TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.7K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማንዌል ማክሮን በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት #ላሊበላ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮንን ላሊበላ ተገኝተው ተቀብለዋቸዋል፡፡

Via የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #አብይ_አህመድ እና ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እየጎበኙ ነው፡፡

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለ157 ሰዎች ሕልፈት ምክንያት የሆነውን ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን #የአደጋ_መንስኤ የሚያጣራ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል። በማጣራት ሂደቱ ውስጥ የሚሳተፉ የአሜሪካ የምርመራ ቡድን አባላት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምንጭ፡- የትራንስፖርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይግ 737 ማክስ አሮፕላን እሁድ እለት ተከስክሶ 157 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ተከትሎ የተለያዩ አገራት ያሏቸው ተመሳሳይ አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ እያደረጉ ነው፡፡

አውስትራሊያ እና እንግሊዝ ቦይግ 737 ማክስ 8 ያገዱ አገራት ዝርዝርን ተቀላቅለዋል፡፡

ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን ጨምሮ ሲንጋፖር፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቻይና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ካንቦዲያ እና ሜክሲኮ ቦይንግ 737 ማክስ 8ን ያገዱ አገራት ናቸው።

በርከት ያሉ የአየር መንገዶች ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኖች መጠቀምን በጊዜያዊነት ማቆማቸውን ተከትሎ የቦይንግ ኩባንያ የአክስዮን ዋጋ ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተነገረው።

በትናንትናው እለትም የቦይንግ የአክሲዮን ዋጋ በ13 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በአሜሪካ አየር መንገዶች አውሮፕላኑ አሁንም አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝና አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ነው የሚሉ መግለጫዎች እየወጡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር #መለስ_ዐለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አቅርበዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከካናዳ የተነሳ ቦይንግ 737 800 አውሮፕላን ያለመዳረሻው ለማረፍ ተገደደ። ከሞንትሪያል ካናዳ ወደ አሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት 189 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ቦይንግ 737 800 በኒው ጀርሲ ለማረፍ ተገዷል፡፡ በአውሮፕላኑ የዕቃ መጫኛ አካባቢ የታየ ጪስን ተከትሎ ነው አውሮፕላኑ በድንገት በኑዋርክ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ የተገደደው፡፡

የበረራ ቁጥር 942 የሆነው አውሮፕላን አሳፍራቸው የነበሩ መንገደኞች በአደጋ መውጫ እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ሁለት መንገደኞች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡በዕቃ መጫኛ አካባቢ የተከሰተው ጪስ በምን ምክኒያት የተከሰተ ነው የሚለው እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ አሶሸትድ ፕሬስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ድጋፍ በመንግሥት ስለተፈጸሙ ቅጥሮች ሪፖርተር ጋዜጣ የካቲት 24 ያወጣውን ዘገባ ድርጅቱ “ሐቅ የጎደለው” ብሎታል፡፡ በድርጅታችን ድጋፍ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተፈጸመው ቅጥር የተመድን አሠራርና ደንብ የተከተለ፣ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች ክፍት የነበረ ነው ብሏል፡፡ በድርጅቱ ድጋፍ የተፈጸሙ ቅጥሮች በቅርቡ ተገምግመው ተቀባይነት ስለማጣታቸው የቀረበውን ዘገባም ከእውነት የራቀ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ድርጅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ዕሁድ ዕለት የታተመለትን ማስተባበያውን በትዊተር ገጹ አጋርቷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia