TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ህዳር10

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን ለመወሰን በሚደረገው የህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጫ ቀን ስራም ሆነ ትምህርት እንደማይኖር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። በውሳኔው መሰረትም ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ዞን የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመጪው ረቡዕ ህዳር 10 ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።

(DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ህዳር10

በሲዳማ ዞን ረቡዕ ለሚካሔደው ሕዝበ-ውሳኔ 10 ሺህ በጎ ፍቃደኞች፣ 15 ሺህ ሚሊሻ፣ ከ2500 -3000 ፖሊስ ፣ ከ250 -300 የሚጠጋ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚሰማሩ የሀዋሳና የሲዳማ ዞን አስተዳር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊዎች ገልጸዋል።

በሕዝበ ውሳኔው ድምፅ ከተሰጠም ሆነ ውጤት ከተገለጸ በኋላ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ተከልክሏል፤ረቡዕ የጫት ገበያ በሁሉም የሲዳማ ዞን ተከልክሏል፤ ማክሰኞ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት-ዓርብ ጠዋት በሐዋሳ ሞተር ብስክሌቶች ታግደዋል።

(እሸት በቀለ~ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia