TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ቦይንግ ኩባንያ ለቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ዩኒቶች ያለባቸውን ችግር በቀጣዮቹ ቀናት ለመፍታት የሚረዳ አዲስ ሶፍትዌር ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ፡፡ አዲሱ ሶፍትዌር የአውሮፕላን የቀዘፋ ስርአት የሚቆጣጠረውን አሰራር የሚገድብም ነው ተብሏል፡፡ አዲሱ ሶፍትዌር በተጨማሪ ቦይንግ በአብራሪዎች ክፍል የማስጠንቀቂያ ስርዓት ላይ ለውጥ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን የበረራ ባለሙያዎች የሚሰለጥኑበት ሰነድ ወቅቱን የጠበቀ እና በኮምፒውተር የታገዘ እንዲሆን ይደረጋል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያዊያን የአውሮፕላን አደጋ መርማሪዎች በፈርንሳዊያን ባለሙያዎች ያስገለበጡትን የበረራ ክፍል መቅረጸ ድምጽ መረጃ ይዘው ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ከተከሰከሰው ቦይንግ አውሮፕላን 737 ማክስ 8 ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው እና የበረራ ተቆጣጣሪ አሕመድ ኑር ሞሐመድ #በአማርኛ ያደረጉትን የመረጃ ልውውጥ ያዳመጡት ኢትዮጵያዊያኑ መርማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡ የመረጃ ልውውጡ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምትክ አልባ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ አዲሱ የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር አውሮፕላኑ ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ አፍንጫውን ወደ ታች አዘቅዝቆ እንዲከሰከስ እንዳደረገው የዘርፉ ባለሙያዎች ያምናሉ፡፡

Via ሮይተርስ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በዛሬው እለት በቀን 10/07/2011 በኦሮምያ ክልል በጉቢቹ ወረዳ ሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም የጨፌ ዶንሳ ነዋሪዎች እና ከተለያያ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው 25 የሚሆን ጀነራሎች ባይንግ 737 max 8 በወደቀበት ስፍራ በማቅናትጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የተሰማቸውን ሃዘን ገልፅዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው ሁሉ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ስለማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ያስተላለፉት መልዕክት::

Via PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኳታር ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአስፓየር ዞን ፋውንዴሽን ከዋና ሥራ አስፈጻሚው #መሐመድ_ኸሊፋ_አል_ሱዋዲ ጋር ታይተዋል። ይኸ ተቋም የቅንጡ ስፖርታዊ ውድድሮች ማካሔጃዎች ባለቤት ነው። ከስፓርት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ይሰራል። ለተጎዱ አትሌቶች ሕክምናና የማገገሚያ አገልግሎትም ያቀርባል። ጠቅላይ ምኒስትሩ ወደ ኳታር ሲያቀኑ ከዚህ ማዕከል ጋር በተያያዘ ሥራ ይኖራቸው እንደሁ የታወቀ ነገር የለም።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አትናገር፤ ተናገር ካሉህ ግን እውነቱን ብቻ ተናገር!" ቢኒ

ጌዴዎ እንደወረት ሰሞኑን በጌዴዎ ተፈናቅለው ለምግብ እጥረት፣ አካላዊ ህመም እና ስነ ልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ለሞት ተዳርገው የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያው እያየን ፣ ሀዘን በወለደው ስሜታዊ መነሳሳት ሁሉም በተቻለው ሁሉ ድምጹን በማሰማት አስተጋብቷል። ጉዳዩ ከመንግስት አይን እና ጆሮ እርቆ በሀገር ውስጥ የተደረገ እስከማይመስል ድረስ ትኩረትን አጥቶ ነበር። ከማህበራዊ ሚዲያው ጩኸት ብዛት ትኩረት ያገኘ እና የተፈታ መስሎ ፡ የአንድ ሰሞን ወሬ ሆኖ አልፏል።

‘‘ማን ያውራ የነበረ፡ማን ያርዳ’’ የቀበረ ነውና ፡በቦታው ተገኝተን ሁኔታውን ለመመልከት ችለናል። ያየነውን እንናገራለን፣ በምስል ያስቀረነውን እናጋራለን፣ ስላለው ችግር በድጋሚ እንጮሃለን።

"አትናገር፤ ተናገር ካሉህ ግን እውነቱን ብቻ ተናገር!" ቢኒ

ጌዴዎ ከአዲስ አበባ 365 ኪ.ሜ. ወደ ደቡብ ፣ ከሀዋሳ ደግሞ 96 ኪ.ሜ. ላይ የሚገኝ ዞን ሲሆን ፣ በውስጥ መፈናቀል ምክናያት የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት አደጋ ላይ የወደቀባቸውን ገደብ እና ጎቲት ለመጎብኘት ችለናል።

በቦታው በርካታ ህጻናት በምግብ እጥረት ምክንያት የጎድን አጥንታቸው ወጥቶ ፣ ሆዳቸው ተነፍቶ እና እግራቸው አብጦ ላየ ፣አንጀትን የሚበላ አሳዛኝ ክስተት ይረዳዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተያያዥ የህክምና ችግሮች ተመልክተናል።

እነርሱም የቆዳ እከክ በሽታ፣ የአይን ማዝ በሽታ እንዲሁም ተቅማጥ ዋናዎቹ ናቸው።

ለመርዳት በምናረገው ጥረት የመድሐኒት እጥረትም ነበር።

ለምሳሌ ORS, BBL, Permethrin, Zink, omeprazole, Augmentin, እና Azithromycine እጥረት ነበር።
ውሃ ለእኛ እንካን ምግብ አልበላንም ነበር ለምን ... ከበደን ሰው አይደለን...
ከአዲስ አበባ፣ሀዋሳና ዲላ ከተማ ከመጡ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና ጤና ባለሙያዎች ጋር በመሆን የምንችለውን ያህል ለመርዳት ሞክረናል።

ሰውን መርዳትን የመሰለ ነገር የለም እና ድካምን እና ምቾት ማጣትን ሳንቆጥር እርዳታ ለማድረግ ሞክረናል።

ለማሳሰብ የምንፈልገው ነገር ግን ፣ ይህ ችግር ቀላል እንዳልሆነና በቂ ትኩረት እንደሚሻ ነው።

ጥቆማ
 ብዙ ሚልየኖች በስማቸው ቢሰበሰብም፣ በጊዜ ደርሶ ህይወታቸውን ካልታደገው ዋጋ አይኖረውም

 የመድሐኒትና የጤና ባለሙያ እጥረቱ በቶሎ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል።

በ FB ከ100 በላይ ጤና ባለሙያዎችን
በፈቃደኝነት መመዝገብ ተችሏል።

ቦታው ላይ ደርሰው እርዳታ ለመስጠት ግን ጊዜ እየወሰደ ይገኛል። ለምን የምኪና ችግር መኪና ያላቹ ብትተባበሩን ደስ ይለናል። ውሃ በጣም በጣም ያስፈልጋል። በተለይ ለሴቶች እና ለህፃናት በተለይ ውሃ ስሌለህ ሴቶች የምትረድት ይመስለኛል። ከላይ የጠቀስኩትን መርዳት የምትፋልጎ ቢንያም 0927707000 ወይም 0915955656 ላይ ማናገር የምትችሎ መሆኑን አሳውቃለው

ውሃ የምትሸጡ አንድ በሉን ለሴቶች ስትሉ!

አዘጋጅ፦
TIKVAH-ETHIOPIA ከሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን ጋር በመተባበር የቀርበ
@Tsegabwolde @tikvahethiopia