#MOR
° ባለፉት ዘጠኛ ወራት 374.20 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል።
° 23ሺ ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ክፍያ መፈጸም ችለዋል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት 9 ወራት 374.20 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ የ9 ወራት ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልፀዋል።
መስሪያ ቤቱ 391.34 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ሲሆን፤ የዕቅዱን 95.62 በመቶ ማሳካት እንደቻለ ገልጿል።
ከነዚህ ውስጥ 23,071 ግብር ከፋዮች በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ዘዴ ክፍያ መፈጸም መቻላቸውም ተገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቅንጅት በመስራት ባለፉት 9 ወራት የቴሌ ብር ሥርዓትን ለቀረጥና ታክስ አሰባሰቡ በሥራ ላይ ማዋል በመቻሉ 7,130 ግብር ከፋዮች በቴሌ ብር በኩል ክፍያቸውን እንደፈፀሙ ተነግሯል።
በተያየዘ የኤሌክትሮኒክ የክፍያ ዘዴን ለማሳለጥ የታቀፉ የንግድ ባንኮች ቁጥር 21 እንዲደርስ የተደረገ መሆኑን ሲጠቆም የተቀሩት ባንኮችንም ወደ ሥርዓቱ ለማስገባት ሥራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
@TikvahethMagazine