#COVID_ORGANIC
ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ መፍትሄ ነው ብላ COV/COVID ORGANIC ተሰኘ ባህላዊ መድሃኒት አስተዋውቃለች!
በተለያዩ ሀገራት ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ በሽታ መድሃኒት ለማግኘት ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ። የክትባት ሙከራዎች እየተካሄዱ እንዳለ ይታወቃል።
ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዚህ ዓለምን ለፈተነ ወረርሽኝ መፍትሄ ይሆናል ፣ ሰዎችንም ከጭንቀት ይገላግላል ያለችውን መፍትሄ ይዛ ለመቅረብ የተለያዩ የምርምር ስራዎች እየሰራች እንደሆነ መግለጿ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
አሁን ደግሞ የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና ሀገራቸው (በIMRA በኩል) ለኮሮና ቫይረስ በሽታ ፍቱን የሆነ ባህላዊ መድሀኒት አግኝተናል ሲሉ በይፋ አሳውቀዋል። የመጀመሪያው የክሊኒካል ፍተሻ አመርቂ ውጤት አምጥቷልም ብለዋል።
ፕሬዘዳንቱ ባህላዊ መድሃኒቱ ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ታማሚዎች ብቻ ሳይሆን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንዳይያዙም የማድረግ አቅም አለው ሲሉ ነው የተናገሩት። መክፈል ለማይችሉ ሰዎች በነፃ ይሰጣል፤ ለሌሎች ደግሞ በቅናሽ ይቀርባል ሲሉም ተደምጠዋል።
በማዳጋስካር የዚህ ባህላዊ መድሃኒት መገኘት ይፋ በተደረገበት ስነ ስርዓት ላይ የቻይና እና የደቡብ ኮሪያ አምባሳደሮች ተገኝተው እንደነበር የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
እስካሁን ድረስ በማዳጋስካር 121 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን 39 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል፤ ምንም ሞት አልተመዘገበም።
በአሁን ሰዓት በዓለም ጤና ድርጅት የተረጋገጠ ምንም አይነት የኮሮና ቫይረስ በሽታን የሚፈውስ መድሃኒት የለም።
PHOTO : ከማዳጋስካር ፕሬዘዳንት የትዊተር ገፅ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia