TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ጋና

" የእኔን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎች ደመወዝ በ30 በመቶ ቀንሷል " - የጋና ፕሬዜዳንት

የጋናው ፕሬዝደንት ናና አዶ ዳንኩዋ አኩፎ-አዶ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ የራሳቸውን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎቻቸው ደመወዝ በ30 % እንዲቀንስ መደረጉን አስታውቀዋል።

ይህን ያስታወቁት ትላንትና የዒድ አል-አድሃ በዓል ሲከበር ባሰሙት ንግግር ነው።

የ30% ቅነሳው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ የመንግስት ኤጀንሲዎችን እና መምሪያዎችን ወጪ ይነካልም ተብሏል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መንግስት እያሽቆለቆለ ያለውን ኢኮኖሚ ለመታደግ በሚያደርገው ጥረት ጋናውያን መስዋዕትነት እንዲከፍሉ ተማጽነዋል።

" አሁን ያለውን ችግር ለመቅረፍ ሁላችንም መስዋዕትነት መክፈል አለብን " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ መምሪያዎች እና ኤጀንሲዎች ወጪ በ30 በመቶ ቀንሷል። የእኔን ጨምሮ የሁሉም ተሿሚዎች ደመወዝም በ30 በመቶ ቀንሷል " ብለዋል።

የነዳጅ ኩፖን ምደባ በ50 % መቀነሱን እንዲሁም ሌሎች ወጪዎች መታገዳቸውን ገልፀዋል።

ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ጋናውያን እንዲታገሷቸው አሳስበዋል።

ፕሬዝዳንት ናና አዶ አኩፎ አዶ እኤአ ሰኔ 1/2022 የገንዘብ ሚኒስትሩ ኬን ኦፎሪ-አታ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ጋር ይፋዊ ግንኙነቶችን እንዲጀምሩ አዘው ነበር።

የIMF ድጋፍ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ እያጋጠሙ ያሉ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ነው ተብሏል።

Video Credit : Citi TV, Ghana

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #Eurobond ኢትዮጵያ የቦንድ ብድር ወለድ በወቅቱ ያልከፈለችው ለምንድነው ? ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮ ቦንድ ሰኞ ዕለት መክፈል የነበረባትን ወለድ እስካሁን አልከፈለችም። የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ ለሽያጭ የቀረበው ከ9 ዓመት በፊት በ2007 ዓ.ም ነበር። ኢትዮጵያ ይህንን ቦንድ ሸጣ ከገዢዎች አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ያገኘች ሲሆን ብድሩ የሚመለሰው…
#Update

ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ለሸጠችው የአንድ ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ወለድን በቀነ ገደቡ መክፈል ባለመቻሏ ዕዳቸውን መክፈል ካልቻሉ አገራት ተርታ እንደተመደበች ሮይተርስ የዜና ወኪል አስነብቧል።

ኢትዮጵያ ትናንት ሰኞ ታኅሳስ 15/ 2016 ዓ.ም. መክፈል የነበረባትን የ33 ሚሊዮን ዶላር ባለመክፈሏ ዕዳዋን መክፈል ያልቻለች ሶስተኛዋ የአፍሪካ አገር መሆና መመዝገቧ ተገልጿል።

ከ10 ዓመት በፊት በታኅሣሥ 2007 ዓ.ም. የ1 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ሽያጭ አድርጋ ላገኘችው ብድር የወለድ መክፈያ ጊዜያው ከሁለት ሳምንት በፊት ታኅሣሥ 1/2016 ዓ.ም. ነበር።

ከመክፈያ ጊዜው ቀነ ገደብ በኋላ የነበረው የ14 ቀናት የእፎይታ ጊዜም እንዲሁ ተጠናቀቋል።

ከዚህ ቀደም መንግስት ወለዱን እንደማይከፍል ማስታወቁ ይታወሳል።

የገንዘብ ሚኒስቴር የማሻሻያ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት ሂንዣት ሻሚልም ፤ ክፍያው አለመፈጸሙን እና የሚከፈል አለመሆኑንም ማረጋገጣቸውን ብሉምበርግ ዛሬ ማለዳ ዘግቧል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ ዕዳቸውን መክፈል የማይችሉ (Sovereign default ውስጥ ከገቡት) ሁለት የአፍሪካ አገራት ጎራ ተሰልፋለች። ዕዳቸውን መክፈል የማይችሉ የተባሉት ሁለት የአፍሪካ አገራት #ጋና እና #ዛምቢያ ናቸው።

ገንዘብ ሚኒስቴር ከጥቂት ቀናት በፊት በዚህ ጉዳይ በሰጠው መግለጫ፤ ኢትዮጵያ ዕዳዋን የማትከፍለው፤ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ እጥረት ሳለልባት ሳይሆን ሁሉንም አበዳሪዎች " በእኩል ለማስተናገድ " በሚል መሆኑን ተናግሯል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋም ከቀናት በፊት ከፋና ቴሌቭዢን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ይህንን የክፍያ ጉዳይ አንስተው ነበር።

ዶ/ር ፍፁም ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ወለድንያልከፈለችው የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ችግር ስላለባት አይደለም።

- በዓመት በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ከውጭ ለምናስገባው ዕቃ የምንከፍል ሀገር ነን ስለዚህ 30 ሚሊዮን ዶላር [ገደማ] ገንዘብ ተቸግረን አይደለም ያልከፈልነው ኢትዮጵያ እንዲያውም ብድሯን በጣም በመክፈል የምትታወቅ አገር ናት በችግር ውስጥም ቢሆን።

- ወለዱ ያልተከፈለው ሁሉም አበዳሪ እና ተበዳሪ ተመሳሳይ አይነት አያያዝ ነው ሊያዝ የሚገባው በሚል ምክንያት ነው።

መረጃውን ቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ሮይተርስ እና ብሉምበርግን ዋቢ በማድረግ ነው ያስነበበው።

@tikvahethiopia
#ጋና

የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች እና በዚህ ዙሪያ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሚከሰሱ ሰዎች ላይ ጠንከር ባለ እስር የሚቀጣ ሕግ አጽድቋል።

አዲሱ ሕግ ምን ይላል ?

በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ 3 ዓመት የሚደርስ እስር ፤

ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ 5 ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል።

በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በፊርማቸው ሲያጸድቁት ነው።

ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አብዛኛው የአገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉት ከሆነ ሕጉን እንደሚያጸድቁት ተናግረው ነበር።

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በጋና ውስጥ ቀደም ብሎም ሕገወጥ ሆኖ በ3 ዓመት እስር የሚያስቀጣ ነው።

አዲሱ የጋና ሕግ በተለይ ህጻናት ላይ አተኩሮ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ለማስተዋወቅ በሚደረግ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የተሳተፈ ማንኛውም ሰው አስከ 10 ዓመት የሚደርስ እስር የሚቀጣ ነው።

ባለሥልጣናት “ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ” ለማስቻል ሕብረተሰቡ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ማኅበራት አባላትን እንዲጠቁሙ ሕጉ ያበረታታል።

ይህ ሕግ እንዲረቅ ምክንያት የሆነው ከ3 ዓመት በፊት በጋና ዋና ከተማ አክራ የመጀመሪያው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የማኅበረሰብ ማዕከል መከፈቱን ተከትሎ እንደሆነ የፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል።

ይህንንም ተከትሎ ብዙኃኑ ክርስቲያን በሆነባት ጋና የሃይማኖት እና ባህላዊ መሪዎች በፈጠሩት ግፊት ሕዝባዊ ተቃውሞ በመቀስቀሱ ፖሊስ ማዕከሉ እንዲዘጋ አድርጓል።

በወቅቱ የጋና የክርስትና እምነት ማኅበራት ባወጡት የጋራ መግለጫ የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት “ ለአገሪቱ ባህል እና የቤተሰብ ዕሴት እንግዳ በመሆኑ የጋና ዜጎች ሊቀበሉት አይችሉም ” ሲሉ ተቀውመዋል።

የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የጋና ፓርላማ ያጸደቀውን ሕግ በመቃወም አስተያየት እየሰጡ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ጋና #ፀረግብረሰዶም

ባለፈው ወር መጨረሻ #የጋና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ጠንካራ ይዘት ያለው " የፀረ-ግብረሰዶም " ረቂቅ ህግ አፅድቋል።

ረቂቅ ህጉ በክርስቲያኑ ፣ በሙስሊሙ እና በጋና ባሕላዊ መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድጋፍ ያለው ነው።

ወደ ተግባር እንዲገባና ህግ ሆኖ እንዲወጣ ግን የፕሬዜዳንት ናና አኩፎ-አዶን ፊርማ እየጠበቀ ነው።

በጋና አሁንም ቢሆን ግብረሰዶማዊነት እስከ 3 ዓመት ድረስ ወደ እስር ቤት ያስወረውራል።

በአዲሱ ረቂቅ ህግ ላይ ቅጣቱ ጠበቅ እንዲል የተደረገ ሲሆን ፦
- በማንኛውም መንገድ ግብረሰዶማውያንና እንቅስቃሴያቸውን ማስተዋወቅ
- የግብረሰዶም ስብስብ መፍጠር
- ግብረሰዶማውያንን ስፖንሰር ማድረግ
- ግብረሰዶማውያንን እና የሚያደርጉትን ማንኛውም እንቅስቃሴ በምንም መልኩ መደገፍ እስከ አምስት (5) ዓመት ወደ እስር ቤት ያስወረውራል።

ምዕራባውያኑና በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ ተቋሞቻቸው የጋና ፓርላማ ያፀደቀውን ረቂቅ ህግ ክፉኛ ነው የተቃወሙት።

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት እስካሁን ያልፈረሙበት ሲሆን ረቂቅ ህጉን የሚደግፈው ህዝብ " ምነው ዘገዩ ? " የሚሉ ቅሬታዎች እያነሳ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋና መገናኛ ብዙሃን ላይ ተመልክቷል።

የሀገሬው ሰው ፕሬዜዳንቱ #እንዲፈርሙ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ እርዳታ ሰጪ ምዕራባውን ፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እንዳይፈርሙበት እያሳሰቡ ናቸው።

ጋና ጠንካራ ነው የተባለውን የፀረ-ግብረሰዶም ህግን ወደ ተግባር ምታስገባው ከሆነ በሚቀጥሉት አምስት እና ስድስት ዓመታት ውስጥ ከዓለም ባንክ የምታገኘውን 3.8 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ልታጣ ትችላለች ተብሏል።

@tikvahethiopia