TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ለኢ/ር ታከለ ኡማ በህጻናትና እናቶች በመደገፍ በኩል ላበረከቱት አስተዋጽኦ ስጦታ አበረከተ፡፡ ማህበሩ 7ኛውን መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡

የሴቶች ማህበሩ ኢ/ር ታከለ ኡማና የከተማ አስተዳደሩ በተያዘው አመት በስፋት የተጀመረው የተማሪዎች የምገባ መርሀግብር የመሪነት ሚና በመጫወታቸው ፤እንዲሁም የተማሪዎችን የመማሪያ ቁሳቁስና ዩኒፎርም አቅርቦት ላይ የከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ተግባር በማህበሩ አድናቆት ተችሮታል፡፡

ከዘህ በተጨማሪም በክረምቱ የአረጋውያንን ቤት በማደስ ከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ተግባር የሚመሰገንና መቀጠልም ያለበት ነው ተበሏል፡፡ ለእነዚህና የከተማ አስተዳደሩ ሴቶችና ሀጻናትን በሚመለከት ላከናወናቸው ተግባራት ምስጋና መገለጫ የሚሆን የ"ካባ" ስጦታ ለኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ -- የከተማ አስተዳደሩ ለሴቶችና ህጻናት የሚሰጠው ትኩረት ቀጣይነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው"ለሴቶች ፣ህጻናትና አረጋውያን የማትመች ከተማን መፍጠር አንፈልግም " ብለዋል፡፡

(EPA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞሞና ኤፍ ኤም ተመረቀ!

የመቐለ ዩኒቨርሰቲ ማሕበረሰብ ተኮር ማሕበረሰብ ሬዲዮ ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ህዳር 06/2012 ዓ/ም የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ከንድያ ገ/ህይውት፣ ው/ሮ ሊያ ካሳ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ውንድውስን አንዱሃለም የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ አካላት በተገኙበት ተመርቆ መደበኛ ስርጭቱን የጀመረ ሲሆን ከናሕሴ 09/2011 ዓ/ም ጀምሮ በሙከራ ስርጭት ላይ ቆይቷል።

More👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-18

(ሞሞና ኤፍ ኤም ~ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ህዳር 06/2012 ዓ/ም የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ከንድያ ገ/ህይወት፣ ወ/ሮ ሊያ ካሳ የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ወንድወስን አንዱሃለም የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ አካላት በተገኙበት ተመርቆ መደበኛ ስርጭቱን ጀምሯል።

(ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራንና ለተማሪዎች ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ!

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 8/2012 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት እንደሌለ ምንጩ ያልተረጋገጠ መልዕክት በመተላለፉ ምክንያት አንደንድ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንደወጡ ተረድቻለሁ ብሏል።

ነገር ግን ጉዳዩ ከዩኒቨርሲቲው ዕውቅና ውጭ ስለሆነና በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ የተፈጠረ ምንም አይነት ችግር ባለመኖሩ የተለመደው መማር ማስተማር ሂደት እንደሚቀጥል ገልጿን። ህዳር 10/2012 ዓ ምርጫ ቦርድ በተላለፈለት መልዕክት መሰረት ትምህርት የማይኖር መሆኑን አሳውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት መግለጫ፦

ከሰሞኑ በተለያዩ የአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተከሰቱት አሳዛኝ ክስተቶች ተማሪዎች ላይ የሞት፣ የአካል እና ስነልቦናዊ ጉዳት መድረሱ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህም የተነሳ የመማር ማስተማር ሂደቱ ተስተጓጉሏል፡፡ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረዉን ሁኔታ ለማረጋጋት እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታን ለመፍጠር እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ ቆይቷል እያደረገም ይገኛል፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሴኔትም ጉዳዩን በተመለከተ ዛሬ በቀን 8/03/2012 ዓ. ም ባካሄደዉ ስብሰባ የክስተቱን ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመ ሲሆን፣ ከሁሉ አስቀድሞ በዩኒቨርሲቲው የተከሰተ የሞት አደጋ ባይኖርም እንደ አገር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያጋጠመው የተማሪዎች ህልፈተ-ህይወት ሰብአዊነትን ያልተላበሰ በመሆኑ ሴኔቱ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያወግዘውና ህይወታቸው ላለፉት ተማሪዎችም የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል፡፡

ሴኔቱ ጅማ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች ከጉዳታቸዉ በፍጥነት አገግመዉ ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመለሱ ያለዉን ከልብ የመነጨ ምኞቱን ገልጿል፡፡ በደረሰው ጉዳትም ላይ ከየትኛውም ወገን የተሳተፉ አካላት ላይ በማስረጃ የተደገፈ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት በማሳሰብ ከስጋት ነጻ የሆነ የመማር ማስተማር ሁኔታ መፍጠር ላይ መወሰድ ስላለባቸዉ እርምጃዎች አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

More👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-18-2

@tikvahethiopia
#SEMERA

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የሰመራ ሎግያ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጤና ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ማህሙዳ ኢብራሂም እንደተናገሩት በከተማው የኮሌራ በሽታ የተከሰተው ከጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ነው።

እስካሁን ድረስም በበሽታው 26 ሰዎች ሲያዙ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን ተናግረዋል። በሰመራ ጤና ጣቢያ ጊዜያዊ የሕክምና ማዕከል ተዘጋጅቶ በበሽታው ለተያዙ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ኃላፊው አመልክተዋል።


(ENA)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዛሬም በዩኒቨርሲቲው ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክሮ ውሳኔ አስተላልፏል፦

የወልዲያ ዩኒቨርሲቲውን ክስተት ተከትሎ በመቱ ዩኒቨርሲቲም የታየው አለመረጋጋትና ትምህርት ማቋረጥን ተከትሎ የመቱ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ህዳር2/2012 ዓ. ም ተሰብስቦ ችግሩን የሚፈታበትን አቅጣጫ በመወሰን ስንቀሳቀስ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ እስካሁን በተሰራው ስራ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስና የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ማድረግ ቢቻልም መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር ባለመቻሉ ሴኔቱ ዛሬ ህዳር 8/2012 ዓ.ም ተገናኝቶ የተሰሩ ስራዎችን ከገመገመ በኋላ የሚከተሉ ውሳኔዎችን አስተላልፈዋል፡፡

1. ከዶርም ወጥተው በአደራሽ ተጠልለው ያሉ ተማሪዎች ወደተዘጋጀላቸው መኝታ ክፍል (ዶርም) እንዲገቡ፤

2. ተማሪዎች ዳግም ምዝገባ (Reregistration) እንዲያከሄዱ እና

3. መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የዳግም ምዝገባ አካሄደው ከህዳር 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርታቸውን እንድጀምሩ የወሰነ ሲሆን ይህን ለማስፈጸም የተለያዩ ንዑስ ኮሚቴዎችን አዋቅሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሳኒ ሬዲ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ችግሩን ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ምክክር እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

(መቱ ዩኒቨርሲቲ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH

ውድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆናችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ያለምንም እረፍት የናተን ጉዳይ በመከታተል፣ ድምፃችሁን ለማሰማት፣ ጥያቄያችሁን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሳቸው በማድረግ አብረናችሁ ነን፤ በየመማሪያ ክፍል ውስጥ ከምታድሩት ጋር አለን፣

በየቤተ እምነቱ ከተጠለላችሁት ጋርም አለን፣ ሜዳ ላይ ከሆናችሁትም ጋር አለ፤ ወደፊትም ችግራችሁ ሙሉ በሙሉ ተፈቶ፤ መፍትሄ እስኪሰጣችሁ፤ በሰላም መማር እስክትጀምሩ ድረስ ድምፃችሁ ሆነን እንቆያለን። እያንዳዷን አለ የምትሉትን ችግር ማሳወቅ ትችላላችሁ።

ዩኒቨርሲቲያችን በግቢ ውስጥ እየሆነ ስላለ ጉዳይ ደብቆታል የምትሉት ጉዳይ ካለ "በማስረጃ ብቻ" አስደግፋችሁ አሳውቁን ይፋ እናደርጋለን። ከዛ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ ይምታገኙትን መረጃ ሁሉ ብታቀብሉን ደጋግመን ስለምናጣራው እና ስለምንመረምረው ልንቀበላችሁ አንችልም።

እጅግ እናከብራችኃለን!

@tikvahethiopiaBot👈ሀሳቦቻችሁን መቀበያ!
ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ 2.3 ሚሊዮን ህዝብ መመዝገቡን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ!

ለሲዳማ በክልልነት መደራጀት ጥያቄ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔ ሁለት ሚሊዮን ሥስት መቶ ሺህ ገደማ ድምፅ ሰጪዎች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። ከነገ በስቲያ ረቡዕ ለሚደረገው ሕዝበ ውሳኔ ለድምፅ መስጫነት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች በሲዳማ ዞን ወዳሉ አካባቢዎች ዛሬ መሰራጨት ጀምረዋል።

ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከጥቅምት 27 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት የተከናወነው የድምፅ ሰጪዎች ምዝገባ የተጠናቀቀው «ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው» ብሏል። ቦርዱ የድምፅ ሰጪዎችን ምዝገባ ያከናወነው በ1,692 ጣቢያዎች መሆኑን ገልጾ ሆኖም ከፍተኛ የተመዝጋቢ ቁጥር በታየባቸው ቦታዎች ላይ ተጨማሪ 175 ጣቢያዎችን ለድምፅ መስጪያው ቀን እንደሚያዘጋጅ ጠቁሟል።

(DW)
@tsegabwloldw @tikvahethiopia
#ህዳር10

በሲዳማ ዞን ረቡዕ ለሚካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ 10 ሺህ በጎ ፍቃደኞች፣ 15 ሺህ ሚሊሻ፣ ከ2500 -3000 ፖሊስ ፣ ከ250 -300 የሚጠጋ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚሰማሩ የሀዋሳና የሲዳማ ዞን አስተዳር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

በሕዝበ ውሳኔው ድምፅ ከተሰጠም ሆነ ውጤት ከተገለጸ በኋላ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል፤ረቡዕ የጫት ገበያ በሁሉም የሲዳማ ዞን ተከልክሏል፤ ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት-ዓርብ ጠዋት በሐዋሳ ሞተር ብስክሌቶች ታግደዋል።

(እሸት በቀለ~ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DTU
 
የደብረ ታቦር ከተማ አገር ሽማግሌዎች፣ እና ከከተማው የተውጣጡ የማህበረሰብ አካላት  በዩኒቨርስቲው የሚገኙ የኦሮሞ ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ካፍቴሪያ በመገኘት እራት አስመገቡ።

(DTU - ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ብልፅግና ፓርቲ” የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርብ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ!

-- የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ3ኛ ቀን ውሎው ብልፅግና ፓርቲ የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርብ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከስምምነት ላይ መድረሱን የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ አስታውቀዋል፡፡

የፓርቲው የስራ ቋንቋን በተመለከተም አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ፣ ትግርኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች ለስራ ቋንቋነት የተመረጡ ሲሆን ፓርቲው በአገሪቱ ለሚገኙ ቋንቋዎች በሙሉ እውቅና መስጠቱም ተገልጿል፡፡

የፓርቲው አደረጃጀትን በተመለከተ ጠቅላላ ጉባኤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚኖረው ሲሆን ፓርቲው በፕሬዝዳንት እና በምክትል ፕሬዝዳንቶች ይመራልም ተብሏል፡፡ በክልሎችም የክልል ስያሜዎችን እንደያዘ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ይኖራል ተብሏል፡፡ በውህድ ፓርቲው ላይም ከስምምነት የደረሰው ፓርቲው ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ውይይት አጠናቋል፡፡

ፓርቲው በሀገሪቱ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ሌሎች ፓርቲዎች የምርጫ የፓርቲ ምዝገባን ሥነ ምግባር እንደሚከተልም አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ3ኛው ቀን ውሎው በፓርቲው ረቂቅ ህገደንብ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የውሳኔ ሀሳቦቹ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርቡ መስኗል፡፡

(EBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል!

ግርማቸው ጌትነት የተባለ የአንደኛ አመት ተማሪ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሞተ ተብሎ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብሏል ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ። ተማሪው በ1ኛ ዙር የሀገር መከላከያ ሠራዊትነት ምልመላ በቦንጋ ከተማ ኮታ በፍቃደኝነት ተመልምሎ የሄደ መሆኑን የደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግስት የካፋ ዞን ሚሊሻ ፅ/ቤት አስታውቋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ግርማቸው ጌትነት በብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ማዕከል በመኮንነት ሙያ አልፎ ማሰልጠኛ ማዕከል የገባ መሆኑን ከካፋ ዞን ሚሊሻ ፅ/ቤት ደብዳቤ ለመረዳት ችሏል። በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን መደበኛ የመማር ማስተማሩ ስራም እጅግ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉ ተነግሮናል።

(ደብዳቤው የተላከልን - ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ነው)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ያረጋል አይሸሹም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ያረጋል አይሸሹም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አቶ ያረጋል ክልሉን የመጀመሪያው ርዕሰ መስተዳድር በመሆን አገልግለዋል። አቶ ያረጋል የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርም ሆነው አገልግለዋል።

ምንጭ ፦ኢዜአ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AIW (Africa Industrialisation Week)

18-22 November 2019,Addis Abeba, Ethiopia

(Africa youth Union Commission)

PHOTO: Aamanuel Eticha(Tikvah Family)

@tsegabwolde @tikvahethiopia