TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በሀገራችን አንዳንድ መልካም የስራ ስነምግባር የጎደላቸው ፣ ከአሸከርካሪዎች ጉቦ ካልተቀበሉ ቀኑ መሽቶ የማይነጋ የሚመስላቸው ፣ አንዳንዴም ሆን ብለው ምክንያት ፈልገው የቅጣት ወረቀት ለመፃፍ በኃላም #ጉቦ ለመቀበል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የሌላቸው ፣ ፀሀዩ በረታብኝ ፥ ዝናቡም አካፍብኝ ብለው የሚጠለሉ የትራፊክ የፖሊስ አባላት እንዳሉት ሁሉ ፦
- ለስራቸው ታማኝ
- ህግን አክባሪ
- ቅን አገልጋይ
- ፀሀይ ፣ ዝናብ ሳይሉ ህዝብን አክብረው የሚሰሩ በርካታ የትራፊክ ፖሊስ አባላት አሉ።

ለእነዚህ አይነት ህዝብን አክብረው ምንም አይነት ሁኔታ ሳይገድባቸው ለሚሰሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላት #ምስጋና ይገባል።

በሀገራችን ካሉ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሰላም ተምሳሌቷ #ድሬዳዋ ❤️ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶቿ በተለያየ ጊዜ በመልካም ስነምግባራቸው ስማቸው ተደጋግሞ ይነሳል።

ትላንትና በከተማው ከባድ ዘናብ ዘንቦ በነበረበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል በዝናብ ውስጥ ሆኖ ስራውን ሲያከናውን የሚያሳይ የተቀረጹ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲያጋሩት ውለዋል።

@tikvahethiopia
#ጋና #ፀረግብረሰዶም

ባለፈው ወር መጨረሻ #የጋና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ጠንካራ ይዘት ያለው " የፀረ-ግብረሰዶም " ረቂቅ ህግ አፅድቋል።

ረቂቅ ህጉ በክርስቲያኑ ፣ በሙስሊሙ እና በጋና ባሕላዊ መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ያለው ነው።

ወደ ተግባር እንዲገባና ህግ ሆኖ እንዲወጣ ግን የፕሬዜዳንት ናና አኩፎ-አዶን ፊርማ እየጠበቀ ነው።

በጋና አሁንም ቢሆን ግብረሰዶማዊነት እስከ 3 ዓመት ድረስ ወደ እስር ቤት ያስወረውራል።

በአዲሱ ረቂቅ ህግ ላይ ቅጣቱ ጠበቅ እንዲል የተደረገ ሲሆን ፦
- በማንኛውም መንገድ ግብረሰዶማውያንና እንቅስቃሴያቸውን ማስተዋወቅ
- የግብረሰዶም ስብስብ መፍጠር
- ግብረሰዶማውያንን ስፖንሰር ማድረግ
- ግብረሰዶማውያንን እና የሚያደርጉትን ማንኛውም እንቅስቃሴ በምንም መልኩ መደገፍ እስከ አምስት (5) ዓመት ወደ እስር ቤት ያስወረውራል።

ምዕራባውያኑና በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ ተቋሞቻቸው የጋና ፓርላማ ያፀደቀውን ረቂቅ ህግ ክፉኛ ነው የተቃወሙት።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እስካሁን ያልፈረሙበት ሲሆን ረቂቅ ህጉን የሚደግፈው ህዝብ " ምነው ዘገዩ ? " የሚሉ ቅሬታዎች እያነሳ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋና መገናኛ ብዙሃን ላይ ተመልክቷል።

የሀገሬው ሰው ፕሬዜዳንቱ #እንዲፈርሙ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ እርዳታ ሰጪ ምዕራባውን ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዳይፈርሙበት እያሳሰቡ ናቸው።

ጋና ጠንካራ ነው የተባለውን የፀረ-ግብረሰዶም ህግን ወደ ተግባር ምታስገባው ከሆነ በሚቀጥሉት አምስት እና ስድስት ዓመታት ውስጥ ከዓለም ባንክ የምታገኘውን 3.8 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ልታጣ ትችላለች ተብሏል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ
አዲሱን የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ደንበኞች እንዴት ወደ አዋጭ አካውንት ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ?
ሊንኩን በመጠቀም መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ!

ለአንድሮይድ ስልኮች https://play.google.com/store/apps/details?id=com.boa.boaMobileBanking&hl=en&gl=US

ለአፕል ስልኮች  https://apps.apple.com/us/app/boamobile/id6463218765

ለሁዋዌ ስልኮች https://appgallery.huawei.com/app/C110106115
#BankofAbyssina #mobilebanking #boamobile #bankinginethiopia #banksinethiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
የ5 ዓመቷን ህፃን የደፈረው የ17 ዓመት ወጣት 6 ወር ተፈረደበት ይለናል የወምበራ ኮሚኒኬሽን። የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል የተከሰሰው የ17 ዓመቱ ወጣት #በ6ወር እስራት መቀጣቱ ተሰምቷል። የ10ኛ ክፍል ተማሪና የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ግለሰብ በአስገድዶ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ታህሳስ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ በደብረ―ዘይት ከተማ…
“ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ? ”

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ አካላት ላይ የሚወሰነው ፍርድ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ወንጀል ፈፃሚዎች ከስህተታቸው ተምረው እንዲታረሙና ድርጊቱ እንዲቆም በማስቻል ፋንታ “ አይዟችሁ በርቱ ” የሚል ይመስላል ፣ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ ? የሚሉ ትችት እና ጥያቄዎችን በተለይም ከሰሞኑን በበርካቶች ዘንድ ሲሰነዘር ተስተውለዋል።

በርካቶችን ካስቆጡ የወንጀል ቅጣቶች መካከል አንዱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ዓርብ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ/ም አንድ የ17 ዓመት ተማሪ ፣ ምንም ነፍስ ያላወቀች የ5 ዓመቷን ህፃን አስገድዶ ደፈሩን ተከትሎ የወረዳው ፍ/ቤት መጋቢት 9/ 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በወንጀል ፈጻሚው ላይ የ6 ወራት እስራት የፍርድ ቅጣት ማስተላለፉ ተጠቃሽ ነው።

እንዲሁም፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ኬሌ 01 ቀበሌ መጋቢት 2015 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ተማሪ ፣ የ13 ዓመት ታዳጊ ፣ የአብራካቸው ክፋይ የሆነች #ልጃቸውን አስገድደው ደፈሩ የተባሉትን የ42 ዓመት አባት ላይ የዞኑ ፍርድ ቤት የ10 ዓመታት የእስራት ቅጣት መወሰኑም ሌላኛው ትችት ያጫረ የፍርድ ውሳኔ መሆኑ አይዘነጋም።

ሌሎች ተያያዥ በርካታ ወንጀሎች መኖራቸው እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ አብነት ከላይ በተጠቀሱት የአስገድዶ መድፈር ረገድ በተላለፉ የወንጀል ቅጣት ውሳኔዎች እና የቤንሻንጉል ወንበራውን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ወንጀል የተሰጠውን ቅጣት በተመለከተ ፦
➡️ ምን አይነት ቀልድ ነው ?
➡️ ይሄ ውሳኔ አሁን ቅጣት ነው ?
➡️ እስከ መቼ ነው በሰው ቁስል የሚቀለደው ? በሚል ብዙኅን ጥያቄዎች አንስተዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን #ልጃቸውን ደፈሩ የተባሉትን አባት የቅርብ ጊዜ የፍርድ ቤት ቤት ቅጣት ውሳኔ በተመለከተ፣ “ 10 ዓመት እስራት ብቻ ?፣ ውሳኔው ድርጊቱ እንዲበረታታ እንዲያደርግ ታስቦ የተሰጠ ነው እንዴ ? ” የሚሉ ጥያቄዎችን አጭሯል ተስተውሏል።

በተያያዘ ከዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአምስት ዓመታት በታች የሆኑ ወንዶችን ሁሉ የደፈሩ ወንጀለኞች ከአምስት ዓመታት በታች በሆኑ የእስራት፣ ከ2,000 ብር ያልበለጡ ቅጣቶች ሲወሰኑባቸው መስተዋሉ በርካቶችን “ ፍትህ የት ናት ? ” ያስባሉ ጉዳዮች ናቸው። 

በወቅቱ አስተያዬታቸውን የሰጡ ምሁራንም፣ ወንድ ልጅ ላይ “ እንዲህ አይነት ወንጀል መፈጸም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሳይሆን፣  የግብረሰዶም ድርጊት ተፈጸመ ነው መባል ያለበት ” ሲሉ ተስተውለው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከሰሞኑ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ የአምስት ዓመቷን ህፃን አስገድዶ ደፈረ በተባለው የ17 ዓመት ወጣት የ6 ወራት የእስራት ቅጣት መወሰኑ፣ በአጠቃላይ በዘርፉ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ለሚሰጠውን “ የተለሳለሰ ቅጣት ” በተመለከተ ሕጉን በድጋሚ ማጤን እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጽያ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ? ” የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በፈጸሙ አካላት ላይ የሚወሰነው ፍርድ ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ወንጀል ፈፃሚዎች ከስህተታቸው ተምረው እንዲታረሙና ድርጊቱ እንዲቆም በማስቻል ፋንታ “ አይዟችሁ በርቱ ” የሚል ይመስላል ፣ ሕጉ ለምን ተለሳለሰ ? የሚሉ ትችት እና ጥያቄዎችን በተለይም ከሰሞኑን በበርካቶች ዘንድ ሲሰነዘር ተስተውለዋል። በርካቶችን ካስቆጡ የወንጀል ቅጣቶች መካከል አንዱ…
#ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኀበር (ኢሕባማ) በፆታዊ ጥቃት ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲወሰን የሚስተዋለውን ፍፁም ያልተመጣጠነ ቅጣት በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማኅበሩ የቅጣት ዋነኛ ዓላማ ወንጀል ፈጻሚዎች ተጸጽተው እንዲማሩ ፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጊት ላለመፈጸም ትምህርት እንዲወስዱ ለማድረግ ቢሆንም አሁን እየሆነ ያለው ግን ከዚህ በተቃራኒው እንደሆነ ገልጿል።

የማኀበሩ ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ቤተልሄም ደጉ ምን አሉ ?

“ አሁን አሁን የምንሰማቸው ውሳኔዎች ይበልጥ እንዲያውም የልብ ልብ የሚሰጡና ‘ምንድነው ይህን ያክል ጊዜ ነው ብታሰር’ የሚሉ አይነት አስተሳሰቦችን በሰዎች ላይ Create የሚያደርጉ ናቸው ” ብለዋል።

ሰሞንኛውን የወምበራ ወረዳ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ6 ወራት የቅጣት ውሳኔ በተመለከተ በሰጡት ቃል ፦

“ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ዝቅተኛው ተብሎ የሚቀመጠው እንኳ 5 ዓመታት ነው።

በልዩ ሁኔታዎች ተብሎ የተቀመጠው እንኳ፣ የወንጀለኛ መቅጫ 620ንና ከዚያ ቀጥሎ ያሉትን ብናይ ከ3 ዓመታት በታች የሚያስወስን የወንጀል ጥቃት የለም።

ከ6 ወራት እስከ 4 ዓመታት የሚወሰኑ ቅጣቶች አሉ። ለችግሩ ዋነኛ ክፍተቱ ምን ላይ እንደሆነ የሚያመላክት ጥናት ግን ገና የለም።

የማስረጃ ሕግ አለመኖር፣ ነገር ግን የማስረዳት ሸክም ጋር ተያይዞ ያሉት ከፍተኛ የሆኑ የማስረጃ ስታንዳሮዶች ራሱን በቻለ መልኩ ፆታን መሠረት ላደረጉ ጥቃቶች Contribute እያደርጉ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

ክፍተት ያለው የቱ ጋር ነው ? ከዳኞች መረዳትና ግንዛቤ ነው ?፣ ከሕግ ማዕቀፎች ነው ? የሚለውን ለመለየት ጥናት ያስፈልጋል።

ቅጣት በሚወሰንበት ጊዜ ዳኞች ሚያስቀምጡት የቅጣት አወሳሰን መመሪያዎችና ደንቦች አሉ። እዚህን መመሪያዎችና ደንቦችን በደንብ መቃኘት ያስፈልጋል " ብለዋል።

... የ3 ዓመቷን ህፃን ላይ በፈፀመው ወንጀል ተላለፈ የተባለው የ6 ወራት የእስራት ቅጣትን በተመለከተ በመነሻው ምናልባት ጉድለት ሲኖር ፣ የማስረዳት ሸክምን ዐቃቢ ሕግ በአግባቡ ሳይወጣ ሲቀር ዝቅተኛ ቅጣት ሊወሰን ይችላል። ግን ጨቅላ ህፃን የደፈረን ሰው 6 ወራት ሊያስወስን የሚችል የህግ መነሻና መንደርደሪያ የለም።

ቅጣቱ የ3፣ 4 ዓመታት እንኳ ቢሆን ዝቅተኛው መንደርደሪያ ላይ አረፈ ብለን፣ በቂ አይደለም ልንል እንችላለን። ይሄ 6 ወራት የሚለው ግን ቅጣት ነው ወይ ? ራሱ፣ የሚለውን ጥያቄ አብሮ ያስነሳል። ስለዚህ የሕግ ማዕቀፋችን እንደገና ሊታይ ይገባል ” ብለዋል።

መፍትሄውን ምንድነው ?

“ ሁላችንም በዘርፉ ያለን ተቋማት ሁሉ የሕግ ማዕቀፎችን Re evaluate ማድረግና ክፍተቶች ካሉ ደግሞ መንግሥት እንዲያስተካክል የAdvocacy ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል ” ብለዋል።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድሬዳዋ❤️

የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው።

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ በከባድ ዝናብ ውስጥ ሆነው ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶች የማበረታቻ የብር ሽልማት ተበረከተላቸው።

ሽልማቱን ያበረከቱት የትራፊክ ፖሊስ አባላቱን ተግባር በማህበራዊ ሚድያ የተመለከቱ የድሬዳዋ ወጣቶች ናቸው።

የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ የትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ ሲያከናውኑት የነበረው ስራ ለሌሎችም ትምህርት ሆኖ ያለፈ ነው። #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
ዒድ ኤክስፖ ትኬትና ሸመታዎን በቴሌብር ያድርጉ!

በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ተዘጋጀው ዒድ ኤክስፖ ጎራ ካሉ የመግቢያ ትኬቱን በቴሌብር http://onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ሲቆርጡና ሲገበያዩ እስከ ብር 2500 ላለው የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት 10% ተመላሽ ያገኛሉ።
#ደመወዝ

" ላለፉት ወራት በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ስንፈተን ቆይተናል " ያሉ የዎላይታ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች " ስራችንን በአግባቡ ለመስራት እንችል ዘንድ መንግሥት በአግባቡ ደሞዝ ሊከፍለን ይገባል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸው ከሰጡት የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ በተለይም #መምህራን እና #የህክምና_ባለሙያዎች ይገኙበታል።

" ጉዳዩን በተዋረድ ለሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ለወረዳ አመራሮች ካሳወቅን ቆየን " የሚሉት እነዚህ ሰራተኞች " ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም ወደ ክልሉ መንግስት መቀመጫ ወደሆነችዉ ወላይታ ሶዶ ከተማ ብናቀናም ሰሚ አላገኘንም " ብለዋል።

በተለይ ይህ የደሞዝ አለመክፈል እና መቆራረጥ ችግር የተከሰተባቸው በዎላይታ ዞን ስር የሚገኙት የኪንዶ ኮይሻ ፣ የሆብቻ ፣ አባላ ፣ አባያ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ፑላሳ ፣ ዳሞት ወይዴ ፣ ኪንዶ ዲዳዬ እና አካባቢዉ ወረዳና ቀበሊያት እንደሆኑ ተገልጿል።

በሆብቻ ወረዳ የሚገኘው የሆብቻ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስራ ካቆመ መሰነባበቱንና ተማሪዎች ቤታቸዉ እየዋሉ መሆኑን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ መምህራን " መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ወስዶ ወደስራችን ይመልሰን " ብለዋል።

ከዚህዉ ጋር ተያይዞ የከልሉን መንግስት ሀሳብ በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አዜብ ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸዉ በመግለጽ ዝርዝር ሀሳብ ከመሰንዘር ተቆጥበዋል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተልን እናሳውቃችኃለን።

መረጃዉን አዘጋጅቶ የላከዉ የሀዋሳው ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት ያላቸዉን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ብሏል።

የወጣቱ ህይዎት ይቀጠፍ ዘንድ ምክኒያት የሆኑ ጉዳዮችን ለማወቅ የስልክ ልውውጦችን ከመመርመር በተጨማሪ በዙሪያው የነበሩ አካላትንም በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ገልጿል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እነማን ተያዙ ? የምርመራዉ አካሄድስ ምን ይመስላል ? ሲል ለአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የለሆኑት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ጥያቄ አቅርቧል።

" የተጫዋቹ መሞት በተሰማበት ወቅት አጠራጣሪ ጉዳዮች ስለነበሩ ፖሊስ የምርመራ እንቅስቃሴ ጀምሯል " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም " በዚህ ወቅት ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " ብለዋል።

በሶሻል ሚዲያ እየተዘዋወረ ያለዉን የእናቱ እና ባለቤቱ መያዝ በተመለከተ ላነሳንላቸዉ ጥያቄ " አሁን ላይ ከእህት እና ወንድሙ ዉጭ የተያዘ አካል የለም በማለት ወደፊት ግን ከተያዙት የሚለቀቅ ካልተያዙት ደግሞ የሚያዝ ሊኖር ይችላል " ብለዋል።

" አሁን ላይ ምርመራዉን በፍጥነትና በጥንቃቄ እያካሄድን ነው " ያሉት ኢንስፔክተር አብርሀም ሙሄ ውጤቱን ለመላ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማድረስ ማሰባቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia