‹‹ከከሰልና #እንጨት ጋር አብረን እንድንጓዝ ተገደናል፡፡›› ነዋሪዎች
.
.
በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ከከሚሴ በደዌ ሃረዋ በሚወስደዉ መንገድ ነዋሪዎች በትራንስፖርት ችግር #እንግልት እየደረሰባቸዉ ነዉ፡፡ የሚመደቡ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶች በቂ ባለመሆናቸዉ በአንድ አዉቶብስ ከ100 እስከ 120 ሰዎች እንደሚጓጓዙ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአካባቢዉ ህብረተሰብ እንደ አማራጭ #የጭነት መኪኖችን ለመጓጓዣነት እየተጠቀመባቸዉ ነዉ፡፡ የአካባቢዉ የትራንስፖርት ችግር ነዋሪዎችን በአይሱዙ መኪኖች ከከሰልና እንጨት ጋር አብረዉ እንዲጓዙ አስገድዷቸዋል፡፡ ለትራፊክ አደጋ #እያጋለጣቸዉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ለአብነት በቅርቡ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተሰምቷል፡፡ የደዌ ሃረዋ ትራፊከ ፖሊስ ምክትል ሳጅን መሃመድ ጀማል ህብረተሰቡ የሚያስፈልገዉን የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኘ አለመሆኑ ይታወቃል በተደጋጋሚ ትርፍ የሚጭኑትን አሽከርካሪዎች እየቀጣን ነዉ፣ ሆኖም መፍትሄ አልመጣም ብለዋል፡፡ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሃሰን በብሄረሰብ አስተዳደሩ የሚታየዉን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በጋራ ያስገነቡት የልብ ህክምና ማዕከል ከሰኞ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የደም ስር መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የፒሲአይ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ ማዕከሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ የሚገኝ ሲሆን ህክምናው ከኮሪያ በሚመጡ የህክምና ቡድን አባላትና በማዕከሉ ባለሙያዎች ይሰጣል፡፡
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጂንካ🔝
17ኛው የአርብቶ አደር ቀን በዓል #በጂንካ_ከተማ ስታዲየም ትከብሯል። በበዓሉ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚ #ደመቀ_መኮንን ተገኝተው ነበር።
ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia

#update ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከ~17ተኛው የአርብቶ አደር ቀን በዓል ጋር በተያያዘ ከአርብቶ አደሩ ህብረተሰብ ተዎካዮች ጋር ጂንካ ከተማ ገፅ ለገፅ ተወያይተዋል። ውይይቱ በመሰረተ ልማት፥ ውሃ እና ግጦሽ፥ የአመለካከትና፥ የሰላም ጉዳይ፥ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እና የመስኖ ልማት ፍላጎት ዙሪያ ያተኮረ ነው።
ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን የኦሞ ኩራዝ ~ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት ጎብኝተዋል። የኦሞ ኩራዝ ~ 3 የስኳር ልማት ፕሮጀክት በሙሉ አቅም የማምረት ሽግግር ሂደት ውጤታማ እንደሆነ የፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊዎች ገለፃ አድርገውላቸዋል።
ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ Office of Deputy Prime Minister of Federal Democratic Republic of Ethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥንቃቄ ይደረግ‼️
በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አንዳንድ ወረዳዎች #የደንጊ_በሽታ_ወረርሽኝ ምልክቶች መታየታቸውንና ሕዝቡ ራሱንና ቤተሰቦቹን ከበሽታው ለመጠበቅ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የሕዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ስጋት መከታተልና ቁጥጥር አስተባባሪ ዶክተር በየነ ሞገስ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የደንጊ በሽታ ወረርሽኙ የተከሰተው በፊቅ ዞን ሲሆን፣በዞኑ ለገሂዳ ወረዳም በአንድ ሳምንት 60 ሰዎች በበሽታው ተጠቅተዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል 41ዱ ህፃናት ናቸው።
በሽታው ከስድስት ወራት በፊት በዞኑ በዶሎ ኦዶ ወረዳ ተከስቶ በ331 ሰዎች ላይ ምልክቶች ታይቶ እንደነበር ዶክተር ሞገስ አስታውሰዋል፡፡ ካለፈው ሳምንት ወዲህ የታዩትን የደንጊ በሽታ ወረርሽኝ ምልክቶች ለመቆጣጠር የክልሉ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን የዳሰሳ ጥናት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ የኢንስቲትዩቱ ህክምና ቡድንም ወደ ሥፍራው መላኩን አስታውቀዋል።
በሽታው ትኩሳት፣ ከፍተኛ ራስ ምታት፣ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ቦታ ህመም ማቅለሽለሽና ማስታወክ ምልክቶች እንዳሉት ያስረዱት ዶክተር በየነ ፣ በሽታው መድሃኒት እንደሌለውና ክትባቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ በአብዛኛው ጥቅም ላይ አለመዋሉን አብራርተዋል።
እንደ ዶክተር በየነ ገለጻ፤ በሽታው በወባ መሰል ትንኝ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ትንኞቹ የሚናደፉት ቀን ላይ ነው፤ ለመራባት ሞቃት ወይም ሐሩር ቦታዎችን ይመርጣሉ፡፡ ኅብረተሰቡ ራሱንና ቤተሰቡን ለመከላከል የታቆሩ ውሃዎች እንዳይኖሩ ማድረግ፣ ርጥበት አዘል ቆሻሻ ነገሮችን ማስወገድ፣ ሰውነትን ሙሉ ለሙሉ በመሸፈን መንቀሳቀስ እና ህፃናትን በአጎበር ማስተኛት ይገባል፡፡
የበሽታውን አስተላላፊ ትንኞች ለመከላከልም የመከላከያ መድሃኒት ርጭት እንደሚደረግ ጠቅሰው፣ በሽታው ደንጊ ነው ብሎ ለማረጋገጥ ከታማሚዎች የደም ናሙና ተወስዶ በሴኔጋል ዳካር ምርመራ እንደሚደረግም ገልፀዋል።
በሽታውን ለመከላከል ቅድመ ትንበያ ተሰርቶ አንደነበር አስታውሰው፣በሽታውን መከላከል ግን አልተቻለም ብለዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የደንጊ በሽታ የላቦራቶሪ ምርመራ ለማድረግ የሚረዱ የመመርመሪያ መሣሪያዎችን ለማስገባትና የላቦራቶሪ ሥርዓቱን ለመዘርጋት አቅሙን ገንብቶ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡
የደንጊ በሽታ ከ2005- 2006 ዓ.ም ጀምሮ በድሬዳዋ ፣ከ2007- 2008 ዓ.ም በድሬዳዋ እና ጎዴ ባለፈው ዓመት ደግሞ በዶሎ አዶ ተከስቶ እንደነበር የኢንስቲትዩቱ መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

አብዴፓ‼️
የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ #አስቸኳይ_ስብሳባውን በትናንትናው ዕለት በሰመራ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
በስብሰባው ወቅትም የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የልማትና መልካም አስተዳደር ተሳታፊና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር #ኤይሻ_መሀመድ ተናግረዋል።
በክልሉ የሪፎርም ስራዎች መጀመራቸውን አመልክተው ይህንን በብቃት በማስፈጸም ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ ፓርቲው ህብረተሰብን ባሳተፈ አግባብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህንን ለማጠናከርም የአብዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር የድርጅትና የፖለቲካ ሪፎርም ስራዎችን የንቅናቄ ሰነድ በጥልቅት በመገምገም ሰነዱን ማፅደቁ ነው የተገለፀው፡፡
በተጨማሪም ፓርቲው በቅርቡ ከህብረተሰቡና ከአባላቱ ጋር የውይይት መድረኮችን ለማካሄድ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴው መምከሩን ሊቀመንበሯ አብራርተዋል፡፡
ትናንት በተጀመረው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴው አስቸኳይ ስብሰባም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያጸደቃቸውን ሰነዶችንና አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

#update የጀርመኑ #ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ነገ ዕሁድ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። በኢትዮጵያ ቆይታቸው ፕሬዝዳንት #ሣህለወርቅ_ዘውዴ እና ጠቅላይ ምኒስትር #ዐቢይ_አሕመድን ጨምሮ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ይነጋገራሉ።
#VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia