TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#መቄዶንያ

ልክ መቄዶንያ በር ላይ ስትደርሱ በፈገግታ የሚቀበሏችሁ አዛውንቶች በሰላምታቸው ያጠግቧችኋል ትንሽ ገባ ስትሉ ደግሞ የሰውን ፍቅር የሚፈልጉ አይን አይናችሁን የሚያዩ የአዕምሮ ህመምተኞች ትኩረታችሁን ይስቡታል።

በመቄዶንያ የሚያስደንቅ መልካምነት ገዝፎ ይታያል ሁሉም የአቅሙን ይሰራል በማእከሉ ገብተው ህይወታቸው የተቀየረ ሰዎች ጭምር በቻሉት አቅም ተቋሙን ለማገዝ በትጋት ሲንቀሳቀሱ ትመለከታላችሁ።

ሌላኛው የመቄዶንያ ገጽታ የስዕል ተሰጥኦ ያላቸው እራሳቸውን የሚያበቁበት ስፍራ፤ የቆረቡ እናቶች ብቻ ተሰብስበው የሚኖሩበት፤ ጥጥ የሚፈትሉ የተፈተለውን የሚሸምኑበት ስፍራ፤ ለተለያዩ ፕሮግራሞች ምግብ የሚሰራበት ስፍራ እና ሌሎችም በማዕከሉ ያሉ የሚጠቀሙበት ስፍራ መኖሩ ይበልጥ ማዕከሉን አስውበውታል።

ሜቄዶኒያ ያስጀመረው ባለ 12 ወለል ሕንፃ ከሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ሲሆን፤ በርና መስኮት ለመግጠም 151 ሚሊየን ብር ያስፈልግ ነበር።

ታዲያ ይህ ማዕከል ለሚያሰራው ህንጻ የሚሆን በር እና መስኮት ለማስገጠም ይረዳው ዘንድ በዶንኪ ትዩብ አማካኝነት እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ተጀምሮ ማክሰኞ ለሊት 6:35 በተጠናቀቀው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ የታሰበው እቅድ መሳካቱ ተነግሯል።

በመጨረሻም የክብር ዶክተር ቢንያም የተናገረው ንግግር የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፦

"ቀኑን ሙሉ ለሚተኛ ሰው ማጨብጨብ አይከብዳችሁም? ለእኔ ማልቀስ ነው ያለባችሁ። ትጋት ከእሸቱ መማር አለብን። ስለራሴ ድክመት ነው ማውራት ያለብኝ። እንደ መቄዶንያ እኛ ዜሮ ነን። ከዜሮ በታች ታውቃላችሁ? የሞት ፍርድ የሚገባው ሰው ማለት እኔ ነኝ።"

ይሁንና የህንጻ ስራውን ለማጠናቀቅ አሁንም ተጨማሪ ገንዘብ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የአቅሙን ያክል ጥረት እንዲያደርግና ጎዳና ላየ ያሉ አረጋውያንን እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethmagazine