TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.15K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ስምምነቶች ተፈረሙ!

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያና በፈረንሳይ መካከል ስምምነቶች እንዲፈረሙ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ ሥልጠና፣ የዐቅም ግንባታና ስትራቴጃዊ የልምድ ልውውጥን የሚያካትተውን የመከላከያ ትብብር ስምምነት ፈርመዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በበኩላቸው

1. የፈረንሳይ መዋዕለ ንዋይን የተመለከተ የመግባቢያ ሰነድ።
2. ለምጣኔ ሀብት ማሻሻያ የፋይናንስ ትብብር የጋራ መግባቢያና
3. የቅርስ ትብብር የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ፈርመዋል።
የእነዚህ ስምምነቶች መፈረም በኢትዮ-ፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት መጠናከሩን ማሳያ ነው።

ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ስኬታማ ነው‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም እንኳ ከትናንት ወዲያ በደረሰው የቦይንግ 737-8 ማክስ ET302 አደጋ ችግር ውስጥ ቢሆንም ዛሬም የአፍሪካው ምርጥ በመሆን ነው የሚታወቀው።

አየር መንገዱ አፍሪካ ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ጥቂት አየር መንገዶች ትልቁም ነው።

በ2017/2018 በጀት ዓመት አየር መንገዱ 245 ሚሊዮን ዶላር ሲያተርፍ 10.6 ሚሊዮን መንገደኞችንም አመላልሷል።

በአፄ ሃይለ ስላሴ አገሪቷን የማዘመን እርምጃ እንደ አውሮፓውያኑ በ1945 የተቋቋመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚያው ዓመት ማብቂያ የመጀመሪያ በረራውን ወደ ካይሮ አድርጓል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በቁጥሮች፦

74 ዓመቱ ነው111 ፕሌኖች አሉት127 መዳረሻዎች አሉት በአጠቃላይ10.6 ሚሊዮን መንገደኞችን አጓጉዟል እንደ አውሮፓውያኑ 2017/20183.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መሰብሰብ ችሏል በ 2017/2018245 ሚሊዮን ዶላር አትረፏል በተመሳሳይ ዓመት

አየር መንገዱ ማስፋፊያ ማድረጉን ተከትሎ 111 አውሮፕላኖች ያሉት ሲሆን አለም ዓቀፍ መዳረሻውን ወደ 106 ፤ የአገር ውስጡን ደግሞ 23 አድርሷል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 787 ድሪምላይነርና 757 ትልልቅ ጫኝ አውሮፕላኖችን ለመጠቀም የመጀመሪያው የአፍሪካ አየር መንገድ ሲሆን በዚህም አዳዲስ አውሮፕላኖችን የሚጠቀም አየር መንገድ ሆኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አማካይ እድሜ 5.4 ዓመት ሲሆን በብሪቲሽ አየር መንገድ የአንድ አውሮፕላን አማካይ እድሜ 13.5 ዓመት፣ በዩናይትድ አየር መንገድ 15 ዓመት እንዲሁም በአሜሪካ አየር መንገድ 10.7 ዓመት ነው።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደህንነት አስተማማኙ የአፍሪካ አየር መንገድም ነው። ቢሆንም እስከ አሁን አራት ከባድ አደጋዎችን አስተናግዷል።

ከአሁኑ አደጋ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ያጋጠመው እንደ አውሮፓውያኑ በ2010 ET 409 ከቤሩት አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ነድዶ ሜዲትራኒያን ላይ በመውደቁ ነበር።

በአደጋው 89 መንገደኞችና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሞተዋል። የሊባኖስ የምርመራ ቡድን የበረራ ስህተት ለአደጋው ምክንያት ነው ቢልም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን አውሮፕላኑን ያጋጠመው ፍንዳታ ነው በማለት የቡድኑን ሪፖርት ውድቅ አድርጎታል።

አውሮፕላኑ አደጋው እንዲያጋጥመው የተሰራ ሴራ፣ መብረቅ ወይም እንዲወድቅ ተመትቷል የሚሉ ግምቶችም በኤክስፐርቶች ተቀምጠዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ1988 ደግሞ በባህር ዳር የአየር መንገዱ አውሮፕላን በማረፍ ላይ ሳለ ኤንጅኑ ውስጥ እርግቦች በመግባታቸው በተነሳ እሳት 35 ሰዎች ሞተዋል።

በ1996 ደግሞ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ይበር በነበረው ቦይንግ 767 ላይ ጠለፋ በመደረጉ አውሮፕላኑ በኮሞሮስ ደሴት አቅራቢያ ህንድ ውቅያኖስ ላይ መውደቁ ይታወሳል። በዚህ አደጋ ከ 175 መንገደኞች 125ቱ ሞተዋል።

የአፍሪካ መሪ፦

አየር መንገዱ ከራሱ አልፎ የሌሎች አፍሪካ አገራት አየር መንገዶችን ይረዳል።

በዚህ እርምጃው በማላዊ አየር መንገድ 49 በመቶ ፣ በዛምቢያ 45 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ያለው ሲሆን በሞዛምቢክም በአዲስ መልክ አየር መንገድ ስራ የማስጀመር ፕላን እንዳለው ቀደም ብሎ አስታውቋል።

በተመሳሳይ ትንንሽ አካባቢያዊ ጣቢያዎችን በጅቡቲ፣ ቻድ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ለመክፈት ንግግር ላይ ነው። እንደ ማላዊና ቶጎ ባሉ አገራት አሁንም ማእከላት አሉት።

በዚህ መልኩ ችግር ውስጥ የገቡ የአፍሪካ አየር መንገዶችን መታደግ ኢትዮጵያ አየር መንገድን በኢንዱስትሪው ትልቅ አድርጎል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በጥሩ የንግድ ስትራቴጂውም ይታወቃል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እየተደረገ ያለው ማስፋፊያ በአፍሪካ አቬሽን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ ሌላ ከፍታ ይወስደዋል ተብሎም ይታመናል።

ምንም እንኳ የአሁኑ አደጋ አየር መንገዱን ቢያንገጫግጨውም የረዥም ጊዜ ራዩን እንደሚያሳካ ይታመናል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉“እግዚያብሔር ሰጠ እግዚያብሔር ነሳ” - የአብራሪ ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር ጌታቸው ተሰማ

👉ለእናቱ ደውሎ ወደእርሷ(ወደናይሮቢ) እየሄደ እንደነበር ነግሯት ነበር

👉አብራው ከምትሠራ ካፒቴን እጮኛው ጋር ሊጋቡ እቅድ ይዘው ነበር

👉ልጄ ከልጆቼ ሁሉ የተለየ መልካም ሰው ነበር - "ደግ አይበረክትም ይባል የለ"

👉አንድ ልጅ እንኳን ለአገሬ ላበርክት ብዬ ነበር ኢትዮጵያ ያስተማርክፐት

👉አስክሬኑን አግኝቼ የመቅበር ዕድል ስላላገኘሁ በቦታው አንዲት ድንጋይ ብትቆምለት ደስ ይለኛል

“እግዚያብሔር ሰጠ እግዚያብሔር ነሳ” - በሚል የፈጣሪያቸው ቃል እየተፅናኑ እንደሚገኙ የገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውና ከትናንት በስቲያ ቢሾፍቱ አቅራቢያ የወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አይሮፕላን አብራሪ ያሬድ ጌታቸው አባት ዶ/ር #ጌታቸው_ተሰማ የእርሳቸው ልጅ ብቻ ሳይሆን ብዙዎች ያለቁበት አደጋ በመሆኑ በቦታው ላይ በስማቸው የመታሰቢያ ሃውልት ቢቆም ምኞታቸው እንደሆነ ተናገሩ። ምክኒያታቸው ደግሞ ከአደጋው ከፍተኛነት የተነሳ የልጃቸውን አስክሬን አግኝተው መቅበር እንደማይችሉ ስለተረዱ ቢያንስ ለመታሰቢያ እንኳን “ስሙ በቦታው ቢሰፍርልኝ” እወዳለሁ ብለዋል።

Via VOA 24
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሌሎች አካባቢ ያሉ መረጃዎች አሰባስቤ እና የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሬ እንደጨረስኩ ወደናተ አደርሳለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው ተወያዪ:: መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዬች ዙርያ ተመካክረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ🔝

በሀዋሳ ከተማ ተጠርቷል በተባለ የስራ ማቆም #አድማ ባንክ ቤቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የንግድ ተቋማት፣ ዝግ መሆናቸውን የአይን እማኞች ገልፀውልኛል። እንዲሁም የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚሰሩ ሰራተኞችም ከስራ እንዲወጡ ተደርጓል። ምክንያቱ ደግሞ የክልል ጥያቄው በአግባቡ ምላሽ እየተሰጠው አይደለም በሚል እንደሆነ ያነጋገርኳቸው የከተማው ነዋሪዎች ነግረውኛል። ከዚህ በተጨማሪ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ምሽት ተሰራጭቷል በተባለ የአድማ ጥሪ ወረቀት የዛሬ የትምህርት መርሃ ግብር ተቋርጧል።

ፎቶ: የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

የሚመለከታቸው አካላት አነጋግሬ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን አቀርባለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መርዶው በቤተሰብ አንደበት...

እናቴ ደህና ዋይ ብሎ ተሰናበተኝ። ሶስት ሺህ አራት መቶ ብር አስራት ለቤተ ክርስቲያን በስሜ ስጡልኝ ፤እኔ ቸኩያለሁ ብሎ አባቱን ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ድረስ ሸኝቶት፤ እርሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ መስሪያ ቤቱ፤ ቀጥሎም ተሽከርካሪውን መስሪያ ቤት ግቢ አቁሞ በታክሲ ተሳፍሮ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዘ።

አየር መንገድ ከደረሰ በኋላም ታላቅ እህቱን በስልክ በረራ መጀመሩን ነግሯታል። ‹‹ሰፈራችን ደርሻለሁ ነይ ውጪ አውሮፕላኑ ቤታችንን እያለፈ ነው እይኝ›› እያለ ቀልዶ ተሰናብቷታል ይላሉ። መጋቢት አንድ ቀን 2011 ዓ.ም የተከሰከሰው አውሮፕላን ልጃቸውን የነጠቃቸው ወይዘሮ ምንትዋብ ምትኩ ። የስንታየሁ እናት ወይዘሮ ምንትዋብ ልጃቸው በሰላም እንደደረሰ ወድሞቹንና እህቱን ጠየቁ። ‹‹አልደወለም ቆየት ብሎ ይደውላል ኔት ወርክ አስቸግሮት ይሆናል›› አሏቸው።

ባለፈው ሲሄድም ቆየት ብሎ እንደደወለም አስታወሷቸው። ግን መረጋጋት አልቻሉም። እነርሱ ግን አደጋውን ሰምተው ነበር። ‹‹ሁልጊዜ ሲጓዝ እንደደረሰ ይደውልልኛል። አሁን ግን መድረሱን ሳይነግረኝ ዘገየብኝ። ሆዴ ሲረበሽ ነበር የዋልኩት። ቴሌቪዠን ከፈትኩ ወደ ኬንያ እየበረረ የነበረው አውሮፕላን ስለደረሰበት አደጋ በዜና ሲናገር ሰማሁ።

ደነገጥኩ ራሴን ስቼ ወደቅኩ። ከእዛ በኋላ የሆነውን አላስታውስም›› ሲሉ ሃዘን በተቀላቀለው አነጋገር የልጃቸውን መርዶ የሰሙበትን አጋጣሚ ነገሩኝ። ወይዘሮ ምንትዋብ ጥቁር ለብሰዋል፣ ነጠላ አጣፍተዋል፣ በለቅሶ ብዛት ድምጻቸው ሰሏል፣ በሀዘን ፊታቸው ጠቁሯል። ደህና ግባ ብለው የተሰናበቱት ልጃቸው ወጥቶ ሳይመለስ ቀርቶባቸዋል። ልጃቸውን ሞት ነጥቋቸዋል። በእነ ምንትዋብ ቤት ደጃፍ ድንኳን ተተክሏል። በእርሳቸው ደጃፍ ሀዘንተኛ እያስተናገደ ነው። ጎረቤቱም ቤተሰቡን እያጽናና፣ አስከሬን እየተጠባበቀ ይገኛል። የአስናቀ ግርማና የስንታየሁ ሻፊ ጓደኝነት የሚጀምረው በ1997 ዓ.ም ነው። አዳማ አጼ ገላውዴዎስ ትምህርት ቤት የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ አንደኛ ዓመት ተማሪ እያሉ ነበር የተዋወቁት።

ስንታየሁ የከፍተኛ ማዕረግ ተማሪ እንደነበር አስናቀ ያስታውሳል። በአጭር ጊዜ ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበ፣ ንቁ፣ ከሰው ጋር ተግባቢና ቁምነገረኛ እንደነበረ ይናገራል። የሁለቱ ጓደኛሞች ጉዞ በስራው አለምም ቀጠለ በ2000 ዓ.ም ሞኤንኮ አብረው ተቀጠሩ። ስንታየሁ በድርጅቱ ታሪክ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገበ ከሲኒየር ቴክኒሽያንነት በአንዴ ቴክኒካል ስራ አስኪያጅ ሆነ። በድርጅቱ ውስጥ የሚደረጉ ውድድሮች ላይ ሁለት ጊዜ አሸንፎ ጃፓን ድረስ ተጉዞ ተሸልሟል። ጃፓን ስልጠናም ወስዷል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ አግኝቷል። በሙያው በአፍሪካ ባሉ የቶዮታ ኩባንያዎች መካከል በተደረገ ሙያዊ ውድድር አሸንፏል። በቶዮታ ኩባንያ ስር ባሉ ኩባንያዎች የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተዘዋውሮ አሰልጥኗል። ስንታየሁ ለአፍሪካውያን ባለሙያዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና ለመውሰድ ኬንያ ይጓዝ ነበር።

የሁለቱ ጓደኛሞች የ14 ዓመታት ጓደኝነትም ወደ ፊት አልቀጠለም። ቅዳሜ ዕለት በስልክ ተሰነባብተዋል። ጓደኛው እስካሁንም የጓደኛው ሀዘን ከውስጡ እንዳልወጣ ገልጾልኛል። ቢቢሲ አማርኛው እንደዘገበው፤ ዋና አብራሪው ያሬድ ጌታቸውና ሃሰን የሚተዋወቁት ከዓመታት በፊት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ፀጉር ቤት ያሬድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበራሪ ፅሁፍ ወረቀት ይዞ ሃሰን [ፓይለት ነህ] ብሎ ያሬድን በጠየቀበት አጋጣሚ ነበር። ያሬድ ኬንያ እንደተወለደ ነግሮት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ያወሩት በስዋሂሊ እንደነበር ሃሰን ያስታውሳል። ሀሰን እንደሚለው ያሬድ ስፖርት የሚወድ አይነት ሰው የነበረ ሲሆን ለራግቢ ግን ልዩ ፍቅር ነበረው።

ያሬድና ሃሰን አዘውትረው ይገናኙ የነበረው ግእዝ የሚባል የፈረንሳይ ሬስቶራንት ራግቢ ስፖርት ለመመልከት ነው።መጀመሪያ አካባቢ ሀሰንም መኪና ስላልነበረው አብዛኛውን ጊዜ ያሬድ ያሽከረክር የነበረውን የአባቱን አሮጌ መኪና እየሾፈረ ብዙ ቦታዎች መሄዳቸውንም ሃሰን ያስታውሳል። ያሬድና ሃሰን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት የነበረ ሲሆን በሎሜ ስካይ አየር መንገድ ስራ ስላገኘው ጓደኛቸው ነበር ያወሩት። ያሬድ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ነው።

እናቱ ኬንያዊ ሲሆኑ አባቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የልጅነት ጊዜውን በኬንያ ያሳለፈ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ተከታትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቬሽን ትምህርት ቤትን ተቀላቅሏል። ጓደኛው የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ የእነሱ ጓደኛ ያሬድ እንደሆነ ሲነግረው ለማመን በጣም እንደከበደውና ሊሆን አይችልም የሚል ስሜት እንደተሰማው ይናገራል። “ለማመን የሚከብድ ነገር ነው።መተኛት አልቻልኩም እስካሁን ድንጋጤ ውስጥ ነኝ” ብሏል ሃሰን።

ቻይና እሁድ ዕለት በቢሾፍቱ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይነት አውሮፕላኖቿ እንዳይበሩ ማገዷን ሲኤንኤን ዘግቧል። ቦይንግ 737 ማክስ 8 የተባለው ይህ አውሮፕላን በስድስት ወራት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መከስከሱ ታውቋል። ከስድስት ወራት በፊት የኢንዶኖዥያ አውሮፕላን ተመሳሳይ አደጋ እንደደረሰበት ይታወሳል። እሁድ ዕለት ጧት ላይ የተከሰከሰው የኢትዮጵያው አውሮፕላን አብራሪ በረራውን ከጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አውሮፕላኑ ችግር እንዳጋጠመው ሪፖርት አድርጎ እንደነበርም ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ 2:38 ደቂቃ ላይ 149 መንገደኞችና 8 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ የሚመረምር ኮሚቴ እንዳዋቀረ በትዊተር ገፁ አስታውቋል። አየር መንገዱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የኢትዮጵያ የሲቪል አቪየሽን ባለስልጣንና የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ጋር በመተባበር የአደጋውን መንስኤ ይመረምራሉ ተብሏል። የሟቾች ማንነት ከታወቀ በኋላ አስከሬናቸው ለቤተሰቦቻቸው እንደሚሰጥ አየር መንገዱ አስታውቋል። በአደጋው የሞቱ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦችም መርዶው ተነግሯቸዋል። በአውሮፕላን አደጋው በአጠቃላይ የ157 ሰዎች ህይወት አልፏል።

አዲስ ዘመን መጋቢት 4/2011
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update እንግሊዝ ማንኛዉም #የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በግዛቷ እንዳይበሩ መከልከሏን አስታወቀች፡፡ ዉሳኔዉን ተከትሎ አየር ላይ የነበሩ 2 የቱርክ አየር መንገድ ንብረት የሆኑ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ አውሮፕላኖቹ ከኢስንታቡል አውሮፕላን ማረፊያ ተነስተው ወደ በርሚንግሃምና ጋትዊክ ሲበሩ ነበር፡፡ ወደ በርሚንገሃም ሲበር የነበረው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከአራት ሰዓታት በረራ ዉስጥ 3 ሰዓቱን በመብረር ምዕራብ ጀርመን ፍራንክፈርት ደርሶ እንደነበር ነው የተገለፀው። ወደ የጋትዊክ ሲበር የነበረው ደግሞ ጉዞውን ከግማሽ በላይ ሸፍኖ ቼክ ሪፐብሊክ ከደረሰ በኋላ ነው እንዲመለስ የተደረገው፡፡ ምንም እንኳን የእንግሊዝ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እቀባዉን የጣለው ሁለቱ የቱርክ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች በረራ ከጀመሩ በኋላ ቢሆንም ህጉን ወዲያው ተግባራዊ በማድረግ አውሮፕላኖቹ ወደ ተነሱበት እንዲመለሱ አድርጓል፡፡ የቱርክ አየር መንገድ ለተጓዦች ሌሎች የበረራ አማራጮችን በማቅረብ ችግሩን እንደሚፈታ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡- ኢንዲፔንደንት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ማብረርን ወደላቀ ደረጃ የማድረስ ህልም ነበረው"የረዳት አብራሪው አህመድ ኑር ጓደኛ
.
.
በቅርቡ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ረዳት አብራሪ የነበረው አህመድ ኑር ፓይለት ከመሆኑ በፊት በልደታ ህንፃ ኮሌጅ በአርክቴክቸር የትምህርት ክፍለ ዘርፍ እንደተመረቀ የሚናገረው በተቋሙ ሲማር በነበረበት ወቅት የዩኒቨርስቲ ጓደኛው የነበረው ፈክሩዲን ጀማል ነው።

ከጓደኝነት በተጨማሪ በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ለሶስት አመታት ያህል በአንድ ዶርም ውስጥ አድረዋል።

አህመድ ኑርን ለመግለፅ ቃላት ያጠረው ፈክሩዲን "አህመድ ኑርን ለመግለፅ ይከብዳል። በጣም የተረጋጋ ሰው ነበር። ምንም ነገር ሲያደርግ በጣም ተረጋግቶ ነው። ትዕግስተኛ ነው" ይላል።

ፈክሩዲን እንደሚናገረው የአርክቴክቸር ትምህርት ፈታኝ ቢሆንም "አህመድ ኑር በተረጋጋ መንፈስ ነገሮችን ስለሚያከናውን ትምህርቱ እንደፈተነው መገመት ይከብዳል።" ይላል።

ለጓደኞቹ ፈጥኖ ደራሽ ነበር የሚለው የሰባት አመት በላይ ጓደኛው ፈክሩዲን "ማብረርን እንደ ጥናት ሳይሆን ወደላቀ ደረጃ የማድረስም ህልም ነበረው" ብሏል።

አብዛኛውን ጊዜም ስለበረራ ለጓደኞቹ ሲያስረዳ በአይነ ህሊናቸው እንዲታያቸው አድርጎ በጥልቀት እንደሚተነትንም ይገልፃል።

ፈክሩዲን እንደሚናገረው የአርክቴክቸር ትምህርት ፈታኝ ቢሆንም "አህመድ ኑር በተረጋጋ መንፈስ ነገሮችን ስለሚያከናውን ትምህርቱ እንደፈተነው መገመት ይከብዳል።" ይላል።

ለጓደኞቹ ፈጥኖ ደራሽ ነበር የሚለው የሰባት አመት በላይ ጓደኛው ፈክሩዲን "ማብረርን እንደ ጥናት ሳይሆን ወደላቀ ደረጃ የማድረስም ህልም ነበረው" ብሏል።

አብዛኛውን ጊዜም ስለበረራ ለጓደኞቹ ሲያስረዳ በአይነ ህሊናቸው እንዲታያቸው አድርጎ በጥልቀት እንደሚተነትንም ይገልፃል።

"በሕይወቱ አቋራጭ ነገር ሲጠቀም አይቼው አላውቅም" ሁልጊዜም በአንድ ጉዳይ ላይ የጠለቀ እውቀት እንዲኖረው ስለሚፈልግም ጊዜውን እንደሚሰጥ ይናገራል።

ልደታ ተማሪ በነበረበትም ወቅት ለማብረር ከፍተኛ ፍቅር እንደነበረው የሚናገረው ፈክሩዲን በህይወቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች አትኩሮት ሰጥቶም እንደሚከታተል ይገልፃል።

በማያጠናበት ወቅት እግር ኳስ ይጫወት የነበረ ሲሆን፤ ለቀድሞ የአማርኛ ሙዚቃዎች ለየት ያለ ፍቅር ነበረው።

"እኩል እድሜ ላይ ብንሆንም እኛ የማናውቀውን ሙዚቃ ይዘፍንና ይሄ ልጅ ግን መቸ ነው የተወለደው ያስብለን ነበር።" በማለት ፈክሩዲን ይናገራል።

ድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው የ26 አመቱ አህመድረ ኑር ወደ አዲስ አበባ የመጣውም በዩኒቨርስቲ ድልደላ በምህንድስና የትምህርት ዘርፍ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተመድቦ ነው።

ተማሪ ሳሉ አዘውትሮ ቤተሰቦቹን ሊጎበኝ ድሬዳዋ ይመላለስ እንደነበር ያስታውሳል።

ከትምህርት ቤት ተመርቆ ከወጣ በኋላና የበረራ ትምህርቱን ከጀመረም ሆነ ማብረር ከጀመረ በኋላ በተቻለ መጠን ይገናኙ እንደነበር የሚናገረው ፈክሩዲን "ገና ጎጆ መውጣቱም ስለነበር፤ አብዛኛውን ጊዜ ወደኛ ቤትም ይመጣል። ከትምህርት አለም ወደስራ መግባቱም ስለነበር ብቻውን ነበር የሚኖረው።" ብሏል።

ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከበረራው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ እለት ሲሆን የህንፃ አጨራረስ ቀለምና ጂፕሰም ላይ የሚሰራ ሌላ ጓደኛውን ከነ ፈክሩዲን ጋር ለማገናኘት ነበር።

"ቆይና ነገ ትሄዳለህ ብንለውም ነገ ወደ ኬንያ እበራለሁ ብሎን ወደ አመሻሹ 12 ሰአት ላይ ወደ ሰሚት ሊሄድ ተለያየን።" ይላል።

ከዚያም በኋላ ዜናውን የሰማው ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚሰራ ትልቅ ወንድሙ ጋር እሁድ እረፋፈዱ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን በመመልከት ላይ በነበሩበት ወቅት ነው።

ወንድሙ የአደጋውን ዜና በኢንተርኔት ሲያይ በጣም ደነገጠ መጀመሪያ ያየውም ካፕቴን ያሬድን ነው።

"ካፕቴን ያሬድን አቀዋለሁ፤ ልጅ ነው። አብሬው ሁሉ በርሬ አውቃለሁ፤ ደስ የሚል ሰው ነው ብሎ ነገረኝ" ፈክሩዲን ቀጥሎም በረራው የት ነበር ብሎ ሲጠይቀው ወንድሙም ኬንያ ብሎ መለሰለት "በጣም ብደነግጥም በረራው ጠዋት እንዳልሆነ ራሴን አሳመንኩኝ፤ እሱ አለበት የሚለውንም ላለማመን ምክንያት ለራሴ ፈለግኩኝ። በቀን የተለያዩ በረራዎች ስላሉ በሌላኛው ይሆናል አልኩኝ" የሚለው ፈክሩዲን በዛው ሳያቆምም ለማጣራት ብዙ ጥረቶችን ማድረግ ጀመረ።

በመቀጠልም ጓደኞቹ ደዋውለው የበረራ ሰዓቱ ጥዋት መሆኑን ተረዱ። በዛም መንገድ ነው አስደንጋጭ ዜናውን የሰማው።

"ያው አምላክ ያመጣውን ነገር ምን ማድረግ ይቻላል፤ ለጓደኞቹ ብዙ ነገር ነው። በጣም እንደ አባት፣ ጓደኛ ፣ ወንድም የሚያዩት ነበሩ።" በማለት በሃዘን ገልጿል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ በሃዋሳ ከተማ አብዛኛው የስራ እንቅስቃሴ ቆሞ ውሏል። በከተማዋ የስራ እንቅስቃሴ የቆመው ኢጄቶ በመባል የሚጠሩት የሲዳማ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ ከጠሩት የ3 ቀናት የስራ ማቆም አድማ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶችም ስራ አቁመዋል፡፡ ነገር ግን እንደ ጤና ተቋማት፤ የትራንስፖርትና እንዳንድ ማህበራዊ አግልግሎት መስጫ ተቋማት ግን በመደበኛ ስራቸው ላይ ይገኛሉ፡፡ ወጣቶቹ የጠሩት አድማ ዋነኛ ምክንያት ከሲዳማ ህዝብ ክልል ጥያቄ ህዝበ ዉሳኔ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia