TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ከነገ ከጥር 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ የ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለዕድለኞች ውል ማዋዋል ስራ ይጀመራል። የውል መዋዋያው " #መገናኛ " በሚገኘው በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የአንድ ማእከል አገልግሎት መስጫ ነው። በሁለቱም የቤት ልማት መርሀ-ግብር ባለድለኞች #በአካል እየተገኙ ውል እንዲዋዋሉ ማሳሰቢያ ተላልፏል። …
የ20/80 እና 40/60 ውል እንዴት እየሄደ ነው ?

" በሁለቱም የቤት ልማት ፕሮግራሞች 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን መውሰድ ችለዋል " - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

የ20/80 14ኛ ዙር እና የ40/ 60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ " በጥሩ ሁኔታ " እየተካሄደ ይገኛል ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፓሬሽኑ በ20/80 14ኛ ዙር  እና በ40/60 3ኛ ዙር የቤት ባለ እድለኞች ውል የማዋዋል ስራ  ከጥር  1/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።

" ውል ከጀመረበት ቀን ጀምሮ 7,051 ሰዎች ተመዝግበው ቅፅ 09ን በሁለቱም የቤት ልማት ኘሮግራሞች መውሰድ ችለዋል " ብሏል።

ተቋሙ ፤ " ባለ እድለኞች እንዳይጉላሉ በቂ ቦታ እና የሰው ሃይል መድቤ በማስተናገድ ላይ ነኝ " ያለ ሲሆን ውሉ ከተጀመረ ጀምሮ ለተከታታይ 60 የስራ ቀናት ብቻ ይቆያል ሲል አስታውሷል።

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መንፈቅ ዓመት 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ዛሬ አቅርቧል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈታሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት አጋማሽ 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። ኩባንያንያው ይህም የእቅዱን 96% ማሳካቱን ነው የገለጸው።

የተገኘው የገቢ ድርሻ በአገልግሎት አይነት ሲታይ ፦

- የድምጽ አገልግሎት 47.4% ድርሻ ሲኖረው

- ዳታና ኢንተርኔት 28%፣

- ዓለም አቀፍ ገቢ 8.4%፣

- እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶች የ6.5%፣

- እቃ ሽያጭ( Device) 4.3%

- የመሰረተ ልማት ማጋራት Infra.Sharing (2.2)

- ሌሎች አገልግሎቶች 3.2% ድርሻ አላቸው ተብሏል።

የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 64.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 90% ያሳካ ነው ተብላል።

ኩባንያው የደንበኞቹ ቁጥር 70 ሚሊዮን መድረሱንም ወ/ሮ ፍሬህይወት ገልጸዋል ፦

- የድምጽ አገልግሎት 67.7 ሚሊዮን

- ዳታና ኢንተርኔት 31.3 ሚሊዮን

- መደበኛ የብሮድባንድ 566.2 ሺ ተጠቃሚዎች

- መደበኛ የስልክ 862.2 ሺ ተጠቃሚዎች መድረሱን አስታውቀዋል።

በዚህም በበጀት አመቱ ግማሽ አመት 15.1  እድገት ያሳየ ሲሆን 9.2 ተጨማሪ ደንበኞችን ማግኘቱን አስታውቀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በውድድር ገቢያ ውስጥ ሆነን ደንበኞችን የማቆየትና አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገብንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthioTelecom ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መንፈቅ ዓመት 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ዛሬ አቅርቧል። የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈታሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮ ቴሌኮም በ2015…
ተጨማሪ መረጃዎች ፦

(ኢትዮ ቴሌኮም)

#DevicePenetration 📱

በኢትዮጵያ 31 ሚሊየን (46%) ዜጎች የዘመናዊ ስልክ ( SmartPhone) ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ከዚህ ውጭ ያሉ (Basic Feature Phone) ተጠቃሚዎች ደግሞ 47.5 ሚሊዮን መድረሳቸውን ነው የተገለጸው። ዳታ የሚጠቀሙ መሳሪያዎች (Data Devices) ደግሞ 1.2 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል።

#NetProfit 💶

ኢትዮ ቴሌኮም በ2022 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት መሰረት 9 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልጿል።

በያዝነው በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ሪፖርቱ መሰረት ደግሞ 8.18 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል።

ይህም በግማሽ ዓመቱ የተገኘ ትልቅ ውጤት መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።

ለዚህም ኩባንያው የያዘው የወጪ ቁጠባ ስትራቴጂ ትልቅ ድርሻ ተጫውቷል ተብሏል። በዚህም በግማሽ በጀት ዓመቱ 3.5 ቢሊዮን ብር የወጪ ቁጠባ ማድረጉን አስታውቀዋል።

#TeleBirr

የቴሌ ብር ደንበኞች 27.2 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን 217 ቢሊዮን ብር ዝውውር መፈጸሙ ነው የተጠቀሰው። ይህም ከ193 ሚሊዮን የዝውውር ብዛት (Transaction Volume) የተገኘ ነው።

ከኢንተርናሽናል ሬሚታንስ ደግሞ 1.6 ሚሊዮን ዶላር ዝውውርም የተፈጸመ ሲሆን ይህም ከ44 ሀገራት (Remitance Countries) የተገኘ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ 98.8 ኤጀንቶች፤ 372 ሱቆች፤ 18 ባንኮች፤ 25.5 ሺህ ሻጮች በመተግበሪያው ተመዝግበው እንደሚገኙ በግማሽ ዓመት ሪፖርቱ ተጠቅሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ተጨማሪ መረጃዎች ፦ (ኢትዮ ቴሌኮም) #DevicePenetration 📱 በኢትዮጵያ 31 ሚሊየን (46%) ዜጎች የዘመናዊ ስልክ ( SmartPhone) ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል። ከዚህ ውጭ ያሉ (Basic Feature Phone) ተጠቃሚዎች ደግሞ 47.5 ሚሊዮን መድረሳቸውን ነው የተገለጸው። ዳታ የሚጠቀሙ መሳሪያዎች (Data Devices) ደግሞ 1.2 ሚሊዮን መድረሱን ገልጿል።…
" ከቀናት በፊት ኔትዎርክ ተቋርጦ የነበረው #በፋይበር ላይ በደረሰ ጉዳት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም

በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ጉዳት የደረሰባቸው እንዲሁም የተጠገኑ የኔትወርክ ሳይቶች ስንት ናቸው ?

በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት ኢትዮ ቴሌኮም በግጭት በግንባታ ሥራ፤ የዓለም አቀፍ መስመሮች መቋረጥና ብልሽት፤ በተፈጥሮ አደጋ እንዲሁም በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ወደ 2,716 የሞባይል ኔትዎርክ ሳይቶቹ እንዲሁም 145 የመደበኛ ሳይቶቹ ሥራ ያቋረጡ መሆኑን ገልጿል።

እነዚህም በአብዛኛው በሰሜን እንዲሁም በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ናቸው። (🔴ከላይ በካርታው ተያይዟል)

በአንጻሩ በበጀት ዓመቱ ግማሽ ዓመት 413 የሞባይል ኔትወርክ ሳይቶች ጥገና ተደርጎላቸው ወደ አገልግሎት የገቡ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር የሚይዘው ጥገና በትግራይ ክልል በ174 ሳይቶች (28 ወረዳዎች/ከተማዎች) ወደ ላይ ተደርጎ ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ አገልግሎት በተቋረጠባቸው በ80 ወረዳዎችና ዋና ከተሞች የአገልግሎት ጥገና ተደርጎባቸዋል ተብሏል። [መሰረተ ልማቱን ለመጠገን የወጣው ወጪ እንዲሁም የደረሰው የጉዳት መጠን ከመግለጽ ተቆጥበዋል]

#FYI

- ኢትዮ ቴሌኮም፤ከሰሞኑ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ዳግም የኔትወርክ አገልግሎት ከጀመረ በኋላ ከቀናት በፊት የተቋረጠው #በፋይበር ላይ በደረሰ ጉዳት መሆኑን ገልጿል።

- በሰሜን ሪጅን (በአብዛኛው በትግራይ ክልል) ካሉ ከ700 በላይ ሰራተኞቹ ወደ 500 የሚጠጉት ዳግም ሥራ ለመጀመር አመልክተዋል ተብሏል።

- ከሰሞኑ በሰመራ የደረሰው የኔትወርክ መቆራረጥ በተወዳዳሪው [ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ] የመሰረተ ልማት ግንባታ መሆኑን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ የገለፁ ሲሆን በኩባንያው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠየቅ ጉዳዩ #በህግ_ተይዟል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ባለፈው ሳምንት የታሰሩት አራት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ሰራተኞች፤ የገንዘብ ዋስትና (የሰብዓዊ መብት ባለሞያዎቹ 4,000 ብር / የድርጅቱ አሽከርካሪ 3,000 ብር) በማስያዝ እንዲለቀቁ በፍ/ቤት ተወሰኖላቸዋል።

ውሳኔውን ያሳለፈው በኦሮሚያ ክልል የሰበታ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ሲሆን ዐቃቤ ህግ የሰራተኞቹን በዋስ መውጣት እንደማይቃወም ገልጿል።

አራቱ ሰራተኞች በፖሊስ የተያዙት፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች እየተካሄደ የነበረውን የቤት የማፍረስ ዘመቻን ለማጣራት በተሰማሩበት ወቅት እንደነበር መገለፁ አይዘነጋም።

ትላንህ በሰበታ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በነበረ ችሎት ሰራተኞቹ ፖሊስ ውንጀላ አቅርቦ ነበር።

ፖሊስ ምንድነው ያለው ?

- ከመስሪያ ቤታቸው ደብዳቤ ሳይዙ በቦታው ላይ ለምርመራ ተሰማርተዋል።

-  ከፖሊስ ፍቃድ ሳያገኙ የፖሊስ ታፔላን ፎቶ አንስተዋል።

-  በብሔር እና ብሔር መካከል ጠብን በሚቀሰቅስ መልኩ፤ ' ቤቶች እየፈረሱ ያሉት ለአንድ ብሔር የወገነ በሚመስል መንገድ ነው ' እያሉ ነበር ሲል ፖሊስ በትላንትናው የችሎት ውሎ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ፤ ፍርድ ቤት የገንዘብ ዋስ በማስያዝ እንዲፈቱ ካዘዘ በኃላ ሰራተኞቹን ፖሊስ ይፈታ ዘንድ ቀጣይ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከሰዓታት በፊት ገልጿል።

እስካሁን ግን ሰራተኞቹ ስለመፈታት አለመፈታታቸው የተሰማ ነገር የለም።

#UPDATE : ታስረው የነበሩት የኢሰመጉ ሰራተኞች ማምሻውን መፈታታቸው ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር / የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ

@tikvahethiopia
#NISS

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፤ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በማለት ኅብረተሰቡን እያጭበረበሩ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየወሰድኩ ነው አለ።

አገልግሎቱ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ የማጭበርበሪያ ስልት  የሚጠቀሙ አካላት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው ያለመከተው።

ሰሞኑን ተደርጓል ባለው ክትትል ፦

- ፈለቀ ዴብሳ ደማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፤ 

- አስፋው አዳማ ሙታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፤

- ሳምሶን ገነነ መንገሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፤

- ተስፋ ሀተው ገምቴሳ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ሰበታ ክፍለ ከተማ ፤

- ዮሰን በቀለ ትክሳ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር ቡራዩ ክፍለ ከተማ ሐሰተኛ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትን መታወቂያ ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጿል።

የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማትን ሐሰተኛ መታወቂያ በመጠቀም ለሕገወጥ ድርጊት የሚያውሉ ግለሰቦችም በጸጥታ አካላት ተይዘዋል ብሏል።

ኅብረተሰቡ " የመንግሥታዊ ተቋማት  አባል ነን " በማለት በሐሰተኛ መታወቂያ የማጭበርበር ድርጊት ለመፈጸም ከሚሞክሩ ግለሰቦች ጋር በተያያዘ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙት ፦

👉 በ910 ነፃ የስልክ መስመር እና [email protected] በሚለው የኢሜይል አድራሻ ለብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት

👉 በ816 እና 987 ነፃ የስልክ መስመር ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ መስጠት ይችላል ተብሏል።

Credit : EPA

@tikvahethiopia
#Tigray

ከሰኞ ጥር 8 ጀምሮ በትግራይ ክልል የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዳግም መሰጠት እንደሚጀምር ተሰምቷል።

ክትባቱ በክልሉ በነበረው ጦርነት እና በነዳጅ እጦት ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ተገልጿል።

የክልሉ ጤና ቢሮ እንዳለው ዳግም ክትባቱን መስጠት የሚጀምረው በክልሉ በ5 ከተሞች ሲሆን ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት እና UNICEF ጋር በመተባበር እንደሚሰጥ አመልክቷል።

ክትባቱ መሰጠት የሚጀመረው በደቡብ ዞን ማይጨው እና መኸኒ ፣ በማዕከላዊ ዞን በዓብይ ዓዲ ፣ በምስራቃዊ ዞን ውቕሮ እና ዓዲግራት ሲሆን ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ክትባቱ ከ5ቱ ከተማች በተጨማሪ ወደሌለችም ከተሞች ይሰፋል ያለው ቢሮው ነዋሪዎች ክታብቱን እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፏል።

ማህበረሰቡ ክትባቱን በተመለከተ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ራሱን በመጠበቅ ከሚመለከታቸው የጤና አካላት ብቻ ማብራሪያ እንዲወስድ ቢሮው አደራ ማለቱን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia