TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
አብዴፓ‼️

የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ #አስቸኳይ_ስብሳባውን በትናንትናው ዕለት በሰመራ ከተማ ማካሄድ  ጀምሯል።

በስብሰባው ወቅትም  የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የልማትና መልካም አስተዳደር ተሳታፊና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ  መሆኑን የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር #ኤይሻ_መሀመድ ተናግረዋል።

በክልሉ የሪፎርም ስራዎች መጀመራቸውን አመልክተው ይህንን በብቃት በማስፈጸም ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ ፓርቲው ህብረተሰብን ባሳተፈ አግባብ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህንን ለማጠናከርም የአብዴፓ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር የድርጅትና የፖለቲካ ሪፎርም ስራዎችን የንቅናቄ ሰነድ በጥልቅት በመገምገም ሰነዱን ማፅደቁ  ነው የተገለፀው፡፡

በተጨማሪም ፓርቲው በቅርቡ ከህብረተሰቡና ከአባላቱ ጋር የውይይት መድረኮችን ለማካሄድ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴው መምከሩን ሊቀመንበሯ አብራርተዋል፡፡

ትናንት በተጀመረው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴው አስቸኳይ ስብሰባም የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያጸደቃቸውን ሰነዶችንና አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia