ፎቶ: ትናንት የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ቦይንግ 737 #ET302 አውሮፕላን የተከሰከሰበት ቦታ በቁፋሮ የወጡ ነገሮችን ከላይ ባለው ፎቶ መመልከት ይቻላል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የእስራዔል እና ቻይና ባለሙያዎች ዛሬ አውሮፕላኑ #ከተከሰከሰበት ቦታ ደርሰው የሟቾችን #ሬሳ በማፈላለጉና በመለየቱ ሥራ ሙያዊ እገዛ ሲያደርጉ ውለዋል። አሜሪካ ደሞ አደጋ መርማሪ ባለሙያዎቿን ወደ አዲስ አበባ መላኳን ኢምባሲው አስታውቋል።
#FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሰው አካል የሚመስል ምንም ማግኘት አይቻልም" ዶክተር ሰለሞን አሊ
የኢትዮጵያ አውሮፕላን ከተከሰከሰበት #ጊምቢቹ ቀበሌ ትልቅ ጉድጓድ ፈጥሯል። በቦታው የደረሱ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በጎ ፈቃደኞች የሰው አካል የሚመስል ነገር አላገኙም። ዶክተር ሰለሞን አሊ "የሰው አካል የሚመስል ምንም ማግኘት አይቻልም። ከደረሰን ሪፖርትና ከፎቶግራፎች እንዳየንው ብጥቅጣቂው ራሱ በጣም ትንንሽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር፤ የቻይና እና የእስራኤል ባለሙያዎች ከትናንት ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 -800 ማክስ አውሮፕላን ከተከሰከሰበት ቦታ ፍለጋ ሲያካሒዱ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰብዓዊ ዲፕሎማሲ፤ የገቨርናስና የዓባላት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን አሊ "የሰው አካል ነው ብለህ የምትላቸው ነገሮች የሉም። ሕይወት ለማዳን የሚቻልበት አይነት ኹኔታ አልነበረም። ስለዚህ እዚያ አካባቢ ተበታትነው የነበሩ ቁሳቁሶችን፤ ንብረቶችን፤ አንዳንድ የሰውነት ክፍሎችን" በጎ ፈቃደኞች ከትናንት ጀምሮ መሰብሰባቸውን ለጀርመን ራድዮ አስረድተዋል።
ዶክተር ሰለሞን "የሰው አካል የሚመስል ምንም ማግኘት አይቻልም። ከደረሰን ሪፖርት እና ከፎቶግራፎች እንዳየንው ብጥቅጣቂው ራሱ በጣም ትንንሽ ነው" ሲሉ አክለዋል። በጎ ፈቃደኞች በቦታው ከነሩ የጸጥታ አስከባሪዎች፤ የሕክምና ባለሙያዎች እና ከሌሎች አገራት ከተጓዙ ባለሙያዎች አጠገብ ሆነው የተቀዳደዱ መፃሕፍት፤ መታወቂያዎች፤ ፓስፖርቶች ሰብስበዋል" ብለዋል።

እጅግ በጣም ያሳዝናል...
"የሰው አካል #የሚመስል ምንም ማግኘት አይቻልም። ከደረሰን ሪፖርት እና ከፎቶግራፎች እንዳየንው #ብጥቅጣቂው ራሱ በጣም #ትንንሽ ነው" ዶክተር ሰለሞን አሊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሰው አካል #የሚመስል ምንም ማግኘት አይቻልም። ከደረሰን ሪፖርት እና ከፎቶግራፎች እንዳየንው #ብጥቅጣቂው ራሱ በጣም #ትንንሽ ነው" ዶክተር ሰለሞን አሊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ መሀዲ ጊሬን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ መሾሙ ተገለፀ።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን በዛሬው እለት ያካሄደ ሲሆን፥ የተለያዩ ሹመቶችንም አፅድቋል።
በጉባዔው ላይም የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ ኢብራሂም ኡስማን የስራ መልቀቂያቸውን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባውም አቶ ኢብራሂም ኡስማን የስራ መልቀቂያን የተቀበለ ሲሆን፥ በምትካቸውም አቶ መሀዲ ጊሬን የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም የተለያዩ ሾመቶችን አጽድቋል፦
አቶ አብደላ አህመድ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ
አቶ ከድር ጁሀር፦ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
አቶ አብዱሰላም አህመድ፦ የግብርና፣ ማእድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
ወይዘሮ ሙሉካ መሀመድ፦ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሙሳ ጠሀ፦ የፍትህ ፀጥታ እና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ፦ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል።
Via FBC

#Breaking
የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡተፍሊካ በቀጣዩ ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ። የ82 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ለአምስተኛ ጊዜ ለፕሬዝዳንትነት እንደሚወዳደሩ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ነበር።

#update የኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክት ቤት ባካሔደው 26ኛው መደበኛ ስብሰባ ለ2ዐ11 በጀት ዓመት በመንግሥት በኩል በቀረበ 33 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር የፌደራል መንግሥት ተጨማሪ በጀት ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ዕይታ ለምክር ቤቱ ገቢዎች ፋይናንስ እና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሜቴ እንዲመራ ውሳኔ አስተላልፏል።
ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላልይበላ🔝
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን ለሥራ ጉብኝት ዛሬ #ኢትዮጵያ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለሁለት ቀናት በሚኖራቸው የኢትዮጵያ ቆይታ የላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚጎበኙ ታውቋል። የላልይበላ ነዋሪዎችም ኢማኑኤል ማክሮንን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል።
Via AMMA

#update የአሜሪካ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ የባለሙያዎች ቡድን የአውሮፕላን አደጋ ስፍራ ምርመራ እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ዲዛይን #ማሻሻያ እንዲደረግ አሜሪካ ቦይንግ ኩባንያን ጠየቀች፡፡ አሜሪካ ጥያቄውን ያቀረበችው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይግ 737 ማክስ 8 አሮፕላን እሁድ እለት ተከስክሶ 157 ሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ተከትሎ ነው፡፡
ምንጭ፡- ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፡- ሮይተርስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ
.
.
ከትናንት በስቲያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 ዋና አብራሪ የነበረው ያሬድ ጌታቸውን ለአስራ አንድ ዓመታት የሚያውቀው ኡጋንዳዊ ጓደኛው ሃሰን ካቴንዴ ያሬድ ራግቢ በጣም ይወድ እንደነበር ይናገራል።
ያሬድና ሃሰን የሚተዋወቁት ከዓመታት በፊት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ፀጉር ቤት ያሬድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበራሪ ፅሁፍ ወረቀት ይዞ ሃሰን [ፓይለት ነህ] ብሎ ያሬድን በጠየቀበት አጋጣሚ ነበር።
ያሬድ ኬንያ እንደተወለደ ነግሮት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ያወሩት በስዋሂሊ እንደነበር ሃሰን ያስታውሳል።
ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ስፖርት የሚወድ አይነት ሰው የነበረ ሲሆን ለራግቢ ግን ልዩ ፍቅር ነበረው።
ያሬድና ሃሰን አዘውትረው ይገኛኙ የነበረው ግእዝ የሚባል የፈረንሳይ ሬስቶራንት ተገናኝተው ነበር ራግቢ የሚመለከቱት።
መጀመሪያ አካባቢ ሀሰንም መኪና ስላልነበረው አብዛኛውን ጊዜ ያሬድ ያሽከረክር የነበረውን የአባቱን አሮጌ መኪና እየሾፈረ ብዙ ቦታዎች መሄዳቸውንም ሃሰን ያስታውሳል።
ያሬድና ሃሰን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት የነበረ ሲሆን በሎሜ ስካይ አየር መንገድ ስራ ስላገኘ ጓደኛቸው ነበር ያወሩት።
ያሬድ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ሲሆን እናቱ ኬንያዊ ሲሆኑ አባቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የልጅነት ጊዜውን በኬንያ ያሳለፈ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ተከታትሎ የኢትዯጵያ አየር መንገድ አቬሽን ትምህርት ቤትን ተቀላቅሏል።
ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ኢትዮጵያዊም ኬንያዊም ማንነቱን ይወድ ነበር። ያሬድ አማርኛ ፣ ስዋሂሊና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን ጥርት አድርጎ ይናገር እንደነበር ሀሰን ገልፆልናል።
"ብዙ ጊዜ ማንነቱን የሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊ ነህ ሲሉት [ኢትዮጵያዊና ኬንያዊ]ብሎ ይመልስ ነበር] በማለት ነገሩ አንዳንድ ጊዜም ያሬድን ያስቆጣው እንደነበር ሃሰን ይናገራል።
ሃሰን የአደጋውን ዜና የሰማው ከማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ጓደኛው በአደጋው ስለመሞቱ ያወቀው ነገር አልነበረም።
"የአደጋውን ዜናና የአውሮፕኑን ሰራተኞች ስም ዝርዝር ስመለከት ያሬድ የሚል ስም ባይም የተለመደ ስም ስለሆነ ሌላ ያሬድ ነው ብዬ አሰብኩ። የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም። ቆይቶ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ሌላ ጓደኛችን ስለ ያሬድ ሰማህ ወይ? ምንድነው ምንትለው? ያሬድ ምን ሆነ ነው ያልኩት። በጣም አሰቃቂ ነው" ብሏል ሃሰን።
ከዚያም ጓደኛው የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ የእነሱ ጓደኛ ያሬድ እንደሆነ ሲነግረው ለማመን በጣም እንደከበደውና ሊሆን አይችልምም የሚል ስሜት እንደተሰማው ይናገራል።
"ለማመን የሚከብድ ነገር ነው። መተኛት አልቻልኩም እስካሁን #ድንጋጤ ውስጥ ነኝ"
እሱ ብቻ ሳትሆን የሀሰን እናትም በድንጋጤ ውስጥ እንዳሉ ይናገራል።
ያሬድ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ይመለከት እንደነበር የሚናገረው ሃሰን "በሚገባ #የሰለጠነ አብራሪ ነው። እርግጠኛ ነኝ #እስከመጨረሻዋ ሰዓት ብቃቱን እንደተጠቀመ" በማለት ጓደኛው ያሬድ እንደ ጀግና እንዲታወስ እንደሚፈልግ ይናገራል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ