#COVID-19
በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የኢንስቲትዩቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ አያሌው ከተናገሩት፦
- የኮሮና ቫይረስ ወደ ክልሉ እንዳይገባ ቀድሞ መከላከል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ ነው።
- የመከላከል ተግባሩን በውጤታማነት ለመምራትም ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ክልላዊ ግብረሃይልና የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።
- ከተደረጉት ዝግጅቶች መካከል በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ላሊበላና ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያዎች የምርመራና ልኬታ ስራዎችን ለማካሄድ የሚያስችል ስራ ተከናውኗል።
- በኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጨምሮ በ39 የልማት ፕሮጀክቶች አጠራጣሪ ምልክት የሚታይባቸውን ሰዎች ተለይተው የሚቆይባቸውን ካምፖች ተዘጋጅተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል።
- የምርምራ ስራውን የሚያካሄዱ ባለሙያዎችን በመመልመል የማሰልጠን ፣ ቁሳቀስ የማቅረብና የማቆያ ቦታዎችን የመለየት ስራ እየተካሄደ ይገኛል።
- በኢንስቲትዩቱ ስር የሚገኘው የወረርሽኝ ማስተባበሪያ ማዕከል አስፈላጊውን ግብዓት ተሟልቶለት ስራውን እንዲጀምር ተደርጓል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ሁሉም የጉንፋን ምልክቶች የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምልክቶች ናቸው?
የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካል የሚያጠቃ ቫይረስ ከመሆኑ አንፃር ምልክቶቹ የጉንፋን አይነት ምልክቶች ማለትም ትኩሳት፣ ሳል፣ ቶሎ ቶሎ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ መብዛት ይገኙበታል። ምንም እንኳን የበሽታው ምልክት ከጉንፋን ምልክቶች ጋር ተመሳሳይነት ቢኖረውም ግን ሁሉም ጉንፋን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አይመጣም።
የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ምልክቶች ከጉንፋን ምልክቶች የሚለየው የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች በተጨማሪ መኖሩ ሲሆን ጉንፋን ምልክት በቶሎ የሚያታይና በአጭር ቀናት የማገገም ሁኔታ ሲታይ የኮሮና ቫይረስ እየተባባሰ የሚሄድ ምልክቶችን ያሳያል።

#SHARE #ሼር
የአለም ስጋት ከሆነው የኮሮና ቫይረስ #COVID19 እራሳችንን ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ ቀላልና ውጤታማ እርምጃዎች፥
- አዘውትሮ በአግባቡ እጅን በሳሙና መታጠብ
- ለሰላምታ በእጅ አለመጨባበጥ
- ፊትን በእጅ አለመንካት
- ትኩሳት፣ ሳል፣ ማስነጠስ ያሉ ምልክቶች ካጋጠሙን የአፍ መሸፈኛ ማስክ ማድረግ
- በሚያስነጥሱ እና በሚያስሉ ጊዜ ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ሌሎችን እንዳይበክሉ መጠንቀቅ
ስለ ኮሮና ቫይረስ መረጃ ለማግኘት በነጻ የስልክ መስመር 8335 ይደውሉ ወይም 0112765340 #COVID-19 update free call 8335 or [email protected]
#ጤናሚኒስቴር

ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ከመሄዶ በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ይገንዘቡ፦
- ለአንድ ታካሚ አንድ አስታማሚ ብቻ ነው መግባት የሚፈቀደው
- አሁን ያለውን የ#COVID-19 ስርጭትን ለመግታት ማንኛውንም ታካሚዎች ባሉበት ሆነው በስልክ ብቻ ለመጠየቅ ይሞክሩ
- ለድንገተኛ ህክምና እና የሀኪም ቀጠሮ ከሌላቹ በስተቀር ወደ ሆስፒታላችን ባለመምጣት ከ#COVID-19 ስርጭት እራሶን እና ቤተሰቦን ይጠብቁ
- እድሜያችሁ ከ 40 አመት በላይ ሆኖ ተላላፊ ያልሆነ ህክምና (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ልብ ፣ ኩላሊት) ክትትል ያላችሁ በቀጠሮ ቀን የእርሶ ጤና አስችኳይ ሕመም ከሌሎት መድሀኒቱን የሚወስድሎት ወጣት ሰው ከቀጠሮ ካርድ ጋር አብረው እየላኩ ያለቀቦትን መድሀኒት ያሉበት ሆነው እዲወስድሎት ያድርጉ
- መግቢያ በሮች ላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች አድርጉ የሚሏችሁን በአግባቡ ተግባራዊ አድርጉ (እጅን መታጠብ፤ የሙቀት ልየታ፤ ርቀትን ጠብቆ መሰለፍ . . .)
- በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፎን እና አፍንጫዎን በክንዶ ወይም መሀረብ/ሶፍት ይሽፍኑ
- አገልግሎት ለማግኘት በሚቆዩበት ጊዜ፤ ሰልፍ እና ወረፋ ሲጠብቁ ርቀቶን ቢያንስ በ1 ሜትር ይጠብቁ
[ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል]

#COVID_ORGANIC
ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ መፍትሄ ነው ብላ COV/COVID ORGANIC ተሰኘ ባህላዊ መድሃኒት አስተዋውቃለች!
በተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። የክትባት ሙከራዎች እየተካሄዱ እንዳለ ይታወቃል።
ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዓለምን ለፈተነ ወረርሽኝ መፍትሄ ይሆናል ፣ ሰዎችንም ከጭንቀት ይገላግላል ያለችውን መፍትሄ ይዛ ለመቅረብ የተለያዩ የምርምር ስራዎች እየሰራች እንደሆነ መግለጿ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
አሁን ደግሞ የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና ሀገራቸው (በIMRA በኩል) ለኮሮና ቫይረስ በሽታ ፍቱን የሆነ ባህላዊ መድሀኒት አግኝተናል ሲሉ በይፋ አሳውቀዋል። የመጀመሪያው የክሊኒካል ፍተሻ አመርቂ ውጤት አምጥቷልም ብለዋል።
ፕሬዘዳንቱ ባህላዊ መድሃኒቱ ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ታማሚዎች ብቻ ሳይሆን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይያዙም የማድረግ አቅም አለው ሲሉ ነው የተናገሩት። መክፈል ለማይችሉ ሰዎች በነፃ ይሰጣል፤ ለሌሎች ደግሞ በቅናሽ ይቀርባል ሲሉም ተደምጠዋል።
በማዳጋስካር የዚህ ባህላዊ መድሃኒት መገኘት ይፋ በተደረገበት ስነ ስርዓት ላይ የቻይና እና የደቡብ ኮሪያ አምባሳደሮች ተገኝተው እንደነበር የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
እስካሁን ድረስ በማዳጋስካር 121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 39 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፤ ምንም ሞት አልተመዘገበም።
በአሁን ሰዓት በዓለም ጤና ድርጅት የተረጋገጠ ምንም አይነት የኮሮና ቫይረስ በሽታን የሚፈውስ መድሃኒት የለም።
PHOTO : ከማዳጋስካር ፕሬዘዳንት የትዊተር ገፅ

TIKVAH-ETHIOPIA
#COVID_ORGANIC ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ መፍትሄ ነው ብላ COV/COVID ORGANIC ተሰኘ ባህላዊ መድሃኒት አስተዋውቃለች! በተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። የክትባት ሙከራዎች እየተካሄዱ እንዳለ ይታወቃል። ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዓለምን ለፈተነ ወረርሽኝ መፍትሄ ይሆናል ፣ ሰዎችንም ከጭንቀት ይገላግላል ያለችውን መፍትሄ…
#COVID_ORGANICS
በማዳጋስካሩ ፕሬዚደንት አንድሪ ራጆሊና የተዋወቀው እና 'የኮሮና ቫይረስ ፈውስ ነው' ለተባለው ባህላዊ መድሃኒት ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ ነው፡፡
'ባህላዊ መድሃኒቱ' ከኮቪድ-19 እንደሚያድን የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊ መረጃ እንደሌለ ቢነገርም ፍላጎታቸው አልተገታም' ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
'መድሃኒቱን' ካዘዙት መካከልም መድሃኒቱን ለማምጣት ወደ ደሴቷ አገር አውሮፕላን የላኩት የታንዛኒያው ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ ይገኙበታል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ኮንጎ ብራዛቪል ፣ ኮንጎ ፣ ጋቦን እና ኮሞሮስ መድሃኒቱን ወደ አገራቸው የማስገባት ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡ ኢኳቶሪያን ጊኒ እና ጊኒ ቢሳዎም የተወሰኑ መድሃኒቶችን ለማምጣት አውሮፕላን ልከዋል - #BBC

#Attention😷
በዶ/ር ሠኢድ መሐመድ (የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት) ፦
የኮቪድ-19 ታማሚዎች እና የፅኑ ህሙማን መጠን የህዝቡን መዘናጋት በሚመጥን መልኩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ከአቅም በላይ የሆነ የኦክስጅን እጥረት ስለተከሰተ፣ ባሳለፍነው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ በርካታ ሆስፒታሎች ከክልል ከተሞች ኦክስጅን በአይሱዙ እያስጫኑ ለማምጣት ተገደዋል። አሁን ግን የክልል ከተሞችም ኦክስጅን እጥረት እያጋጠማቸው ነው።
ለምሳሌ ትላንት ሲዳማ ክልል ውስጥ ያሉ የመተንፈሻ ማሽኖች ሙሉ በሙሉ በኮቪድ ታማሚዎች በመያዛቸው ምክንያት ተጨማሪ ታማሚ ቢመጣ ምንም እርዳታ መስጠት እንደማይችሉ አሳውቀዋል። ሌሎች ክልሎች ውስጥ ተመሳሳይ ችግር እያጋጠመ እንደሆነ ተሰምቷል።
በዚህም ምክንያት ሠሞኑን የቀዶ ህክምና ስንሠራ ሠርጀሪው ተራዝሞ ኦክስጂን ያጥረን ይሆን? እያልን እየተሳቀቅን ነበር።
ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ደግሞ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉ በርካታ ሆስፒታሎች ከድንገተኛ ህክምና ውጪ ያሉ የቀዶ ህክምናዎችን መስራት ያቆማሉ።
ኮቪድ-19 የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሠጥቶን ሳንቀበለው በመቅረታችን የተፈራው መከሠት ጀምሯል።
አሁን ያለው የስርጭት ብዛት እና ከተለያዩ ሐገራት አንፃር ከፍተኛ የሚባለው በበሽታው የመያዝ ምጣኔ ትምህርት ቤቶችን ፣ አላስፈላጊ ስብሰባዎችን እና የዕምነት ተቋማትን በከፊል ወይም በሙሉ ለመዝጋት የሚያስገድድ ደረጃ ላይ የደረሰ ይመስለኛል። የጭፈራ ቤቶች ፣ ሲኒማ ቤቶች ፣ ጫት ማስቃሚያ ቤቶች ለህዝቡ ህልውና ሲባል በአፋጣኝ መዘጋት አለባቸው። ከዚህ በፊት የነበረው ጥንቃቄ የቱን ያህል በሽታውን ባለበት ለማስቆም ረድቶን እንደነበረ ማስታወስ ያስፈልጋል።
በተለይም በቀን አምስት ጊዜ በርካታ ህዝብ የሚሠባሰብባቸው መስጊዶች፣ ሠጋጆቻቸው ማስክ እንዲያደርጉ ፣ ተራርቀው እንዲቆሙ እና በተቻለ መጠን አየር በደምብ የሚገኝበት ስፍራ፣ ማለትም ግቢ ውስጥ ወይም ከበር ውጪ እንዲሠግዱ በማድረግ የጥንቃቄያቸውን መጠን እስከመጨረሻው ጥግ እንዲያሳድጉ ማሳሰብ ያስፈልጋል።
አብያተ ክርስቲያናትም የፀሎት ስነስርአቶቻቸውን ሲያከናውኑ የመጨረሻ (maximum) ጥንቃቄ ሊያደርጉ የሚገባበት ጊዜ አሁን ነው።
#No_Oxygen
#ኢትዮጵያ
#ኮቪድ19
#covid_is_real!
@tikvahethiopia