TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ፌስቡክ በርካታ በማይናማር የሚገኙ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ!

ፌስቡክ በትክክለኛ ማንነት አልተከፈቱም ያላቸውን 216 የሚሆኑ በማይናማር የሚገኙ የፌስቡክ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ፡፡ 89 የሚሆኑ የግል አካውቶች፣ 107 ገፆች፣ 15 የፌስቡክ ቡድኖችና 5 የኢንስታግራም አካውንቶችን መዝጋቱን ነው ኩባንያው ያስታወቀው፡፡

የተዘጉት አንዳንድ የፌስቡክ ገጾች ከወታደራዊ አካላት ጋር የተያያዙና ህዝባዊ ውይይትን የሚያዛቡ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ከጥላቻ ንግግር በተለይም ሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ የማይናማር ወታደራዊ ሓላፊ አካውንትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አካውንቶችን መዘጋታቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ/ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ኢዜማን ልከስ ነው! Via የጀርመን ራድዮ @tsegabwolde @tikvahethiopia
''ኢዜማ ያለምንም ህጋዊ መሰረት ንብረቶቻችንን እየተጠቀመ ስለሆነ ሊመልስልን ይገባል''- #ኢዴፓ

''በህገወጥ መንገድ የያዝሁት ምንም ንብረት የለም'' - ኢዜማ
.
.
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ከኢዴፓ አፈንግጠው በወጡ አራት አባላት የተሰጠውን የፓርቲው ንብረቶች ያለምንም ህጋዊ መሰረት እየተጠቀመ ስለሆነ ሊመልስልን ይገባል ሲል ኢዴፓ ጥሪ አቅርቧል፤ ኢዜማ በበኩሉ በህገወጥ መንገድ የያዝሁት ምንም ንብረት የለም ብሏል፡፡

ከኢዴፓ አፈንግጠው የወጡ አራት ግለሰቦች በምርጫ ቦርድ ፍፁም ህገወጥ የሆነ ትብብር የፓርቲውን ፅህፈት ቤቶች፣ በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ፣ መዛግብትና ማህተም ያለአግባብ በህገወጥ መንገድ እንዲረከቡ ተደርጓል ያለው ኢዴፓ ግለሰቦቹ ኢዴፓ ከግንቦት 7 ጋር እንዲዋሀድ የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብስቦ እንደወሰነ አድርገው የሀሰት መረጃ በማቅረብ ንብረቶቹን በፓርቲዎች ውህደት ሳይሆን በግለሰቦች ስብስብ ለተቋቋመው ኢዜማ ማስረከባቸውን የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

#ኢዜማም ያለምንም ህጋዊ መሰረት እነዚህን የኢዴፓ ንብረቶች እየተጠቀመባቸው እንደሚገኝ የጠቀሰው ማእከላዊ ኮሚቴው በዚህ የተነሳ የእለት ከእለት ስራዎችን በአግባቡ ለማከናወን መቸገሩን ገልፆ ኢዜማ ግለሰቦቹ የፈፀሙትን #የማጭበርበር ወንጀል ተረድቶ ንብረቶችን እንዲመልስ ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-23

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የቀድሞውን የጦር አበጋዝ እና የመንግሥት ሚኒስትር የነበሩትን ግለሰብ የሞቃዲሾ ከንቲባ እና የባዲር ግዛት አስተዳደሪ አድርገው ሾሙ። ሹመቱ ባለፈው ወር ውስጥ በአጥፍቶ ጠፊዎች ህይወታቸው ያለፈውን የቀድሞ ከንቲባ አብዱረህማን ኦማር ኦስማንን ለመተካት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via #BBC/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአገሪቱ ከሚያስገነባቸው 6 እስር ቤቶች መካከል ይኸ በድሬዳዋ የሚገኝ ነው። እስከ 6 ሺሕ ታራሚዎች ይይዛል የተባለው እስር ቤት በሚቀጥለው አመት ሥራ ይጀምራል ተብሏል። ያዩት እንደሚሉት VIP ክፍሎች ጭምር አለው።

Via እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና በክልል ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቀዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!

በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። መዝገቡን በሚገባ በመመርመር ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ ስለሚያስፈልግ በማለት የባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለነሃሴ 21/ 2011 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የተጠርጣሪዎች #ጠበቆች ከምርመራ ሂደቱ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት የሌላቸው የባንክ ደብተርና አልባሳት እንዲመለሱላቸዉ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

የምርመራ ቡድኑም አልባሳትም ሆነ የባንክ ደብተር ለተጠርጣሪዎች ቢመለስላቸው እንደማይቃወም ገልጿል፤ ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሂሳብ ደብተር ላይ ያለው ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ይቻላል ብሏል። ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎቹና ቤተሰቦቻቸው ሌላ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ከሌላቸው የባንክ ደብተሩ እንዲሁም አልባሳቱም በህግ አግባብ ሊሰጣቸው ይገባል በሚል ወስኗል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ የምክር ቤቱ ምስረታ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ አባገዳዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ያስገነባው ት/ቤት ተመረቀ!

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የቀድሞውን የዳስ ትምህርት ቤት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አስገንብቶ አስመርቋል። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ፃግብጂ ወረዳ ላይ ያስገነባውን ገልኩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሁን አስመርቋል፡፡

ስያሜውም ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተብሏል፡፡ ትምህርት ቤቱ ሁለት #ብሎኮች እና ስምንት የመማሪያ ክፍሎች አሉት፡፡ ኃይሌ በሦስት ወራት አስገንብቶ ነው ትምህርት ቤቱን ለመጭው የትምህርት ዘመን ማስተማሪያ ዝግጁ ያደረገው፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ እንደተገለጸው ነዋሪነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አንድ ግለሰብ 8 ሽህ 500 የማጣቀሻ መጻህፍትን ለትምህርት ቤቱ ማበርከታቸው ታውቋል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwplde @tikvahethiopia
ታንዛኒያዊው ጋዜጠኛ በ'ሀሰተኛ ዜና' ታሰረ!

ታንዛኒያዊው ጋዜጠኛ 'ፖሊስ በእስር ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ያሰቃያል' በሚል የሰራው ዘገባ 'ሀሰተኛ ነው' በሚል ለእስር መዳረጉ ተገለፀ። ጋዜጠኛ ጆሴፍ በታንዛኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥምረት በተቋቋመው ዋቴቴዚ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው የሚሰራው።

የቴሌቪዥን ጣቢያው የጋዜጠኛውን መታሰር አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን በትዊተር ገፁ ላይ ጋዜጠኛው በዚህ ወር መጀመሪያ ሪፖርቱን አጠናቅሮበት ወደነበረው ኢሪንጋ መወሰዱን አስታውቋል። ጣቢያው እንዳለው ከሆነ የኢሪንጋ ፖሊስ የተሰራውን ዘገባ አስመልክቶ " ሀሰተኛና አሳሳች ሪፖርት ሲሆን የታንዛኒያን የፖሊስ ኃይል እና መንግሥትን የሚያጣጥል ነው" ሲል ማስጠንቀቂያ አዘል ምላሽ ሰጥተዋል።

"ለደህንነት ኃላፊው አሳሳችና ሀሰተኛ ዜና የሚያሰራጩ ሰዎችን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ፤ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላም ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል " ማለታቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው የአካባቢውን ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል። ከአንድ ወር በፊት በዚያው ታንዛኒያ ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛው ኤሪክ ካቤንደራ ለእስር ተዳርጎ ነበር።

ጋዜጠኛው በእስር ላይ ሳለ በተፈፀመበት የሰብዓዊ መብት ጥሰትም በአገሪቷ የሚገኙ የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎችን ትኩረት ስቦ ነበር። ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ በቅፅል ስማቸው 'ዘ ቡልዶዘር' በአውሮፓዊያኑ 2015 ሥልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ለሚዲያና የሚዲያ ባለሙያዎች ፈታኝ እንደሆነባቸው ይነገራል። ጋዜጦች እና የራዲዮ ጣቢያዎችም ሕግ ጥሰዋል በሚል ሰበብ መታገዳቸው ተጠቅሷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የበጎ አድራጎት ሳምንት ለተሳተፉ በጎ አድራጊዎች ምስጋናውን አቅርቧል። #JimmaUni

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታን አስመልክቶ ስለ ክልሉ የትምህርት ስርዓት የሰጡት መግለጫ፦

#10MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

#Emebet_Mekonen / #ሻደይ / #ሶለል #አሸንዳዬ - #ETHIOPIA #AMHARA

ኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ያላት ሀገር ናት!

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው!! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን !

#14MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን አደረሰን!

Eden Gebreselassie, Trhas Tareke and Rahel Haile - #Ashenda | #ኣሸንዳ #ETHIOPIA #TIGRAY

ኢትዮጵያ ድንቅ ባህል ያላት ሀገር ናት!

ኢትዮጵያን መውደድ የሚገለፀው እርስ በእርስ በመከባበር ነው ፤ ህዝቦቿን በማፍቀር ነው ፤ ባህሎቿን በመንከባከብ ለመጪው ትውልድ በማስተላለፍ ነው !! ሁላችንም ሀገራችን ባሏት ተነግረው በማያልቁ ድንቅ ባህሎች እና ትውፊቶች #ልንኮራ ይገባናል። አሁን ያለነው ትውልድም ኢትዮጵያንና ባህሎቿን ሳንበርዝ ለመጭው ትውልድ የማውረስ ኃላፊነት አለብን።

እንኳን አደረሰን!

#14MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጎባ ወረዳ የተሽከርካሪ አደጋ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ!

በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ሁለት ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው ባደረሱት አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቭዥን ባለሙያ ኮማንደር ናስር ኡመር እንዳሉት አደጋው የደረሰው የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3- 80852 ኢት የሆነ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ተመሳሳይ ከሆነ የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-84695 ኢት ተሽከርካሪ ጋር ትናንት ቀን 10 ሰዓት አካባቢ  በጎባ ወረዳ ሲንጃ የተባለ ስፍራ እርስ በርስ በመጋጨታቸው ነው። ተሽከርካሪዎቹ የተጋጩት ከጎባ ከተማ ወደ ሮቤ  አሸዋ ጭነው በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነው።

በአደጋው ህይወቱ ካለፈው  ሌላ ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች በጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። የሟቹ አስክሬን ቤተሰቦች እንዲረከቡ ተደርጓል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ያመለከቱት ኮማንደሩ ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እየጣለ ያለው ዝናብና ጉም ምክንያት እይታን እንደሚጋርድ በመገንዘብ  አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮሌራ በሽታ ተቀሰቀሰ!

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በምትገኘው የሻሸመኔ ወረዳ የኮሌራ በሽታ መቀስቀሱ ተሰማ። አንድ የወረዳው ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት የስራ ሃላፊ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ እንደገለፁት ወረርሽኙ ከባለፈው ስምንት መጀመሪያ አንስቶ የታየውና የተቀሰቀሰው በወረዳው ቶጋ፣ ቢሊቻ ፣ ጩሉሌ እና ቄሬሳ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው።

በአሁኑ ወቅት በበሽታው የተጠቁ ስድስት ሰዎች ወደ ጤና ተቋማት ተወስደው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የወረዳው የጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሀመድ ገመዴ ተናግረዋል።

አስከአሁን በወረርሽኙ ከተጠቁት ስድስት ሰዎች በስተቀር የሞት አደጋ #አለመድረሱን የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ገልጸዋል። ፅህፈት ቤቱ የበሽታው ስርጭት እንዳይስፋፋ ለማድረግ በአካባቢው በሚሰራጩ የራዲዮ ጣቢያዎች አማካኝነት ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የጥንቃቄ መልዕክቶችን እያስተላለፈ ይገኛል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከአርቲስቶች ጋር ችግኝ ተከሉ!

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከኢትዮጵያዊያን አርቲስቶች ጋር በብሔራዊ ቤተ መንግስት ግቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል፡፡

አርቲስቶቹ በመላው የሀገሪቱ ክልሎች ተንቀሳቅሰው ህዝቡን በማነሳሳት ችግኝ ተከላው ከታቀደው በላይ እንዲከናወን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ፕሬዚዳንቷ አመስግነዋዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደርጋል፡፡ በስብሰባው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ብቻ ለልብ ቀዶ-ጥገና ሰባት ሺህ ህፃናት ተራ እየጠበቁ ነው ተባለ!

በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ለልብ ቀዶ-ጥገና ህክምና ሰባት ሺህ ህፃናት ተራ እየጠበቁ መሆኑን ማዕከሉ አስታወቀ፡፡ በተለያዩ ሆስፒታሎች እና በየክፍለ-ሀገራቱ ያሉት ደግሞ ከዚህ በላይ ይሆናሉም ተብሏል።

የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር እና የልብ ሕሙማን ሕፃናት ስፔሽያሊስት የሆኑት ዶ/ር ሔለን በፈቃዱ፣ የሠለጠኑ ባለሙያዎች እና ዋና ዋና መሣሪያዎችም ማዕከሉ ውስጥ እያሉ በገንዘብ እጥረት ምክንያት አስፈላጊ የሆኑ አላቂ መድኃኒቶችን ማሟላት አለመቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ መሥራት ከሚችለው የቀዶ-ህክምና ሥራ ከአንድ ሦስተኛው በታች ብቻ እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ይህን መሰል ቀዶ-ጥገና የሚሠራ ሌላ የግል ሆስፒታል ባለመኖሩም መክፈል የሚችሉት እንኳን ሕክምናውን ማግኘት አይችሉም፤ በተለይ ደግሞ መክፈል ለማይችሉ ብዙኃኑ ተስፋቸው በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ብቻ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-23-2
"አንድ ብር ለአንድ ልብ" 6710

እንደTIKVAH-ETH ቤተሰብ ድጋፋችን ተጠናክሮ ቀጥሏል!

የቤተሰባችን አባላት፦

•በሀገራቸው ስም
•በባለቤታቸው ስም
•በልጆቻቸው ስም
•በፍቅረኛቸው ስም
•በሚወዷቸው ታዋቂ ሰዎች ስም
•በአባባሎች ... 6710 ላይ እንደ ዜጋ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ነው። እርሶስ?

በትንሹ 3 መልዕክት ይላኩ!

ወደዚህ ግሩብ ግቡና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ፤ ሀገር አለን የምንለው ለዚህ ነው። ሁሌም ለበጎ ስራ አብረን ስለቆምን!!

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://yangx.top/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ
#update ዩናይትድ ኪንግደም ለኢትዮጵያ 4.23 ቢሊዮን ብር (120 ሚሊዮን ፓውንድ) እርዳታ መስጠቷን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የእርዳታ ስምምነቱን የገንዘብ ምኒስትር ድኤታው አድማሱ ነበበና የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ልማት ምኒስትር አሎክ ሻርማ ፈርመውታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia