TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ በከተማዋ ባሉ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የወባ በሽታ የተከሰተ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በለሚ ኩራ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስልክ ላፍቶ እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ግን ያለው ስርጭት ወረርሽኝ በሚያስብል ደረጃ መሆኑ ተገልጻል።

በወባ በሽታ በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተ ሞት ባይኖርም በጽኑ የታመሙ ሰዎች መኖራቸው ተጠቁሟል።

ወቅቱ ከመቼውም በላይ ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ በአዲስ አበባ እየተከሰተበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ የመከላከያ መንገዶችን በመተግበር አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሱን እዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በ2015 ዓ.ም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በአጠቃላይ 2 ሚሊየን ሰዎች ምርመራ አድርገው  648,127 ሰዎች ላይ የወባ በሽታ እንደተገኘባቸው እና ስርጭቱ በተለይም በአማራ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በክፍተኛ ሁኔታ መታየቱን መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
#AddisAbeba💧

በአዲስ አበባ ከተማ በቀን ከሚያስፈልገው አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው 725ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል።

በውሃ አቅርቦት ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎች መንስኤ የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ሲሆን፤ የከተማዋ እድገትና መስፋፋት፣ የሪል ስቴቶችና ሆቴሎች መበራከት፣ ውሃን እንደ ግብዓት የሚጠቀሙ ፋብሪካዎች መብዛት በውሃ ስርጭቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል።

በዚህ ምክንያት ውሃ በፈረቃ እንዲሆን መደረጉ የተጠቆመ ሲሆን፤ በፈረቃ ፕሮግራም ከተጀመረ ወዲህም ብዙ ጊዜ ሰዎች ቅሬታ የሚያቀርቡት የፈረቃ ውሃ ሳይደርሳቸው ሲቀር እንደሆነና ይህ በዋናነት በኤሌክትሪክ መቆራረጥና የመስመር ስብራት ሲኖር የሚያጋጥም እንደሆነ ተጠቅሷል።

ችግሩን ለማቃለል የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት በ570 ሚሊዮን ብር በመበጀት 75ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማልማት እየተሠራ እንደሆነ ተገልጿል፤ ይህንን በሚመለከት እስካሁን በተደረጉ ሥራዎች 20 የውሃ ጉድጓዶች መቆፈራቸውን እና ከዚህ ውስጥም አንዱ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥርጭት መግባቱ ተብራርቷል።

ሌሎች ሰባት የሚደርሱ ጉድጓዶች ቁፋሮ ላይ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ እስከ ሰኔ 30 ድረስ በማጠናቀቅ በውሃ እጥረት ምክንያት የሚመጣው ችግር ለመቅረፍ እንደሚሰራ ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
#AddisAbeba

በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የ82 ሰዎች ህይወት አልፏል ተባለ

በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በ2015 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 380 ድንገተኛ አደጋዎች ደርሰዋል።

ከተከሰቱት  380 አደጋዎች ውስጥ 266ቱ የእሳት ቃጠሎ ሲሆኑ 114 ያህሉ ደግሞ ከእሳት ውጪ የደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች ናቸው።

ከተከሰቱት አደጋዎች 321ዱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣በኦሮሚያ ልዩ ዞኖች 58 እንዲሁም በአማራ ክልል 1 አደጋ ተመዝግቧል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በእሳት ቃጠሎ ዘጠኝ ሰዎችና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ደግም 73 ሰዎች በአጠቃላይ 82 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ከተመዘገበዉ ሞት በተጨማሪ በእሳት 109 ፤ በድንገተኛ አደጋዎች ደግሞ 30 ሰዎች ቆስለዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች ከ707 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን 7 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከዉድመት የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንን ዋቢ አድርጎ ብስራት ራድዮ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
#AddisAbeba 🚘

- በመዲናዋ 703ሺህ የተመዘገበ ተሽከርካሪ ይገኛል፤

- በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት 211 ሰዎች ህይወት በመኪና አደጋ ሲያልፍ 991 ከባድና 749 ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

- ከሟቾች ዉስጥም አብዛኛዉ ከ20 እስከ 49 ዕድሜ ክልል ያሉት ናቸው፤

- ከሚያጋጥሙ የሞት አደጋዎች 78 በመቶ ወንድ ሲሆን 22 በመቶ የሚሆነዉ የሞት አደጋ ሴቶች ላይ የሚያጋጥም ነው፤

- በከተማዋ ከሚፈፀሙ የመኪና አደጋዎች 80 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ እግረኞች ላይ ነዉ፤

በስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የመዲናዋ መንገዶች ላይ በተደረገ ክትትል፦

- 17ሺህ 759 ተሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር፤

- 2698 የደህንነት ቀበቶ ያላደረጉ፤

- 294 ጠጥተው የሚያሽከረክሩ፤

- 4818 ስልክ እያወሩ በሚያሽከረክሩ የትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደ ተገልጿል።

ይህ የተነገረው የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት የስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማና ውይይት ባካሄደበት መድረክ ነው።

#በተጨማሪ

በ2015 ዓ.ም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጥናት በተለዩ 20 የትራፊክ መብራቶችና አደባባዮች ላይ ግብይት የፈፀሙ እና በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ምጽዋት ሲሰጡ የተገኙ አንድ ሺህ 463 አሽከርካሪዎች ላይ ቅጣት ተጥሏል ተብሏል።

@tikvahethmagazine