ የበልግ ዝናብ ወቅት በሶማሌ ክልል ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንዲሁም በሌሎች ክልሎች በመቶ ሺ የሚገመቱ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ " OCHA
በኢትዮጵያ በሶማሌ፣ ደቡብ፣ ኦሮሚያ፣ አፋርን ጨምሮ ሌሎችም ክልሎች እስከ ግንቦት ባለው የበልግ የዝናብ ወቅት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ እና ሊፈናቀሉ እደሚችሉ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
በሪፖርቱ መሰረት፦
- በ #ሶማሌክልል፡- በአፍዴር፣ ሊባን፣ ቆራሄ፣ ኤረር፣ ዳዋ፣ ጃራራ፣ ኖጎብ እና ሸበሌ ዞኖች ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በጎርፍ በጎርፍ ሊጠቁ ይችላሉ ተብሎ የተገመተ ሲሆን ወደ 773,000 የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
- በ #ደቡብ፦ 145,000 የሚጠጉ ሰዎች በጎርፍ ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆኑ 64,000 ሰዎች ቀደም ሲል በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ ክልሎች ተፈናቅለዋል።
- በ #ኦሮሚያክልል፦ 421,000 የሚገመቱ ሰዎች በጎርፍ ይጠቃሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን በቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ምዕራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ ሀረርጌ ወደ 104,000 የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
በ #አፋርክልል፦ 83,000 የሚጠጉ ሰዎች ለጎርፍ አደጋ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ሲሆን 61,000 ሰዎች በተለያዩ ዞኖች ይፈናቀላሉ ተብሎ ይገመታል።
በ #አማራክልል ፦ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከኦሮሞ ልዩ ዞን የተፈናቀሉ 3,000 ግለሰቦችን ጨምሮ ወደ 45,000 የሚጠጉ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎም ተጠቁሟል።
በ #ትግራይክልል፦ 4,000 የሚገመቱ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ ተብሎ የሚገመት ሲሆን 1,000 ሰዎች በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ሊፈናቀሉ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከሰብአዊ የእርዳታ ድርጅቶች ጋር በመሆን ከመጋቢት እስከ ግንቦት የጎርፍ አደጋን ለመከላከል በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና የደቡብ ክልሎች የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራ የሰራ ሲሆን የገንዘብ እጥረት ግን የእርዳታ አቅርቦቱን እየገደበ መሆኑ ተገልጿል።
ፎቶ፦ ፋይል
@TikvahethMagazine

በቦሌ ክ/ከተማ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ
በዛሬው ዕለት ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የክረምት ወር መግባቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች 32 ሺሕ አባወራዎች ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ መሆናቸው ሲገለፅ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና አራዳ ክፍለ ከተሞች በተደጋጋሚ ጎርፍ የሚያጠቃቸውና በከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎች መሆናቸው በጥናት ተለይተው ታውቀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት የለየ ሲሆን ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ መልእክቱን አሰተላልፏል፡፡

በሀላባ ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ 5 ሰዎች መወሰዳቸዉን ፖሊስ ገለፀ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን ነፋስና በረዶ ቀላቅሎ በጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ ጎርፍ 5 ሰዎች ተወስደዉ ህይወታቸዉ ማለፉ የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።
በዞኑ በዌራ ዲጆ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት ከባድ ዝናብ በመጣሉ አካባቢዉ በጎርፍ መጥለቅለቁ ነዉ የተገለፀዉ።
በወረዳዉ በበንዶ ጮሎክሳ ቀበሌ (3)ሰዎች በኡደና ጮሎክስ (1) ሰው በሀለባ ቁሊቶ በገለቶና በገደባ መሀል (1) ሰው በአጠቃለይ ( 5)ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል።
የሶስት ሰዎች አስክሬን በፍለጋ ሲገኝ የሁለት ሰዎች አስክሬን ያልተገኘ በመሆኑ ፖሊስ ከአካባቢዉ መሀበረሰብ ጋር በመሆን የሟቾችን አስክሬን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሙህድን ሁሴን ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ጠቁመው፥ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።
መረጃው የዞኑ ፖሊስ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
በዚህ ዜና ላይ ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://yangx.top/tikvahethiopia/87475?single