TIKVAH-MAGAZINE
197K subscribers
19.9K photos
324 videos
70 files
2.52K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#የዛሬ (ግንቦት 13/2014)

👨‍⚕👩‍⚕ ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 2,898 አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢወጣም አመልካቾች በወጥነት እንዳላመለከቱ በተደረገ ክትትል ታውቋል። በአዲስ አበባ ለ161 ጠቅላላይ ሀኪሞች ቅጥር ወጥቶ ለመቀጠረ ያመለከቱት 2,300 ሲሆኑ በተቃራኒው በሶማሌ እና አፋር ክልል ለጠቅላላ ሀኪሞች የስራ ቅጥር ቢወጣም #ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ለማግኘት አልተቻለም ተብሏል።

🌽 የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

🏤 የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

📝 በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በቦርድ እንዲመራም ወስኗል። በዚህም ለባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
TIKVAH-MAGAZINE
ልጃችንን አፋልጉን ! በፎቶው የምትመለከቱት ህፃን ሳሙኤል ዮሀንስ ይባላል 3ዓመቱ ነው። ጥቅምት 6 10:00 ሰዓት አካባቢ ከአያት ባቡር ጣቢያ ከሚገኘው አፓርታማ ከተቀጠረች ገና 4ወር የሆናት የቤት ሰራተኛ "ሱቅ ማስቲካ እንግዛ" በሚል ይዛው ወጥታ በዛው ቀርተዋል። እንደመረጃ: - አያት ፀበሉ አካባቢ ወድቃ አጠገቧ የነበረው ሳሙኤል ልጇ መስሏቸው ሰዎች ሳንቲም እየሰበሰቡላት እንደነበር ተናግረዋል።…
#Update

በቤት ሰራተኛ ተሰርቆ የጠፋው የሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ህጻን ከአዲስ አበባ ክልል ውጪ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓም በለሚ ኩራ ክ ከተማ ልዩ ቦታው አያት ከሚባል አካባቢ ከቀኑ 10:30 ሰዓት በቤት ሰራተኛዋ ተሠርቆ የጠፋው ህጻን ሳሙኤል ዮሀንስ ከ11 ቀናት ብርቱ ክትትል በኋላ የተገኘ ሲሆን ከተጠርጣሪዋ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጨምሮ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ህጻን ሳሙኤል ዮሀንስ መጥፋት ሪፖርት ከደረሰው ጀምሮ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ባደረገው የሌት ተቀን አድካሚ ክትትል በደብረ ማርቆስ በአዲስ አለም ገጠራማና አስቸጋሪ ቦታዎች ፍለጋውን በማጠናከር እንዲሁም ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ በተደረጉ አድካሚ ፖሊሳዊ ስራዎች #ከፍተኛ_ገንዘብ_ካላመጣችሁ ህፃኑን አታገኙም እያለ ሲደራደር የነበረውም ግለሰብ ጭምር ሊያዝ ችሏል።

ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በተገናኘ ቀሪ የምርመራ ውጤቶች በቀጣይ ይፋ የሚደረጉ ሲሆን ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኞች ሲቀጥር ማንነትና ህጋዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

"ኢዱኬሽን ፈርስት" የተባለ ዓለማቀፍ የትምህርት ተቋም እድሜአቸው ከ 18 - 20 የሆኑ 2.1 ሚሊዮን ወጣቶችን ከ113 ሀገራት የእንጊሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በመገምገም የሀገራትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቃት ደረጃ አውጥቷል።

ተቋሙ የቋንቋውን ተናጋሪዎች ብቃት በጣም የላቀ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ በሚሉ አምስት የብቃት ደረጃዎች በመክፈል ነው ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው።

በሪፖርቱ መሰረትም ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡ የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል፦

🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇰🇪 ኬንያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇬🇭 ጋና
🇺🇬 ኡዳንዳ መሆን ችለዋል።

ከአፍሪካ በቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ  "#በጣም_የላቀ" በተባለው ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ብቃት ያላችው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካትታለች።

2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኬንያ እንዲሁም 3ኛዋ ናይጄሪያ "#ከፍተኛ" በተባለው እንዲሁም  ዩጋንዳ እና ጋና "#መካከለኛ" በተባለው የቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ተመድበዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ🇪🇹 #ዝቅተኛ የእንጊሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ውስጥ ከታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ግብፅ ጋር መመደቧ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኔዘርላንድስ፣ ሲንጋፖር፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ከአለም ከ1 እስከ 5 ያለውን የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት ደረጃ መያዝ ችለዋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በሰሜን ሸዋ ዞን 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ

በሰሜን ሸዋ ዞን ባለፉት ወራት 72 ሺህ 455 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ 8 ሺህ 73 ሰዎች በወባ በሽታ የተጠቁ መኾናቸውን የዞኑን የጤና መምሪያ ዋቢ አድርጎ አሚኮ ዘግቧል።

የወባ በሽታ በተጠቁ ሰዎች አቅራቢያ በተደረገ ተጨማሪ ምርመራ ደግሞ 159 ሕሙማንን መለየት መቻሉም ተነግሯል።

የመምሪያው ኀላፊ ጸዳለ ሰሙንጉሥ በ2016 በጀት ዓመት የወባ ስርጭት ምጣኔ ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ይጠበቅ እንደነበር ሲገልፁ ይሁን እንጂ አሁን ላይ በዞኑ የስርጭት መጠኑ 11 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በተለይ በሸዋሮቢት፣ መርሃቤቴ፣ እንሳሮ፣ ምንጃር እና መሰል ቆላማ የዞኑ አካባቢዎች የበሽታው ስርጭት #ከፍተኛ እንደሆነ ጠቁመዋል። በማኅበረሰቡ ዘንድ የወባ በሽታ የሌለ እስኪመስል ድረስ መዘናጋት መኖሩን መምሪያ ኀላፊዋ ገልፀዋል።

በጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓት እጥረት መኖር እና ወቅታዊ የሰላም መደፍረስ ችግሮችም የወባ በሽታ የመከላከል ሥራ ለመሥራት እክል መሆናቸውን ለስርጭቱ መጨመር በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

#አማራክልል #ወባ #ጤና

@tikvahethmagazine