TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ይገለፃል ?

በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በሁለት ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀን እየጠየቁ ይገኛሉ።

በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመልዕክት መቀበያ አድራሻም እጅግ በርካታ መልዕክቶች ከውጤት ጋር ተያይዞ ከተማሪዎች እና በተማሪ ወላጆች ደርሶናል።

የፈተናው ውጤት መዘግየቱን የሚገልፁት ተማሪዎች እና ወላጆች ትምህርት ሚኒስቴር ውጤቱ መቼ ይፋ እንደሚደረግ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

" የትምህርት ዓመቱ እየገፋ ነው ፤ ገና ከውጤት በኃላ ምደባ አለ ፤ ልጆቻችን ከመደበኛ ትምህርት ርቀው ቤት ከሆኑ በርካታ ሳምንታት አልፈዋል ፤ የሁሉም ውጤት ከ2ኛ ዙር ተፈታኞች ጋር ይገለፃል ቢባልም ዛሬም ድረስ ቀኑ መቼ እንደሆነ አይታወቅም ፤ የተማሪዎችን የትምህርት ዓመት ታሳቢ በማድረግ ቀኑ ቢገለፅ " ሲሉ ወላጆች መልዕክታቸውን ልከዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ውጤት መቼ እንደሚገለፅ ለማወቅ የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችን ለማግኘት ጥረት አድርጓል።

መልዕክት የላኩልን አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አመራር ፤ ምንም እንኳን ቁርጥ ያለው የውጤት መግለጫ ቀን ባይታወቅም ነገር ግን ከጥር 15 ጀምሮ ባሉት ቀናት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ930 ሺ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#BuleHora

በኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ ጉጂ ዞን ፤ ከቡሌ ሆራ ወጣ ብሎ በሚገኝ ማረሚያ ታጣቂዎች ጥቃት ሰንዝረው ከእስር ቤት ያስመለጧቸውን ከ400 በላይ እስረኞችን መልሶ ለመያዝ አሰሳ እየተደረገ መሆኑን የአካባቢው አስተዳደር ማሳወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጥቃቱ ከአንድ ሳምንት በፊት የተፈፀመ ሲሆን ጥቃት አድራሾቹ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነ ቡድን የተፈረጀው " ሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ቡድን)  መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች መናገራቸው ተገልጿል።

ታጣቂዎቹ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በሚገኝ ማረሚያ ቤት ላይ ተኩስ ከፍተው አምስት (5) የፖሊስ አባላትን ከገደሉ በኋላ እስከ 480 የሚደርሱ እስረኞችን አስመልጠው እንደነበር በዘገባው ላይ ተገልጿል።

የቡሌ ሆራ ምክትል ከንቲባ አቶ ጊርጃ ኡራጎ ለቢቢሲ የሰጡት ቃል ፦

" ከማረሚያ ቤት ያመለጡ እስረኞችን መልሶ ለመያዝ የመንግሥት ፀጥታ ኃይል አሰሳ እያካሄደ በማሳደድ ላይ ነው።

ከእስር እንዲያመልጡ የተደረጉት የሕግ ታራሚዎች በተለያዩ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለው የቅጣት ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ የነበሩ ናቸው።

ሁሉም ታራሚዎች ናቸው የወጡት። እስከ 480 እስረኞች ይሆናሉ ብለን እንገምታለን።

አሁን ላይ በዚያ ማረሚያ ቤት ውስጥ ታስሮ የሚገኝ ትክክለኛ የታራሚ ቁጥር የለንም። ነገር ግን ያመለጡት ከ400 በላይ ይሆናሉ።

ካመለጡት መካከል የሸኔ ቡድን አባላት ይገኙበታል።

ታጣቂዎቹ ተኩስ ከከፈቱ በኋላ አምስት የማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት እና አንድ የአካባቢው ነዋሪን ገድለዋ ፤ ሁለት ሰዎችን አቁስለዋል። "

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ምክንያት ከሚኖሩበት ቦታ ተነሺ የሆኑ የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 አፍንጮ በር አካባቢ ነዋሪዎች (65 አባወራዎች) ለአመታት ሲነገረን የቆየውና ውል ከፈረምንበት የተለየ ነገር ገጥሞናል ሲሉ ያላቸውን ከፍተኛ ቅሬታ አሰምተዋል።

ነዋሪዎቹ ይህንን ቅሬታ ያቀረቡት በሸገር ሬድዮ ጣቢያ ላይ ቀርበው ነው።

ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

ለበርካታ ዓመታት ከኖሩበት ለልማት እንደሚነሱ ከተነገራቸው በኃላ (ከአራት እና አምስት ዓመት በፊት የተነገራቸው) የመንግስት ቤት የለንም ኮንዶሚኒየም ምረጡ እንደተባሉ ያስረዳሉ።

ነዋሪዎቹም ካላቸው የቤተሰብ ብዛት አንፃር ባለሶስት መኝታ ቤት ይመርጣሉ ፤ ከሰሞኑን የዕጣ ማውጣት አለ ተብሎ ተነግሯቸው ሲሄዱ የቤት እጥረት ስላለብን አንድ ክፍል ስቱዲዮ ነው ያለን ይባላሉ።

ለምን ያልሞለነው ትሉናላችሁ ? የቤተሰብ ቁጥራችውን በአንድ ክፍል የሚሆን አይደለም ብለው ሲጠይቁ ቤት የለንም የሚል ምላሽ ነው ያገኙት።

ቤታቸው በልማት መነሳቱን የማይቃወሙት ነዋሪዎቹ ሶስት መኝታ ከሞሉ በኃላ ስቱዲዮ ነው ያለው መባላቸው እጅግ እንዳሳዘናቸው እና ቤቱ ካላቸው የቤተሰብ ቁጥር አንፃር ፍፁም እንደማይሆን በመግለፅ መፍትሄ ጠይቀዋል።

አንዲት ነዋሪ ፤ " የት ይሂድ ይሄ ህዝብ ? ሀገር ማለት ህዝብ ነው፤ ባዶ መሬት ምን ሊሆን እንደሚችል አላውቅም፤ ሂዱ ሲሉ 26-30 ካሬ ማለት 6 እና 7 ቤተሰብ ያለው አለ፣ ህመም ያለባቸው አሉ፣ ድሃ አለ አራት እና አምስት ብር የቀበሌ ቤት ከፍሎ መኖር የለመደ ህብረተሰብ ፣ ቀለብ እንኳን የማይችሉ ተማሪዎች አሉ፣ ስራቸው እዛ ቤታቸው እዚህ ሆኖ በዛ ላይ 6 እና 7 ቤተሰብ ተይዞ እንዴት ነው የሚኮነው፤ ይፍረስ ቤቱ ተቃውሞ የለንም ፤ ሀገር ስትለማ የማይወድ ማንም የለም " ብለዋል።

ነዋሪዎቹ ከአንድ ሳምንት በፊት ባንቢስ ቤቶች ኤጀንሲ ሄደው ቤቱ እንዳለቀ ባለ ሶስት መኝታ እንደመረጡ፣ ከሳምንት በኃላ ሲመጡ እጣ ለማውጣት ብቻ እንደሆነ ተነግሯቸው ነበር አሁን ግን ያለው ስቱዲዮ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል።

ነዋሪዎቹ ምትክ ስቱድዮ ቤት ይሰጣቸዋል የተባለው በቦሌ ቡልቡላ ሳይት መሆኑንም አመልክተዋል።

የመንግስት አካላት ምን ይላሉ ?

የጉለሌ ክ/ከተማ የቤቶች አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ህሊና ኃይሌ ፦

" አሁን ላይ የቤት እጥረት አጋጥሞን በዛ መሰረት ያሉትን ስቶኮች አሳውቆናል ያሳወቁንን በስቱዲዮ መልክ ያሉትን አሳውቀናል ለተነሺዎች፣ ስቱዲዮ አይመጥነንም ፣ ከቤተሰባችን ስፋት አንፃር አይበቃንም ካሬው የሚባል ጥያቄ ካለ ምርጫቸውን አስተካክለው ምትክ የቀበሌ ቤት የሚያገኙበት ሁኔታ ይመቻቻል። "

ነዋሪዎቹ መጀመሪያ ላይ ሲነገረን ቀበሌ ቤት ስለሌለ ኮንዶሚኒየም ሙሉ መባላቸውን እንዳነሱና ቀድሞ ከሌለ አሁን የቀበሌ ቤት ከየት መጣ ? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ፦

" በስቶክ ደረጃ ያሉት ቤቶች አሁን የቀረቡት ናቸው። ይሄንን አማራጭ በቀረቡት ቤቶች ላይ መጠቀም የሚፈልጉ ተነሺዎች ዕድሉን ተጠቅመው የቀረቡትን ቤቶች አማራጭ ይዘው በምትክነት ይወስዳሉ።

ቀጣይ የቀበሌ ቤቱ እየተፈለገ በሚገኝበት ሰዓት ምትክ እየተሰጠ ነው የሚሄደው። የቀበሌ ቤት እጥረት አለ ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አምራጮች በራሱ የሚወስዳቸው ይኖራል ፤ እዛ በሚዘጋጁት ላይ በጊዜው ተግባራዊ ሲደረግ በሚዘጋጀው ዕድል ተጠቃሚ እየሆኑ ነው የሚሄዱት ገና ያለቀ ጉዳይ ስላልሆነ ፤ በሂደት ላይ ነው። "

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ፦

" የመልሶ ልማት ተነሺዎች በርካታ ናቸው፤ ተመርጦ ተመርጦ መጨረሻ የቀሩት ስቱዲዮዎች ናቸው ፤ ምንድነው እኛ ማለት ያለብን ያለው ይሄነው ነው፤ በተለያየ ደረጃ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ግን እኛ ያለን ይሄ ነው ብለን እውነታውን ተናግረናል።

ካለ ምን ችግር አለ፤ እንዲመጡ አንፈልግም ለምን ቅሬታ ያቀርባሉ መታቸው ነው እኮ መብታቸው የሆነ ነገር ነው ቢሮር። በአንድ ክ/ከተማ ብቻ አይደለም ልደታ አለ፣ ቂርቆስ አለ የሌሎች ፕሮጀክቶች ይሄ የወንዝ ዳር ዳርቻ ፕሮጀክት ነው ብዙ ነው የሚመጣው የመልሶ ማልማት ተነሺ ፤ አንድ የሚሰጠው ኮንዶሚኒየም ቤት ነው ፤ የመንግስቱ ስለሚነሳ ኮንዶሚኒየም ነው የሚሰጣቸው።

አናውቅም ፕሮጀክቱ አስቸኳይ ነው ምናልባት አሁን እጣ የደረሳቸው የማይዋዋሉ ካሉ Shift የማድረግ ስራ እንሰራለን አሁን ባለው ሁኔታ ያለውን ነው መረዳት ያለባቸው "

Credit : ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopia
#BelaynehKindie

ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ ያስገነቡት በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን #መገጣጠም የሚያስችል የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር ገለፁ።

ይኸው በደብረ ብርሃን ከተማ ላይ ለተገነባው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሁለት (2) ቢሊየን ብር ወጪ እዳደረጉበት ተሰምቷል።

አቶ በላይነህ ፤ " ፋብሪካው ከ3 ወር በኋላ ወደማምረት ሥራ ይገባል፡፡ " ያሉ ሲሆን " በዓመት 1ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም አለው " ብለዋል።

ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሥራ ሲገባ በዚህ ዓመት ከ250 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደሚገጣጠሙ አቶ በላይነህ ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው #ለ500 ሰዎች #የሥራ_ዕድል እንደሚፈጥር መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በዘመቻ መልክ ቤቶች እየፈረሱ ይገኛሉ። የመንግስት አካል እነዚህ ቤቶች እያፈረሰ ሚገኘው ፤  " ህገወጥ ቤቶች ናቸው " በሚል እንደሆነ ተሰምቷል። በተለያዩ አካባቢዎች በ3 ቀን ለቃችሁ ውጡ የሚል መልዕክትም መለጠፉን ተመልክተናል። ነዋሪዎች በበኩላቸው ፤ ለረጅም ያህል ጊዜ የኖሩበት ቤት እየፈረሰ መሆኑን ገለፀው ልጆቻቸው ሜዳ ላይ በመውደቃቸው መፍትሄ እንዲፈለግላቸው…
" እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ የሀገሪቱን እና የዜጎችን ወቅታ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ያላስገባ ነው " - ዶክተር እንዳለ ሀይሌ

በአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ-ወጥ ናቸዉ የተባሉ ቤቶች በዘመቻ መልክ እየፈረሱ እንደሆነ ይታወቃል።

ቃላቸውን ለአሐዱ ሬድዮ እና ቴሌቪችን የሰጡት የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዋና እንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሀይሌ ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ እና ቡራዩ አካባቢ ቤት እየፈረሰባቸዉ ያሉ በርካታ ዜጎች ወደ ተቋሙ እየመጡ ነው ብለዋል።

" ተቋማችን ህገ-ወጥነትን አያበረታታም " ያሉት ዶ/ር እናዳለ ፤ " አሁን እየተካሄደ ያለዉ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ወቅታዊ ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

" ጉዳዩን በህገ-ወጥነት መነጽር ብቻ መመልከት አግባብ አይደለም " ያሉት ዋና እንባ ጠባቂዉ " የበአል ወቅት እንደመሆኑ፤ በርካታ ተፈናቃዮች በተለያዩ ክልሎች እንደመኖራቸዉ እና ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ በዘመቻ መልክ ይህን ለመፈጸም አስቻይ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።

የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ቤት የማፍረስ ዘመቻዉን ከማካሄዳቸዉ በፊት  ጊዜዉ አስቻይ ነዉ ወይ የሚለዉን ማየት ነበረባቸዉም ብለዋል።

" ሰዎች ህገ-ወጥ አሊያም ህግን ባልተከተለ መንገድ ቤት ከገበሬ ላይ የሚገዙበትን ምክንያት የመንግስት አካላት ሊያጤኑት ይገባል " ያሉት ዋና ዳሬክተሩ " የመሬት ፖሊስን ፤በቂ የቤት አቅርቦት እና ተደራሽነት መኖር እና የቤት ሽያጭ ስረአቶች በህግ መእቀፍ ዉስጥ ያሉ ናቸዉ ወይ የሚለዉን ከግምት በማስገባት ማስተካከያዎችን መዉሰድ አለባቸዉ " ብለዋል።

Credit : AHADU RADIO & TV

@tikvahethiopia
#ግሬስ

ከሆስፒታል እንደወጡ ለማገገም የት እንደሚሄዱ ግራ ገብቶታል ? የቤትዎ አለመቸት ፣ የህክምና መሳሪያ እና ባለሙያ አለመኖር እንዲሁም ያስታማሚን ችግር ለመፍታት ወደተቋቋመው ግሬስ የህሙማን እና የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ብቅ ይበሉ።

ሁሉን ነገር ባሟላ ማገገምያ ማእከላችን ልምድ ባላቸው ዶክተር እና ነርሶቻችን ቤተሰብዎን ከሆስፒታል እንደወጡ በመንከባከብ እናግዝዎታለን ፤ በነፋሻ ግቢያችን ውስጥ 24/7 የNursing Home አገልግሎት ያገኛሉ።

አድራሻ ፦ አያት አደባባይ ወደ ለገጣፎ በሚወስደው መንገድ ላይ በቀኝ በኩል በፍሬሽ ኮርነር ገባ ብሎ 2ኛ ቅያስ ወደ ቀኝ በድጋሚ 3ኛ ቅያስ ወደ ቀኝ ታጥፈው ያገኙናል።

ለበለጠ መረጃ በ0967-03-42-42 ወይም በ0954-99-11-90 ይደውሉ።
#አቢሲንያ_ባንክ

በቅርቡ አዲስ ነገር በእጅዎ ! ከሚገምቱት በላይ ፈጣን፣ ቀላል እና ዘመናዊ ።
ዝግጁ ይሁኑ!

#Apollo #OurNewProduct #ProductLaunch
#selfie #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
TIKVAH-ETHIOPIA
#China ቻይና ከ3 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ድንበሯን #ለጎብኚዎች ከፍት አድርጋለች። ቻይና በመጋቢት 2020 ዓ/ም የኮቪድ  19 ወረርሽኝን ተከትሎ ነበር የጉዞ እግድ የጣለችው። ከአሁን በኃላ ገቢ መንገደኞች ማቆያ ስፍራ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ መግባት ይችላሉ። ይሁንና ገቢ መንገደኞች #በ48_ሰዓታት ውስጥ የወሰዱትን የክትባት ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ፅፏል። @tikvahethiopia
#Ethiopia 🛫 #China 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ #ቻይና ሳምንታዊ የበረራ ምልልሱን ከፍ ሊያደርግ ነው።

በቻይና መንግስት ተጥለው የነበሩ የኮቪድ-19 ክልከላዎች መነሳታቸውን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው የካቲት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ቻይና ወደሚገኙ መዳረሻዎቹ የሚያደርገውን ሳምንታዊ የበረራ ምልልስ ከፍ በማድረግ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር መሆኑን አየር መንገዱ ዛሬ አሳውቋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት (3) ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቡሽን ማዕከል " የልጆች ንባብ ፌስቲቫል " ተዘጋጅቷል።

በፌስቲቫሉ ላይ ለልጆች የሚሆኑ መጽሐፍቶችና የእረፍት ጊዜያቸውን በደስታ የሚያሳልፉበት መርሐግብር መዘጋጀቱን አዘጋጆቹ አሳውቀውናል።

ይኸው የንባብ ፌስቲቫል መግቢያ ያለው ሲሆን ለ3 ሰው 250 ብር ለአንድ ሰው 100 ብር መሆኑ ተገልጿል።

የቲክቫህ ቤተሰቦችም ፤ በሀገራችን በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ለተጎዱ አከባቢዎች ላሉ ትምህርት ቤቶች የሚውል  የመጽሐፍት ማሰባሰብ ዘመቻ በዚሁ ፌስቲቫል ላይ ያከናውናሉ።

ለፌስቲቫሉ የምትመጡ ቤተሰቦች ቤት ካሏችሁ መጽሐፍ መለገስ የምትችሉ ሲሆን በዕለቱ የሚገኙ ተሳታፊዎች መጽሐፍ ለመለገስ መመዝገብ ይችላሉ፤ ምዝገባውን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንታት በየቤታችሁ በመገኘት መረከብ እንችላለን።

በዚህ ልዩ የህጻናት ፌስቲቫል ላይ ከልጆት ጋር ለመሳተፍ ሲመጡ ፦
- ከ9-12 ማንኛውም መፅሀፍ፣
- ከ1-8 አጋዥ መፅሀፍ ብቻ
- ማንኛውም አይነት ያገለገሉ ኮምፒዩተሮች፣ ታብሌቶች፣ ፕሪንተር፣ የፕሪንተር ቀለም፣ ነጭ ወረቀት ማበርከት ይቻላል።

ዛሬ በይፋ የተጀመረው ፌስቲቫሉ ቅዳሜ እና እሁድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
" መረጃ ለሰጠኝ እስከ 10,000,000 ዶላር ወሮታ እከፍላለሁ " - አሜሪካ

አሜሪካ ፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን መሪ ነው ያለችው ሞሐሙድ አብዲ አደንን በተመለከተ መረጃ ለሰጣት እስከ 10,000,000 ዶላር (አስር ሚሊዮን ዶላር) / 540,000,000 ብር ወሮታ እንደምትከፍል አስታወቀች።

ሞሃሙድ እ.ኤ.አ. በ2019 አልሸባብ በኬንያ፣ ናይሮቢ ዱሲትዲ2 ሆቴል በፈፀመው እና 22 ንፁሃን ዜጎች በተገደሉበት ጥቃት ውስጥ እጁ እንዳለበት አሜሪካ ገልፃለች።

አሜሪካ ይህን ግለሰብ በተመለከተ መረጃ ለሰጣት እስከ 10,000,000 ዶላር የሚደርስ ወሮታ እከፍላለሁ ብላለች።

እ.አ.አ በ2019 አልሸባብ በጎረቤታችን ኬንያ ናይሮቢ፤ ቅንጡ ከሚባሉት ሆቴሎች አንዱ በሆነው ዱሲትዲ2 የሽብር ጥቃት ፈፅሞ 22 ንፁሃን ተገድለዋል።

ከተገደሉት መካከል አንድ የአሜሪካ ዜጋ ነበር።

በወቅቱ የአልሸባብ ቡድን ቃል አቀባይ ፤ በናይሮቢ ለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ገልፆ ነበር።

@tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia