#UPDATE - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዛሬው ዕለት መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ በአዲስ አበባ የተካሄደው 19ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር በሠላም መጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዐብይ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ሊወያዩ ነው!
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግንባሩን በማዋሃድ ወጥ ፓርቲ ለመመስረት በቀረበለት የውህደት ዝርዝር ጥናት ላይ ተወያይቶ በስድስት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ከስምምነት ላይ መድረሱን ይታወቃል። በስብሰባው ላይ ከተሳተፉት የግንባሩ አባል ድርጅቶች መካከል የቀረበውን ሃሳብ ተቃውመው ድምጽ የሰጡት የህወሓት አባላት ሲሆኑ ከቀድሞው የደህንነት ተቋም ኃላፊ ከአቶ ጌታቸው አሰፋ በስተቀር የህወሓት አባላት መሳተፋቸውን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባል አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ውሳኔው በተሰጠበት ጊዜ ስድስት ብቻ መቃወማቸው ድምጽ በሚሰጥበት ወቅት ከተሳታፊዎች መካከል "መውጣትና መግባት" ስለነበረ በአጋጣሚ የተፈጠረ መሆኑን አቶ አስመላሽ ገልጸው በውይይቱ ሁሉም እንደተሳተፉና "በፓርቲያቸው አቋም ጸንተው መውጣታቸውን" ገልጸዋል። በዚህ ወሳኝ ድምጽ በሚሰጥበት ጊዜ ሁለቱ አባላት ያለመገኘታቸው አጠያያቂ ቢሆንም አቶ ስመላሽ በጉዳየ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።
የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የድርጅቱ ውህደትን በሚመለከቱ ቀጣይ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ዛሬም ስብሰባውን የቀጠለ ሲሆን ውህደትን በተመለከተ የቀረበውን ሃሳብ የተቃወሙት የህወሓት አባላት ግን በዛሬው ስብሰባ ላይ እንደማይሳተፉ አቶ አስመላሽ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ከህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለጻቸው ከእርሳቸው ጋር እንደሚነጋገሩ አቶ አስመላሽ ጠቁመዋል።
More👇
https://telegra.ph/BBC-11-17
(BBC)
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከበረራ የታገደው ቦይንግ 737 ማክስ ስሪት አውሮፕላኖች ለመቀበል ከውሳኔ አለመድረሱን አቶ ተወልደ ገብረማርያም ተናገሩ። በዱባይ በመካሔድ ላይ በሚገኘው "የአውሮፕላን አምራቾች አውደ ርዕይ" በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ በቦይንግ 737 ማክስ ስሪት አውሮፕላኖች የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር እና በሥልጠና ላይ አምራቹ እያደረገ ያለው ማሻሻያ “ገና በሒደት ላይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። አቶ ተወልደ ማሻሻያው “ተጠናቆ ልናየው ይገባል። ተጨማሪ የሙከራ በረራዎች ውጤቶች ገና ወደፊት የሚታዩ ናቸው” ብለዋል።
(DW)

አርባምንጭ ከተማን አለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ጥረት እየተካሄደ ነው!
በሆቴልና ሪዞርት ኢንቨሰትመንት የተሰማሩ አለም አቀፍ ባለሀብቶች ወደ ሀገር ቤት ለማምጣት ያለመ ከፌደራል: ከክልል: ከጋሞ ዞን እና ከአ/ምንጭ ከተማ የተውጣጣ ቡድን የሥራ ጉብኝት (learning visit) በሲሸልስ አካሂዷል።
በፕሮግራሙ የተወከሉ የሥራ ሀላፊዎች ኢንቨስተሮች ለመሳብ በክልሉ እና በከተማው ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶችንና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስረዳት በመንግስት በኩል አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ ለማድረግ ያለውን ዝግጅት አረጋግጠዋል። ከባለሀብቶቹ ጋር በተደረገ ውይይትም ዝግጁነታቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

የአጼ ቴዎድሮስ መታሰቢያ ሃውልት ተመረቀ!
በትውልድ ቀያቸው ቋራ ወረዳ ገለጉ ከተማ የተገነባው የአጼ ቴዎድሮስ መታሰቢያ ሃውልት ዛሬ ተመረቀ። ከሶስት ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተገነባው የመታሰቢያ ሀውልቱ ሲመረቅ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደባባይ ሙሉጌታ በምረቃው ስነስርዓት ወቅት እንደተናገሩት የመታሰቢያ ሐውልቱ የተገነባው አጼ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ አንድነት ያደረጉትን አስተዋፅኦ ሁሉም ዜጋ ተገንዝቦ እርስ በርስ ከመጋጨት በመቆጠብ የሀገሩን አንድነት እንዲጠብቅ በማሰብ ነው ብለዋል።
(ENA)
@tikvahethioiaBot @tikvahethiopia

የዛሬ የተማሪዎቻችን ሁኔታ...
የቲክቫህ ቤተሰቦች የሆኑ ተማሪዎች ያሉበትን የዛሬ ሁኔታ አሳውቀውናል። ተማሪዎቹ የመንግስትን ቸልተኝነት፣ የዩኒቨርሲቲዎችን ችግርን እቅልሎ ማቅረብ፣ ተነግሮ መፍትሄ በሚፈለግላቸው ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን የመደበቅ እንቅስቃሴ እጅጉን ኮንነዋል። አሁንም በወንድማማቾች እና እህትማማቾች መሃል የገቡት ጥቂት ሰዎች ናቸው ለይቶ እርምጃ ካልተወሰደና ለሌላውም መማሪያ ካልተደረገ ተመሳሳይ ችግሮች መቀጠላቸው አይቀሬ ነው ብለዋል። ዛሬም ሚዲያዎች በአንድ በኩል የተማሪውን ድምፅ እያሰሙ በሌላ ቦታ ያለውን ችግር ድምፅ እያፈኑ፣ ሌሎች ለጥፋት እንዲነሳሱ በማድረግ ትልቅ ችግር እየፈጠሩ እንደሆነ ገልፀዋል። ሚዲያዎች በሚሰሩት ስራ የማይጠየቁ ከሆነ ሀገሪቱ ሌላ ትልቅ ችግር ውስጥ እንደምትውድቅ ተናግረዋል።
የማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚነዛው አሉባልታ እና ሀሰተኛ መረጃ ለችግሮች መባባስ ዋነኛው ነው የሚሉት ተማሪዎቹ የሰው ህይወት ያላለፈበትን ቦታ የሰው ህይወት እንዳለፈ አድርጎ የሀሰት ወሬ በማሰራጨት ሌላ ቦታ የሚገኙ ተማሪዎችን ለተጨማሪ ችግር እያጋለጡ ነው ብለዋል። ከሰሞኑን ያየነው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እጅጉን የሚያሳፍር ነው ያሉት የቲክቫህ ቤተሰብ አባላቶች በተማሪዎች ስቃይ ቁማይ ባይጫወቱ መልካም ነው ሲሉ መክረዋል። አስታራቂ ሃሳብ ሳይሆን ብሶትን እየቀሰቀሱ ተማሪዎችን ለእልቂት እያነሳሱ ያሉ ግለሰቦች፣ የቴሌቪዥን ጠቢያዎች፣ የፌስቡክ ገፆች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አስጠንቅቀዋል።
የዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ(ከቲክቫህ ቤተሰቦች)👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-17

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በውህድ ፓርቲው ረቂቅ ፕሮግራም ላይ ተወያይቶ ረቂቁን ለኢህአዴግ ምክር ቤት መራ!
የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በዛሬ ውሎው በወደፊቱ ውህድ ፓርቲ ፕሮግራም (ማኒፌስቶ) ላይ ዝርዝር ውይይት እና ክርክር በማካሄድ ረቂቁ ወደፊት ለሚካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ እንዲቀርብ መወሰኑን የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ፍቃዱ ተሰማ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ስብሰባ በነገው ዕለትም የሚቀጥል ሲሆን ኮሚቴው በነገው ውሎው ለወደፊቱ ውህድ ፓርቲ በተዘጋጀው ረቂቅ ሕገ-ደንብ ላይ እንደሚመክር አቶ ፍቃዱ ገልፀዋል፡፡
የዛሬውን ውሎ አስመልክቶም የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፈዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባስተላለፉት መልዕክት በሚዋሃደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል።
በፓርቲ ፕሮግራሙ ላይ በመወያየት መፅደቁን በመግለፅ አዲሱ ፓርቲ የኢትዮጵያን የፌደራል ሥርዓት እና ዴሞክራሲን ያጠናክራል፤ አካታች ሆኖ ብዝኃነታችንን ያከብራል፤ ኅብረ ብሔራዊነትን ያከበረ አንድነትን መሠረት ያደርጋልም ብለዋል በመልዕክታቸው።
(EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ...
"ትላንት ካደረግነው የፓርቲ ውሕደት ወሳኝ ውይይት በመቀጠል ዛሬም በሚዋሐደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ተመካክረናል። በፓርቲ ፕሮግራሙ ላይ ተወያይተን ማጽደቃችንን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ትላንት ካደረግነው የፓርቲ ውሕደት ወሳኝ ውይይት በመቀጠል ዛሬም በሚዋሐደዉ ፓርቲ ቁልፍ የፕሮግራም አቅጣጫዎች ዙሪያ ተመካክረናል። በፓርቲ ፕሮግራሙ ላይ ተወያይተን ማጽደቃችንን ሳበሥር በታላቅ ደስታ ነው።" ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WolloUniversity
ወሎ ዩኒቨርሲቲ(ደሴ ካምፓስ) የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ዛሬ ከተማሪ ተወካዮች ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተነግሮናል። አብዛኛው ተማሪ ትምህርት ፈላጊ ነው፤ ዛሬ ውይይት ከተደረገ በኃላ ነገ ትምህርት ይጀምራል የሚል ተስፋ አድሮብናል ብሎናል አንድ የወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ተወካይ። በሌላ በኩል አሁንም ስጋታቸው ሙሉ በሙሉ እንዳተቀረፈ፤ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እንደሚፈልጉ መልዕክቶቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ገልፀዋል።
በተመሳሳይ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒስቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎቹ ተመልሰው ትምህርታቸው እንዲማሩ ድጋሜ ማስታወቂያ ቢያወጣም በማህበራዊ ሚዲያዎች ውስጥ ለውስጥ የሚሰራስጩ የማስፈራሪያ መልዕክቶች ስጋት አጭረውብናል ብለዋል የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ተማሪዎች። ዩኒቨርሲቲው እንዲህ ያሉ ነገሮችን እንዲቆጣጠር አሳስበዋል።
በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት ትምህርት የተቋረጠባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየሰሩ እንደሆነ እየገለፁልን ይገኛሉ። በአንፃሩ ችግር ላይ ነን የሚሉ ተማሪዎች ድምፃችን ይሰማ፤ ወደቤተሰቦቻችን፣ ወደ እናትና አባታችን በሰላም መልሱን እያሉ ይገኛሉ።
የዩኒቨርሲቲ ሁኔታዎች(07/03/2012)👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-17
አዳዲስ ጉዳዮች ሲኖሩ እናሳውቃለን!
@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia

#ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶና የእስልምና ኃይማኖቶች ሰባኪያን፣ መምህራንና ምሁራን ግጭቶችን በትብብር ለመፍታት የሚያስችል ውይይት አደረጉ። ውይይቶቹ መሬት ላይ ወርደው አንዱ እምነት ለአንዱ ደጀን በመሆን ችግሮችን ለመፍታት እስከ ወረዳ ድረስ ተደራሽ እንደሚሆን አስታውቀዋል።
‘የኃይማኖቶች ትብብርና የጋራ መድረክ ለሕዝቦች ሰላምና አንድነት’ በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው የውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጴጥሮሳዊያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረትና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የተዘጋጀ ነው።
ውይይቱን አስመልክተውም የጴጥሮሳዊያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና መብት አስጠባቂ ኅብረት ሰብሳቢ ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑና የሙሰሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አገሪቷ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ግጭቶች እየተባባሱና ኃይማኖታዊ መልክ እየያዙ በመምጣታቸው፣ ከየትኛውም ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ውጭ አማኙ ማኅበረሰብ ውስጥ የማይጠበቁ ጥፋቶች መከሰታቸውን ተከትሎ ግጭቶችን በጋራ ለመፍታት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

TIKVAH-ETHIOPIA
የዶክተር ቦጋለች ገብሬ ቀብር'ን በተመለከተ፦ ለሁሉም የመገናኛ ብዙሃን እና ጉዳዩ ለሚመለከታችሁ አካላት በሙሉ፤ በየጊዜው እንደምታደርገው በሀገር ቤት ለምታከናውናቸው የበጎ አድራጎት ስራዎች ድጋፍ ለማሰባሰብና በዚያዉም ለህክምና ወደ አሜሪካ ሎስ አንጀለስ ከተማ እንደተጓዘች፣ በድንገትና ባልተጠበቀ ሁኔታ ጥቅምት 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷ የሚታወቅ ነው። የዶህተር ቦጋለች…
የዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አስክሬን ኢትዮጵያ ደርሷል!
በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አስክሬን ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፥ የብሔራዊ ዕርቅ እና ሰላም ኮሚሽን አባላት፥ ታዋቂ ግለሰቦች፥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን፥ የኃይማኖት አባቶች፥ ወዳጅ ዘመድ፥ የሥራ ባልደረቦቻቸው አቀባበል አድርገውለታል።
(ከምባታ ጠምባሮ ዞን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አስክሬን ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፥ የብሔራዊ ዕርቅ እና ሰላም ኮሚሽን አባላት፥ ታዋቂ ግለሰቦች፥ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን፥ የኃይማኖት አባቶች፥ ወዳጅ ዘመድ፥ የሥራ ባልደረቦቻቸው አቀባበል አድርገውለታል።
(ከምባታ ጠምባሮ ዞን)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE
የዶክተር ቦጋለች ገብሬ(ቦጌ)አስክሬን ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፥ በታዋቂ ግለሰቦች፥ በብሔራዊ የዕርቅ እና ሰላም ኮሚሽን አባላት፥ በቤተሰቦቿ እና በከምባታ ጠምባሮ ዞን ተወካዮች አቀባበል ተደርጎለታል።
የሴቶች መብት ተሟጋቿ እና ተመራማሪዋ ዶክተር ቦጋለች ገብሬ( ቦጌ) አስክሬን ግብዓተ መሬት ወደ ሚፈፀምበት ወደ ከምባታ ጠምባሮ ዞን መዲና ዱራሜ አሸኛኘት እየተደረገለት ነው። በብሔራዊ የእርቅ እና ሰላም ኮሚሽን ኮሚሽነር ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል ቡራኬ ተደርጎለት ጉዞ ወደ ዱራሜ ተጀምሯል።

#DTU - በአሁን ሰአት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከአገረ ሽማግሌዎች እና ከህይማኖት አባቶች እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር እየተወያዩ እንደሚገኙ ገልፀውልናል።
@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
#DTU - የደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲው የስራ አመራር ሀላፊዎች፣ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንቶች፣ ከአገረ ሽማግሌዎች፣ ከህይማኖት አባቶች እና ከከተማው ከተውጣጡ የማህበረሰብ አካላት ጋር እየተወያዩ ነው።
(ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ)
ፎቶ: ደብረ ታቦር ቲክቫህ ቤተሰቦች
@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot
(ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ)
ፎቶ: ደብረ ታቦር ቲክቫህ ቤተሰቦች
@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot
በቦሌ ኤርፖርት 12,064,000 ብር የሚያወጣ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ!
መነሻውን ከብራዚል ሳኦፖሎ ያደረገ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 507 በቀን 07/03/2012 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በዓለም አቀፍ መንገኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በጉምሩክ ኢንተሊጀንስ ሰራተኞችና በኢንተር ፖል አባል እንዲሁም በሰዓቱ ከነበረ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።
በሰዓቱም አደንዛዥ ዕፁን ሲያዘዋውር የነበረው ግለሰብ ባራቱንደ ሞጆድ የፓስፖርት ቁጥሩ 505538358 የሆነ አሜሪካዊ ቀጣይ የጉሾ መዳረሻውም ህንድ የነበረ ግለሰብ በሻንጣው ውስጥ ሻግ በመስራት 5.2 ኪሎ ግራም በገንዘብ 12,064,000 ብር የሚገመት ኮኬይን እንደያዘ በቁጥጥር ስር ውሏል።
አደንዛዥ ፅፁና አዘዋዋሪው መንገደኛምም በቁጥጥር ስር የዋለው WCO-REGIONAL intelligence LIASON OFFICE (RILO)- EASTERN AND SOUTHERN AFRICA REGIONAL OFFICE በደረሰ መረጃና በተደረገ ክትትል ነው።
ህገ ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ ስራ የአገርን ሉዓላዊነት ለአደጋ የሚያጋልጥ፤ የማህበረሰቡን ማህበራዊ ህይወት የሚያቃዉስና የተረጋጋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር የሚያደርግ በመሆኑ ህዝቡ እንደዚህ አይነት ህገ ወጦች ሲያጋጥሙ የሚደርገዉን ጥቆማ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት የገቢዎች ሚኒስቴር አሳስቧል፡፡
(የገቢዎች ሚኒስቴር)

"ውሸት ነው! የታወከ ስብሰባ የለም!" ወይዘሪት ሶልያና ሽመልስ
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
"በሃዋሳ ከተማ ለሲቪክ ማህበራት ሊሰጥ የነበረ ስልጠና በተደራጁ ወጣቶች ለአንድ ሰዓት ያክል ተረበሸ" እየተባለ ስለሚሰራጨው መረጃ የኢትዮጵየ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን አማካሪን ወ/ሪት ሶልያና ሽመልስን የጠየቅን ሲሆን ኃላፊዋ "ውሸት ነው! የታወከ ስብሰባ የለም!" የሚል ምላሻቸውን ሰጥተውናል።
በተጨማሪም የስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጉዳዩን በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ እንደተመለከቱ ገልፀውልን "ሀሰተኛ መረጃ" ነው ብለዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ራሳችሁን #ከሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠብቁ በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን!

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፦
•ህዳር 3 ረቡዕ ምሽት ለሃሙስ አጥቢያ በተማሪዎች መካከል በደሴ ግቢ ብቻ ግጭት ተፈጥሮ ነበር።
• ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ክሊኒክና በደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸው ተመልሰዋል።
• ሁለት ተማሪዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ስለነበር በሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል ሲደረግላቸው የነበር ቢሆንም የአንድኛው ተማሪ ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። ሁለተኛው ተማሪ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል።
• የተማሪውን አሟሟትና የጉዳት ሁኔታ ለማጣራትና ተጨማሪ የአስክሬን ምርመራ ለማድረግ ወደ አዲስ አበባ ተወስዷል።
• ዩኒቨርሲቲው የተማሪውን ህይወት ለማትረፍ ለተደረገው ርብርብ የህክምና ባለሞያዎችን አመስግኗል።
• የሟች ተማሪ ወንድም ከፍተኛ ሀዘን ላይ ቢሆንም የወንድሙን ህይወት ለማትረፍ ለተደረገው ከፍተኛ ርብርብ ምስጋና አቅርቧል።
• ከደሴ ግቢ ውጪ ኮምቦልቻ ምንም አይነት ችግር የለም። የመማር ማስተማሩ ሂደት እጅግ ሰላማዊ ነው።
(ወሎ ዩኒቨርሲቲ)

አምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ትምህርት እንዲጀምሩ አሳሰበ!
አምቦ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር በዩኒቨርሲቲውም በአብዛኛው የትምህርት ፕሮግራም ተቋርጦ እንደነበር አስታውሷል። ከፀጥታ ችግሩ ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዳይስፋፋ ዩኒቨርሲቲው ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ እንደነበር ጠቅሶ በሁን ሰዓት ግን በሁሉም ካምፓሶች ትምህርት የሚያስቋርጥ አንዳችም ምክንያት ባለመኖሩ ተማሪዎች ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ እስከ እሮብ ድረስ ምዝገባ አከናውነው ትምህርት እንዲጀምሩ አሳስቧል።

#አስቸኳይ
"ከእስታይሽ ወደ ወልዲያ በሚወስደው መንገድ አንድ መኪና መንገድ ስቶ ገደል ውስጥ ገብቶ አደገኛ አደጋ ደርሷል። የሚመለከተው አካል አውቆ አፋጣኝ እርዳታ እንዲያደርግ እንጠይቃለን። በአካባቢው አምቡላስ የለም!!" - በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች