#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ ከሰኔ 16ቱ የቦንብ ጥቃት እና የኢንጅነር ስመኘው ሞትን እንዲሁም የእሳቸውን ጤንነት አስመልክቶ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች የሰጧቸው ምላሾች፦
▪️የሰኔ 16ቱ ጥቃት በሚመለከት ውጤት በሚመለከት ባለሙያዎች የደረሱበትን ማስረጃ ለህዝብ ያሳውቃሉ፡፡
▪️የምርመራ ውጤቱ ገለፃ የዘገየው የተጣራ መረጃ ለህዝብ ለማቅረብ ሲባል ነው፡፡
▪️የኢንጅነር ስመኘው ሞት የሚያሳዝን ነው፤ስለአሟሟቱ ጥብቅ ክትትል ተደርጓል፡፡ ይህም ጉዳይ በምስራቁ የአገሪቱ ክፍል በተከሰተው አለመረጋጋት የምርመራ ውጤቱ ገለፃ ዘግይቷል። በቅርቡ ባሙያዎቹ የደረሱበትን ውጤት ለህዝብ ያሳውቃሉ፡፡
▪️በእኔ ጤንነት ጉዳይ የተወራው አሉባልታ ነው፣ ሙሉ #ጤነኛ ነኝ፡፡ #በተለይ ከአሜሪካ ከተመለስኩ በኃላ ሙሉ ጤነኛ ሆኘ ስራ ላይ ነው።
©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተነሳበት ተቃውሞ ምንድነው ?
ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ስራ ሊጀምር በዝግጅት ላይ በሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል።
የዘመቻው ምክንያት ቅጥር የሚፈፀመው እና ውክልና የሚሰጠው አግላይ በሆነ መንገድ ነው በሚል ነው።
#በተለይ ደግሞ በድርጅቱ የሰራተኞች አቀጣጠር እና ውክልና አሰጣጥ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ ተወላጆች ድርጅቱ ከአድሎ እንዲታቀብ ፣ ኢትዮጵያን እንዲመስል፣ ሁሉንም እንዲያቅፍ ካልሆነ በኦሮሚያ ክልል ያለው ህዝብ የድርጅቱ ደንበኛ እንዳይሆንና አገልግሎቱን እንዳይጠቀም ዘመቻ እንደሚያካሂዱ አስጠንቅቀዋል።
ከተነሱ ቅሬታዎችና ፍትሃዊ የሆነ አሰራር ተጓድሏል ከተባሉ ጉዳዮች መካከል የሲም ካርድና ሞባይል ካርድ አከፋፋዮች ላይ አድሎ አለ፣ የህትመት የማስታወቂያ የፕሮዳክሸን ስራዎች በአድሎ ተሰጥተዋል፤ እየተፈፀመ ያለው ቅጥር በቂ ልምድ ያላቸውን የኦሮሚያ ተወላጆችን ባገለለ መልኩ ነው፤ በድርጅቱ በየእርከኑ የተመደቡ ኃላፊዎች በአድሎ የተመደቡ ናቸው፤ ድርጅቱ ኦሮሚያ ክልል ላይ አፋን ኦሮሞ ላለመጠቀም ሲያንገራግር ነበር የሚሉ ናቸው።
ጉዳዩን በተመለከተ በቀጥታ ከድርጅቱ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም ፤ ነገር ግን ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ ዘመቻውን እየመሩ ናቸው ካላቸው ተወካዮች ጋር መነጋገሩን አሳውቋል።
ሳፋሪኮም በውይይቱ የተወካዮቹን ስጋት በጥሞና ማዳመጡን ገልጿል። " ሁሉንም ኢትዮጵያ ሚወክል ድርጅት ያለአንዳች ወገንተኝነትና አድሎ እየገነባን እንደሆንን አረጋግጠንላቸዋል " ብሏል።
" በማንኛውም ጊዜ ለውይይት ዝግጁ ነን " ያለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፤ " ሁሉንም ቋንቋዎች እና ባህሎች ባከበረ መንገድ ሁሉንም ኢትዮጵያ ለማገልገል ቁርጠኞች ነን " ሲል አሳውቋል።
@tikvahethiopia