TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፈተ። ከዛሬ ጥር 17 ቀን ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆየው ይህ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዝቢሽን ማዕከል በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል። አቶ ጌታቸውን ለመያዝ አስፈላጊ ሒደቶች እየተከናወኑ እንደሆነም ነው የተሰማው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በከባድ #የሰብዓዊ_መብት_ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉት 14 ሰዎች ላይ አቃቤ ሕግ ለቀዳሚ ምርመራ የጠየቀውን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ፈቀደ። ተጠርጣሪዎቹ በነ ጎህ አጽባሃ መዝገብ በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል በቁጥጥር ስር ከዋሉት 33 ሰዎች ዝርዝር መካከል ከ1ኛ እስከ 16ኛ ያሉት ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ወጣቶች‼️

የዓመታት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎቻቸው #በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በድሬደዋ ወጣቶች ባካሄዱት ሰልፍ ጠየቁ፡፡

ወጣቶቹ በተለያዩ የከተማው አስተዳደር አካባቢዎች በመዘዋወር ባካሄዱት ሰልፍ ጥያቄያቸውን ባሰሟቸው መፈክሮች  አስተጋብተዋል፡፡

በዚህም ድሬዳዋ ሁሉም ብሔሮችና ብሔረሰቦች በፍቅር በአንድነትና በእኩልነት የሚኖሩባትን መሆኗን ጠቅሰው አብዛኛውን ወጣትና ህዝብ ያገለለ የመንግስት መዋቅርና አሰራር ሊፈርስ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በተግባር ላይ ያለው የፖለቲካ የስልጣን ክፍፍልና አሰራር የአብዛኛውን ህዝብና ወጣት ከልማት ተጠቃሚነት ያገለለ መሆኑን ወጣቶቹ ገልጸዋል፡፡

መዋቅሩ ወጣቱን ለከፋ የመልካም አስተዳደር ችግር የዳረገው በመሆኑ በፍጥነት እንዲቀየር ጠይቀዋል፡፡

በሰልፉ የተካፈለው ወጣት ሰለሞን መክብብ  በሰጠው አስተያየት የአስተዳደሩ ከንቲባ ወጣቶችን ለማናገር የያዙትን ቀጠሮ መሰረዛቸው በወጣቶቹ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን ተናግራል፡፡

”እኛ ሁሉም ወጣቶች የሚሳተፉበት ውይይት ነው የምንፈልገው ፤ የወጣቶች ወኪል እየተባለ አዳራሽ የሚሰበሰበው እኛን ስለማይወክሉ የውክልና ውይይት አንፈልግም” ብሏል፡፡

”አንድም ባለስልጣን ቀርቦ #ያናገረን የለም፤ ከተማዋ መሪ የላትም፤ የፌደራል መንግስት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ለጥያቄዎቻችን ምላሽ እንዲሰጠን እንፈልጋለን”  ያለው ደግሞ ሌላው የሰልፉ ተካፋይ ወጣት ሲሳይ አየለ ነው፡፡ በሁሉም  መስክ አድሏዊነት የሌለው ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖር ጠይቋል፡፡

የኢዜአ ሪፖርተር በከተማው ተዘዋውሮ እንደተመለከተው ዛሬ በከተማ የተካሄደው ሰልፍ ካለፉት ሁለት ቀናት የበለጠ  አብዛኛውን የከተማው  አካባቢ ያዳረሰ ነው። በነበረው ግርግር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና አገልግሎት መሰጪዎች መሰተጓጎላቸውን ተመልክቷል፡፡

በጤና ጣቢያዎችና በድል ጮራ ሆስፒታል የኢዜአ ሪፖርተር ባደረገው ቅኝት የተጎዱ ሰዎች ህክምና አግኝተው ሲመለሱ አይቷል፡፡

#የመከላከያ_ሠራዊት አባላት የወጣቶቹ ቁጣ  በሰላማዊ መንገድ ለማብረድና ለማረጋጋት ያደረጉት ጥረት በሰልፍ አድራጊዎችና በሌላም ህብረተሰብ ዘንድ በአዎንታዊ ጎኑ ድጋፍ አግኝቷል፡፡

በአሁን ሰዓት ሰራዊቱ በድንጋይ የተዘጉትን መንገዶች በማጽዳት ለተሸከርከሪዎች ክፍት እንዲሆኑ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገለጹ፡፡ በዞኑ ሻኪሶና ጎሮዶላ ወረዳ የትጥቅ ትግል ሀሳብ የነበራቸው 20 የኦነግ አባላት ትጥቃቸውን በማስቀመጥ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ተመልሰዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንዱስትሪ ፓርኮች

ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር አልመው የተቋቋሙት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከፍተኛ #የሰራተኛ_ፍልሰት እየፈተናቸው ነው ተባለ፡፡ ከቀጠሯቸው ሰራተኞች በሩብ አመት ውስጥ እስከ 98 በመቶ መልሰው የለቀቁባቸው ፓርኮች መኖራቸውን ተሰምቷል፡፡

ለዚህ ዋናው ምክንያት ፓርኮቹ ተመርቀው ስራ ከጀመሩ በኋላ በአካባቢው የቤት ኪራይ በከፍተኛ መጠን #መጨመር ነው ተብሏል፡፡

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ለ3 ተከታታይ አመታት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ያደረገው የክዋኔ ኦዲት ግኝት እንደሚያሳየው በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሰራተኞች ፍልሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው፡፡

እንደ ምሳሌም በቦሌ ለሚ ቁጥር አንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ በ2008 ሩብ አመት ከተቀጠሩ ሰራተኞች 42 ነጥብ 5 በመቶ ለቅቀዋል፡፡

በ2009 ዓ/ም ደግሞ በዚሁ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እድል ካገኙት 72 ነጥብ 3 በመቶዎቹ ስራውን ትተው ሄደዋል፡፡

በሶስተኛ አመት 2010 ዓ/ም ከቀደሙት ጊዜ በባሰ ሁኔታ የለቀቁት ሰራተኞች ቁጥር 98 ነጥብ 9 በመቶ መድረሱን የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ያሳያል፡፡

እንዲህ ያለው የሰራተኞች ፍልሰት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የተቋቋሙበት ዋና ዓላማ የሆነውን ለዜጎች የስራ እድል መፍጠርን ሳይሳካ እንዲቀር ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የፓርኮቹ ምርታማነትና የወጪ ንግዱ ላይም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ተነግሯል፡፡

ወሬውን የሰማነው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ የተደረገውን የክዋኔ ኦዲት ግኝትና የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎችን በተመለከተ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ሲመክር ተገኝተን ነው፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ #ሌሊሴ_ነሜ እንዳሉት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ስራ #የሚለቁ ሰራተኞች ቁጥራቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደረገው ዋና ምክንያት የቤት ኪራይ መጨመርና የኑሮ ውድነት ነው ብለዋል፡፡

#የሐዋሳ_ኢንዱስትሪ_ፓርክ ስራ በጀመረ ጊዜ 300 ብር የነበረው የቤት ኪራይ ከ1 ሺህ 100 ብር በላይ ሆኗል ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነቱ ሰራተኛው ፓርኩን ለቆ በተለያዩ የግንባታ ስራዎች ላይ በቀን ሰራተኝነት ለማስራት እንዲመርጥ አድርጎታል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡ በመሆኑም መንግስት ለጉዳዩ እልባት በመስጠት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ስራ በጀመሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች 45 ሺ ሰራተኞች ተቀጥረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
በአቶ በረከት ስምኦን ጉዳይ...‼️
በአቶ በረከት ስምኦን ጉዳይ...


በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩት ቀድሞው የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ሚንስትር የአቶ #በረከት_ስምኦን እስር ዜና አሁንም እያነገገረ ነው።

አቶ በረከት በገዥው ፓርቲ ውስጥ የነበራቸውንና ለረዥም ዓመታት የዘለቀ ከፍተኛ የፖለቲካ ሚናና የመንግሥት ሥልጣን ተንተርሶ የተለየ ትኩረት የሳበው እስራቸው፤ ከተለያዩ አካባቢዎች በርካታ አስተያየትችን ጋብዟል።

ከዚህ ቀደም በትዊተር አማካኝነት ባስተላለፏቸው መልዕክቶች “አቶ በረከት ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” የሚል አስተያየት የሰነዘሩት የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ ሚስ #አና_ጎሜሽ የቀድሞው የኢሕአዴግ ባለ ሥልጣን እስር ዜና እንደተሰማ እርምጃውን በማወደስ ፈጥነው አስተያየታቸውን ካሰፈሩት ውስጥ ናቸው።

ሚስ አና ጎሜሽ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲያ ጉዳዮች ዙሪያ ጠንከር ያሉ ትችቶችን በማቅረብም ይታወቃሉ።

“የተከሰሱበትን ጭብጥ ሙሉ በሙሉ ባላውቅም .. በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በደረሰው በደል፣ በበኩላቸው በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ ይሆናሉ፤ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።” የሚሉት ሚስ ጎሜሽ - የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚያ ቀደም ታይቶ በማያውቅ ደረጃ ወጥቶ ድምጹን በሰጠበት፣ የአውሮፓ ሕብረትን በመወከል በታዛቢነት በተሳተፉበት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ወቅት ያዩትን ዋቢ አድርገው፤ ከአቶ በረከት ጋር በቀጥታ የተገናኙባቸውን ጊዜያት ያነሳሉ።

በኢትዮጵያ በመጣው “እጅግ አሰደናቂ” ባሉት ለውጥ .. ከሀገራቸው ውጭ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ተቃዋሚዎች ወደ ሃገር እንዲገቡ መደረጋቸው፣ የሚያምኑትን በግልጽ መናገር መቻላቸው “አሳድሮብኛል” ያሉትን ትልቅ ተሥፋም ሚስ ጎሜሽ ገልጠዋል።

ምንጭ፦ VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰሱ። ም/ፕሬዚደንት ሙስጠፋ ኡመር የሶማሌ ህዝብ ዲምክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ላይ የደረሱበትን ማስረጃ ለሚዲያ ለመግለፅ የማይቻልና ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ ለፌዴራል ባለስልጣኖች በሚሰጡት ማብራሪያ ላይ የሚገለፅ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል። ሙስጠፋ 11 የካቢኔ አባላትን መርተው ዛሬ ከሰዓት #አዲስ_አበባ መግባታቸውን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።
.
.
https://telegra.ph/BREAKING-01-25
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ15 ደቂቃ ውስጥ🔄የTIKVAH-ETH #የጥር 17 ማጠቃለያን ይዤ እቀርባለሁ!! የትም እንዳትሄዱ። በተለይ በስራ ስትደክሙ የዋላችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅድስተማርያም ዩኒቨርሲቲ‼️

የቅድስተማርያም ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ እውቀትን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል “የተሞክሮ ማካፈያ” መድረክ አካሄደ።

ተሞክሮቸውን ያካፈሉት በአለም እውቅና ያላቸውና በግዕዝ ሶፍትዌር ስራ የታወቁት ኢትዮጵያዊ ዶክተር አበራ ሞላ ሲሆኑ፤ በወቅቱ እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያዊያን ብዙ መስራትና በቴክኖሎጂው መርቀቅ የሚችሉ ናቸው።

በቴክኖሎጂ የታገዘ ሀብትን ለአገር መስጠት ትልቅ ነገር ነው ያሉት ዶክተር አበራ ሶፍትዌሩን ሰርቼ ለአለም እንዲተዋወቅና ጥቅም ላይ እንዲውል ያደረኩት ሌላው እኔን ተከትሎ ተጨማሪ ነገር እንዲሰራ ነው። በተለይ ወጣቶች አሁን ያለውን እድል ተጠቅመው መስራት ቢችሉ አገርን ወደ ተሻለ ማሸጋገር ከማስቻላቸውም በላይ ቋንቋችንንም ያሳድጋሉ።

እንደ ዶክተር አበራ ገለጻ፤ የራስን በራስ ማስተዋወቅ የበለጠ ትርፋማ ያደርጋል። ምክንያቱም ሁሉን ነገር ማወቅ ይቻልበታልና። በዚህም ወጣቱ እኔን አርኣያ አድርጎ ያለውን አማራጭ የአገር ሀብት የሆኑ ሰዎችን መጠቀም አለበት። ከእነርሱ ለመማር እራሱን ዝግጁ ሊያደርግ ይገባልም።

ብዙ ሰዎች የአማሪኛ ፊደላትን ወይም ግዕዙን እንዲሁም የተለያዩ ብሔረሰቦች ቋንቋን ትተው እንግሊዝኛ ያጋደሉበት ምክንያት ሰፊ አማራጮችን ፍለጋ ነው። በአገርኛ ቋንቋዎቻችን ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ደግሞ በቴክኖሎጂ ረገድ እውቀት ያላቸውን ዜጎች መጠቀም ይኖርብናል ይላሉ ዶክተሩ።

«ይህ ትውልድ ሰፊ አደራ አለበት፤ ትውልዱ ሀብት እንዳለው አምኖ ቴክኖሎጂውን ለዚህ ሀብት መገልገያነት ማዋል ይጠበቅበታል» ያሉት ዶክተር አበራ፤ ቅድስተ ማርያም ዩኒቨርስቲ ይህን መረሃ ግብር ሲያዘጋጅ አገርኛ ቋንቋን ተጠቅሞ በቴክኖሎጂው እንዴት መላቅ እንደሚቻል ለማስተማረ ነው ብለዋል።

የዩኒቨርስቲው የምርምር እውቀት ማኔጅመንት ቢሮ ዳይሬክተር ዶክተር ከበደ ካሳ በበኩላቸው፤ እውቀት ኖሮት እውቀቱን የሚያካፍል አገር ወዳድ ሰው አገሪቱ አላት። ይሁንና መጠቀሙ በግለሰቦች ፍላጎት ይወሰናል። በመሆኑም ዩኒቨርስቲው እንደነዚህ አይነት ምሁራንን በመጋበዝ ልምዳቸውን እንዲያጋሩ ያደርጋልና በተማሩት መሰረት ወደተግባር የመቀየሩ ሁኔታ የተማሪው መሆን አለበት ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድሬዳዋ‼️DireTv በድሬዳዋ ትላንት ቀጥሎ ስለዋለው ተቃውሞ የዘገበው...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተለያዩ ወንጀል #ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ለዋሉና ሲፈለጉ ለነበሩ 4 ሺህ 382 ግለሰቦች #የምህረት የምስክር ወረቀት መሰጠቱን የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ መስሪያ ቤት ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዙምባዌ‼️

በዚምባቡዌ የተቀሰቀሰውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር የተሰማሩ የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት በሚያደርጉት አሰሳ ሴቶችን #አስገድደ_ይደፍራሉ ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ወነጀሉ። መንግስት እየወሰደ ያለው ኃይል የተቀላቀለበት እርምጃ መቀጠሉ ተነግሯል።

“ቁጥራቸው በርከት ያሉ ሴቶች በጸጥታ ኃይሎች አባላት እንደሚደፈሩ የሚያመለክቱ የሚረብሹ መረጃዎችን ተቀብለናል” ሲሉ የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች የደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ዴዋ ማሂንጋ ለአሶሴትድ ፕሬስ ተናግረዋል። “ድብደባ፣ ማስፈራራት እና ሌሎችም ጥቃቶች ከምንጋጋዋ መመለስ በኋላም ቀጥለዋል” ብለዋል።

የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት #ኤመርሰን_ምንጋጋዋ በነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት በሀገራቸው የተቀሰቀሰውን ብጥብጥ ለማረጋጋት በውጭ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝታቸው አቋርጠው ባለፈው ሰኞ ወደ መዲናይቱ ሃራሬ መመለሳቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንቱ በሀገሪቱ ያለው “ሁከት” ተቀባይነት እንደሌለው ቢናገሩም ዚምባቡዌ አሁንም መረጋጋት እንደራቃት እና ጥቃቶች መቀጠላቸውን የሀገሪቱ ዜጎች ይናገራሉ።

ባለፈው ሳምንት በዚምባቡዌ በተቀሰቀሰው ግጭት ቢያንስ 12 ሰዎች ሲገደሉ 300 ሰዎች መቁሰላቸውን የመብት ተሟጋቾች እና የህክምና ባለሙያዎች አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia