TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ኢትዮጵያዊያን የአውሮፕላን አደጋ መርማሪዎች በፈርንሳዊያን ባለሙያዎች ያስገለበጡትን የበረራ ክፍል መቅረጸ ድምጽ መረጃ ይዘው ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ከተከሰከሰው ቦይንግ አውሮፕላን 737 ማክስ 8 ካፒቴን ያሬድ ጌታቸው እና የበረራ ተቆጣጣሪ አሕመድ ኑር ሞሐመድ #በአማርኛ ያደረጉትን የመረጃ ልውውጥ ያዳመጡት ኢትዮጵያዊያኑ መርማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡ የመረጃ ልውውጡ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ምትክ አልባ መሆኑ ታምኖበታል፡፡ አዲሱ የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር አውሮፕላኑ ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ አፍንጫውን ወደ ታች አዘቅዝቆ እንዲከሰከስ እንዳደረገው የዘርፉ ባለሙያዎች ያምናሉ፡፡

Via ሮይተርስ(በዋዜማ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia