TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ከማእድን ዘርፍ የሚገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከዓመት ወደ ዓመት እየቀነሰ መምጣቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታወቀ። የማእድን ዘርፍ በ2004 በጀት አመት 654 ሚሊዮን ዶላር በማስገኘት ከቡና ቀጠሎ በሁለተኛ ደረጃ የሃገሪቱ ከፍተኛ የውጥ ምንዛሪ ምንጭ ነበር። በ2002 እና በ2005 የበጀት አመታት ከአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ውስጥ የማእድን ዘርፉ በተለይም የወርቅ ማእድን የ19 በመቶ ድርሻ ነበረው። ይሁንና በ2010 በጀት አመት በ3•6 በመቶ ዝቅ ብሏል። በ2011 ም በ3•3በመቶ ዝቅ ብሎ 44 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ገልጿል። የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት፣የተለያዩ ፖሊሲዎችና የህግ ማዕቀፎች በተሟላ መልኩ አለመኖር፣ በቂ አቅም ያለው የሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ አለመኖር እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ መሆን ለዘርፉ ውጤታማ አለመሆን ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OSA_2019

ታዋቂው ባለሃብት አቶ ድንቁ ደያስ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የOSA conference ላይ ተገኝተው ለታዋቂው ምሁር ዶ/ር #ገመቹ_መገርሳና ለባለቤታቸው ዶ/ር አኒሳ የግማሽ ሚሊዮን ብር ስጦታ አበርክተዋል። በተጨማሪም ለታዋቂው ምሁርና የገዳ ተመራማሪ ፕሮፌሰር #አስመሮም_ለገሰ የ200,000 ብር ስጦታ አበርክተዋል።

Via THE FINFINNE INTERCEPT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ!

በሀገር ዓቀፍ #ደረጃ ሲካሄድ የነበረው 2ኛው የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት በአገር ውስጥ ባለሙያዎች በሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከቀረቡ 159 ሆቴሎች መካከል ለደረጃ ምደባው 88ቱ ተለይተው ነበር፡፡

በዚህም በዓለም ዓቀፍ የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ከ88ቱ ውስጥ 83ቱ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ኮከብ አግኝተዋል፡፡

ደረጃ ካገኙት መካከል በአዲስ አበባ 30፣ በአማራ ክልል 12፣ በኦሮሚያ ክልል 12፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል 10፣ በትግራይ ክልል 8፣ በቤኒሻንጉል ክልል 3፣ በድሬዳዋ 2 እንዲሁም በጋምቤላና በሀረር አንድ አንድ ሆቴሎች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ ምደባ አግኝተዋል፡፡

በአጠቃላይ 12 ባለ አራት፣ 13 ባለ ሶስት፣ 31 ባለሁለት እንዲሁም 27 ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ ነው ለሆቴሎቹ የተሰጠው፡፡

ከእነዚህ መካከል በአዲስ አበባ 6 ባለ አራት፣ 4 ባለ ሶስት ሲሆኑ፤ በአማራ 3 ባለ አራት 2 ባለ ሶስት እንዲሁም በኦሮሚያ 2 ባለ ሶስት ኮከብ ደረጃ ተለይተዋል፡፡

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሃምሌ22

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለደጋፊዎቹ የችግኝ ተከላ ጥሪ አስተላልፏል!!
.
.
የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ከሚያደርጉት ዘርፈ ብዙ በጎ ተግባራት አንዱ በክረምት ወቅት የተቸገሩ ወገኖቻችን ቤት ማደስና የሚያፈሱ ቆርቆሮዎችን መቀየር ፤ በትምህርት መሳሪያዎች እጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ ታዳጊ ህፃናት የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎችን አሰባስበው እርዳታዎችን ማድረግ እና በተመረጡ ቦታዎች የችግኝ ተከላዎችን ያከናውናሉ።

አፄዊያን ደጋፊዎቻችን የ2011 ዓ/ም ከመጠናቀቁ በፊት የፊታችን ሰኞ ሐምሌ 22 ቀን ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ፅ/ቤት የጳጳሱ መኖሪያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አቅጣጫ ገነት ተራራ ላይ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በተዘጋጀ ቦታ ደጋፊዎቻችን ማሊያ በማድረግ የችግኝ ተከላውን እንድታካሂዱ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club/ https://yangx.top/fasilkenemaSC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀምሌ22

ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ

የአረንጓዴ አሻራ ቀን የፊታችን ሰኞ ሃምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 200,000,000 (ሁለት መቶ ሚልዮን) ችግኝ እንደሚተከል ይታወቃል። እርሶም የዚህ ተግባር ተሳታፊ ይሁኑ! ከሚወዱት ክለብዎ ደጋፊዎች ጋር ችግኝ ይትከሉ!

የመትከያ ቦታ ቲሻየር አከባቢ ሲሆን ሁላችንም ቦኒ አካባቢ ተገናኝተን ተሰባስበን የምንሄድ ይሆናል መቅረት ክልክል ነው። ማልያ መልበስ እንዳይረሳ @jimmaAbajiifar

ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ

@tsegabwolde #tikvahethiopia
#ሐምሌ_22

ኢትዮጵያ ቡና

ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ሰኞ በሙሉ ኢትዮጵያ ከተማዎች እንደሚተከል ይጠበቃል። ሁላችንም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማልያ በመልበስ ከጠዋቱ 1:00–1:30 በተመደበልን ቦታ በሰአቱ በመገኘት ቀጥታ የክለባችንን አሻራ ለሀገራችን እናሳርፍ።

የመሳፈርያ ቦታዎች፦

#ፒያሳ_መዘጋጃ
#ሜክሲኮ_ቡና_እና_ሻይ
#መስቀል_አደባባይ
#ጀሞ
#ሳሪስ_አደይ_አበባ
#ሰባተኛ_ቶታል

#ኢትዮጵያ_ቡና @BUNA_GEBEYA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ብሄራዊ_ቤተ_መንግስት

የ2011 በጀት ዓመት የታማኝ የግብር ከፋዮች የሽልማትና የእውቅና መድረክ በብሄራዊ ቤተ-መንግስት ተካሂዷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፣ የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ፕሮግራሙን ታድመዋል።

“ሀገረን መውደድ በተግባር ነው” በሚል መሪ ቃል ነው መርሃ ግበሩ የተካሄደው። ወ/ሮ አዳነች በመክፈቻ ንግግራቸው በ2011 በጀት ዓመት 198.2 ቢሊዮን ብር የግብር ገቢ መሰብሰቡን ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር ከዋሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችም 1.6 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡንም ተናግረዋል። በመጨረሻም በበጀት ዓመቱ በታማኝ ግብር ከፋይነት ለተመረጡ 163 ተቋማት በዕለቱ የክብር እንግዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አማካይነት እውቅናና ሽልማት ተበርክቷል።

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅማ #ሀረማያ ~ አረንጓዴ አሻራ!
#TIKVAH_ETHIOPIA

ከወራት በፊት በጅማ እና በሀረማያ አረንጓዴ አሻራችንን እንዳሳረፍን ሁሉ በነገው ዕለት የሁለተኛ አመት ምስረታችን ሲከበር በአዲስ አበባ ከተማ አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤና ልማት ድርጅት ውስጥም አሻራችንን እናሳርፋለን።

🌱ቢሾፍቱ፣ ቡራዩ እና በሌሎች የአዲስ አበባ ከተማ አቅራቢያ የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች በሙሉ ነገ አበበች ጎበና እንድትገኙ ጥሪ እናቀርባለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎂TIKVAH ETHIOPIA~2 ዓመት🎂

#ደብረ_ብርሃን #ወሎ #ጅማ #ሀረማያ #ሀዋሳ #ወልቂጤ #መቐለ #ወልዲያ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #ሆሳዕና/#ዋቸሞ/

📎የሰውልጅ በሰውነቱ የሚከበርበት፤ የግለሰቦች አመለካከት፣ እምነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የኔ ነው የሚሉት ሁሉ የሚከበርበት፤ ፍቅር፣አንድነትና መተባበር የነገሰበት፣ የሰው ልጅ ሁሉ መሰብሰቢያ የሆነች ከጥላቻ የራቀች ሀገር እንገነባለን!! ተባብረን እንሰራለን፤ ለመጭው ትውልድ ኢትዮጵያን እናወርሳለን!!

እኛ ስንኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ ኢትዮጵያ ስትኖር እኛም እንኖራለን!

#ድፍን_ሁለት_ዓመት_በፍቅር_በመተባበር!

ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት እንገናኝ፤ ከእናታችንም ምርቃት እንቀበል!! ሁላችሁም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ናችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ስጦት_ለናተ

TIKVAH-ETH የተመሰረተበትን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የቤተሰባችን አጋሮች ስጦታ አዘጋጅተውላችኃል። ስጦታው በአ/አ እና ዙሪያዋ ለምትገኙ ቤተሰቦች የሚደርስ ይሆናል።

በአንድ ጊዜ 20 የቤተሰቡ አባል ይሸለማል...

የመጀመሪያ 5 አባላት Health watch
ቀጣዮቹ 5 አባላት Smart watch
ቀጣዮቹ 5 አባላት Century cinema 5 ትኬት
ቀጣዮቹ 5 አባላት Water prooof case

የሚቀርበውን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ ኖት?
ጥያቄው ለቀጣይ ስጦታዎች ይቆየን...

"እኔ ጥላቻንና ስድብን እፀየፋለሁ!"

ይህን👆ፅሁፍ ከታች ወዳለው አድራሻ ላኩ የቀደሙ 20 ሰዎች ይሸለማሉ፦

ምትልኩት በዚህ ብቻ ነው👉 @Emush21
.
.
ስጦታውን የሰጧችሁ፦
ሴንቸሪ ሲኒማ /@Century_Cinema/
ቴድ ቴክኖሎጂ @Tedtechofficial
@habmartofficial /ሀብማርት