TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ‼️

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ መስከረም አራት ቀን በቡራዩ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት በተሳታፊነት በጠረጠራቸው 109 ግለሰቦች ላይ ክስ መመስረቱን አስታወቀ፡፡

ከተጠርጠሪዎቹ ውስጥ 81 የተያዙ ሲሆን፥ 28 የፍርድ ቤት ማዘዣ ወጥቶባቸው እየታደኑ ነው ተብሏል፡፡

የቡራዩን ጥቃት ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ በታያው የጸጥታ ችግር በማነሳሳት እና በተሳታፊነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስቀመጠው በሐዋሳ ከተማ በወላይታ በሲዳማ ብሄር መካከል ግጭት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱና ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ከ90 በላይ ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቷል፡፡

ከነዚህ ተጠርጣሪዎች መካከል የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባና የፖሊስ አባላትም ይገኙበታ፡፡

ጠቅላይ አቃቢህግ በምርምር ደረስኩበት ባለው መረጃ መሰረት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች እና የጸጥታ ችግሮች በተደራጀ ቡድን የሚመሩ ናቸው ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ‼️

የአማራ መስተዳድር የልዩ ጥበቃ ፖሊስ አዛዥ መኖሪያ ቤት ዉስጥ ትናንት የተያዘዉ የሽጉጥ «ክምር» በየሥፍራዉ #ሊከፋፈል እና #ሊሰራጭ የተቃደ እንደነበር የመስተዳድሩ የሠላም እና ደሕንነት ቢሮ አስታወቀ። ባሕርዳር በሚገኘዉ የመስተዳድሩ የልዩ ጥበቃ አዛዥ በነበሩት በኮምንደር ዉበቱ ሺፈራዉ መኖሪያ ቤት፣ በሰባት ጆንያዎች ተቋጥሮ የተገኙት ሽጉጦች ብዛት 498 ነዉ። የአማራ መስተዳድር የሠላም እና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጌድየር ጄኔራል #አሳምነዉ_ፅጌ ዛሬ ለDW እንደነገሩት ሽጉጦቹ በሙሉ አዳዲስ እና ቱርክ ሠራሽ ናቸዉ።

ሽጉጦቹ የተያዙት ጉዳዩን በቅርብ በሚያዉቁ ወገኖች ጥቆማ እና ትብብር ነዉ። ጄኔራል አሳምነዉ አክለዉ እንዳሉት ሽጉጦቹ የተያዘባቸዉ ኮማንደር ዉበቱ በቁጥርጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ «አባሪ ተባባሪ» ተብለዉ የሚጠረጠሩ ወገኖችን ለመያዝ ክትትሉ ቀጥሏል። ጄኔራል አስምነዉ «ባንድ እና በሁለት ሰዉ ይሠራል ብለን እንገምትም» ብለዋል።

አንድ የክልሉ ፀጥታ ኃይል ከፍተኛ ባለሥልጣን ይሕን ያክል ጦር መሣሪያ ደብቀዉ መገኘታቸዉን፣ ጄኔራል አሳምነዉ «አሳዛኝ እና አሳፋሪ» ብለዉታል። ሽጉጦቹ ሊከፋፈልላቸዉ ነበር የተባሉት ወገኞችም ሆነ የተላከበት ስፍራና የላኪዉ ማንነትም እስካሁን በይፋ አልተነገረም።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሶማሌ ላንድ ተነስተው በቶጎጫሌ ወደ ጅግጅጋ ሲያመሩ የነበሩ ኮድ-04046፣ ኮድ-05759 ሁለት ቅጥቅጥ አይሱዙዎች እና ኮድ-39416 የጭነት ተሸከርካሪ ግምታዊ ዋጋቸዉ 550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ፤ ምግብ ነክ፣ ጨርቃ ጨርቅ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነዉ በህገወጥ መንገድ ወደ ጅግጅጋ ለመግባት ሲሞክሩ በፌደራልና በክልል ፖሊሶች እንዲሁም በጉምሩክ ሰራተኞች ክትትል ታህሳስ 23/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 እስከ ምሽት 2 ሰዓት ባለዉ ጊዜ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ #ደመላሽ_ተሾመ አያይዘዉ እንደገለጹትም በድርጊቱ ተሳታፊ የነበረዉ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ዉሎ አስፈላጊዉ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዉ በቀጣይም ህብረተሰቡ ይሄን መሰል ድርጊቶች በንቃት በመከታተል ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

Via~EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ 117 ሚሊየን ብር ወጭ የተደረገባቸው ሶስት የህዝብ መናፈሻ ፓርኮች በተያዘው ዓመት #እንደሚጠናቀቁ ተገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የብሮድካስት ባለስልጣን ምላሽ🔝

በሸገር ኤፍ ኤም 102.1፣ ድሬትዩብን የተመለከተ አንድ ዘገባ ማቅረቡ አይዘነጋም፡፡ ድሬትዩብ ዘገባው፣ “መልካም ሥምና #ዝናዬን በማጉደፍ ድርጅታችን በሕዝብ ላይ ያለውን ተደማጭነት እና ተዐማኒነት አላግባብ ሆን ብሎ ለመሸርሸር በማሰብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሶብናል” በሚል ለብሮድካስት ባለሥልጣን ክስ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ክሱን አስመልክቶ ከሸገር የቀረበውን ምላሽ የተመለከተው የብሮድካስት ባለሥልጣን፣ “ባካሄድኩት ማጣራት ሸገር ያቀረበው ዘገባ ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና ሙያዊ ሃላፊነት በተመላበት አግባብ ተዘጋጅቶ የተሰራጨ” ነው ሲል ብያኔውን ሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምርመራ እየተደረገ ይገኛል‼️

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተከሰቱ ግጭቶች አቀነባባሪዎችን ለመለየት ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። እንዲሁም በችግር ፈጣሪ #ተማሪዎች ላይ ተቋማዊ #የዲሲፕሊን_እርምጃዎች መውሰድ ተጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"#የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል‼️"

ምዕራብ ኦሮሚያ እና ኦሮሚያን ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ባለፉት ተከታታይ ወራት በርካታ ሰዉ በገደሉ እና ባፈናቀሉ ታጣቂዎች ላይ «የማያዳግም» ያለዉን እርምጃ መዉሰዱን ባካባቢዉ የሠፈረዉ ጦር አስታወቀ።

በቅርቡ «ኮማንድ ፖስት» በሚል መጠሪያ ወደ አካባቢዉ የዘመተዉ ጦር ዛሬ ባሰራጨዉ መግለጫ እንዳለዉ ቁጥራቸዉን ያልጠቀሰዉ የታጠቁ «ፀረ ሠላም» ኃይላት እጅ ሰጥተዋል፣ እጅ ባልሰጡት ላይ ደግሞ የኃይል እርምጃ ወስዶ «አበረታች» ያለዉን ዉጤት አስመዝግቧል።

ሰዉ የገደሉ፤ ሕዝብ ያንገላቱ፣ የዘረፉ፣ ያፈናቀሉና መንገድ የዘጉ ኃይላትን #መያዙንም አስታዉቋል።

በመግለጫዉ መሠረት ጦሩ፣ ከያዛቸዉ ኃይላት ላይ በርካታ የጦር መሳሪያ እና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ #ማርኳልም

ሠላምን ያዉካሉ በተባሉት ኃላት ላይ ጠንካራ እርምጃ በመወሰዱ #ተዘግተዉ የነበሩ መንገዶች፣የንግድ መደብሮች፣ የጤና እና የሌሎች አገልግሎት መስጪያ ተቋማት #መከፈታቸዉን መግለጫዉ ጠቅሶ፣ ዝርዝሩን ወደፊት ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።

የኦሮሚያ የጤና እና የትምሕርት ቢሮዎች በአብዛኛዉ የምዕራብ ኦሮሚያ የጤና እና የትምሕርት አገልግሎት መቋረጡን ትናንት አስታዉቀዉ ነበር።

ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ኦሮሚያን ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ ጋር በሚያዋስኑ የድንበር ግዛቶች ካለፈዉ መስከረም ጀምሮ በተባባሰዉ ግጭት በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸዉ፣ በመቶሺሕ የሚቆጠሩ መፈናቀላቸዉ እና በርካታ ሐብትና ንብረት ወድሙ ወይም መዘረፉ በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ክልል ካፋ ዞን፣ ደቻ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ 9 ሰዎች በድንገተኛ ጥቃት #ተገድለዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው ባንድ ሠፈራ ጣቢያ ውስጥ መሆኑን ሪፖርተር የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ አስነብቧል፡፡ በጥቃቱ ሌሎች 4 ሰዎች ክፉኛ ተጎድተዋል፤ ብዙ ንብረትም ወድሟል፡፡ ጥቃት አድራሾቹ ከዞኑ ጠረፋማ አካባቢዎች ወይም ከአጎራባቾቹ ቤንች ማጂና ደቡብ ኦሞ ዞኖች የመጡ መዔኒት የተባሉ አርብቶ አደር ጎሳ አባላት እንደሆኑ ተገምቷል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር(wazemaradio)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎቹ‼️

የ2011/18 የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች ነን ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ የዉጭ ትምህርት እድል ካልቻለም ደግሞ ሀገር ዉስጥ የማስተርስ ትምህርታችንን እንድንማር ቃል መግባታቸዉ በኢትዮጵያዊያን ህዝብ ሁሉ የታወቀ ነዉ ሁሉም ሚዲያዎች ይህንን ጉዳይ መዘገባቸው ይታወሳል።

ይሁን አንጂ እስካሁን ባለዉ ጊዜ ምንም አይነት የትምህርት እድልም ሆነ ስላለው ነገር ትክክለኛ መረጃም ቢሆን አላገኘንም።

በዚህም ምክኒያት፦

1, ብዙ የትምህርት እድሎች አምልጠውናል

2. የስራ እድሎችንም አልፈውናል

3. UAE scholarship አለ ሁሉንም ዶክመንት ፓስፖርትንም ጨምሮ አስገቡ ተብሎ አስገብተን ተሰረዘ ተባልን በዚህም የተነሳ ላልተገባ ወጪ ተዳርገናል፡፡

4. ወርቅ የሆነውን ጊዜያችንን በከንቱ እያሳለፍን እንገኛለን፤ ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ እንረዳለን ቢሆንም እድገት የሚመጣዉ በአስቸጋሪም ሁኔታ ዉስጥም ቢሆን ልማትን በጎን ማሰኬድ እንደሚቻል እናምናለን። ይህ መልዕክት ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከታላቅ አክብሮት ጋር እንዲደርስ እንጠይቃለን፡፡ እንዲሁም አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠንም እንጠይቃለን እናመሰግናለን!!

የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ተማሪዎች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከዛላምበሳ ግምባር የጦር መሳሪያ ጭነው ወደ መሀል ሀገር ሲንቀሳቀሱ #የታገቱ የመከላከያ ተሽከርካሪዎች #ተለቀዋል። የመከላከያ ተሽከርካሪዎቹ የተለቀቁት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር #ውይይት ተደርጎ ስምምነት ላይ በመደረሱ ነው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ያጋጠመውን የሰላም #መጓደል ለመቅረፍ በምስራቅ ወለጋ ዞንና በነቀምቴ ከተማ ህዝባዊ ውይይት ሲካሄድ ውሏል። እንዲሁም በትናንትናው ዕለት የኦሮምያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ኋላፊ ረዳት ፕሮፌሰር #ምህረቱ_ሻንቆ ከወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወረታ ከተማ የደረሰ የትራፊክ አደጋ!
አሳዛኝ ዜና‼️

በወረታ ከተማ የአደጋ መከላከያ እህል ክምችት መካዝን አካባባቢ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የሰው ህይወት አለፈ።

በትላንትናው ዕለት ከጎንደር ወደ ባ/ዳር ሲጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ET 78608 የሆነ ዳንጎቴ የከባድ ጭነት መኪና መንገዱን በመሳት ከወረታ ወደ ወርቅ ሜዳ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ 23141 ከሆነ ባጃጅ ጋር #በመጋጨቱ ከባጃጁ ውስጥ ሆነው ሲጓዙ ከነበሩት 5 ተሳፋሪዎች መካከል 2ቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።

በአደጋው 1 ሰው ከባድ ጉዳት የደረሰበት መሆኑንና ወዲያዉኑ ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል በአንቡላንስ መላኩንና 2ቱ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው በወረታ ከተማ ጤና ጣቢያ እየተረዱ መሆናቸውን የወረታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ከስፍራው መዘገቡን የጽ/ቤቱ የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት የለውጥ ቡድን መሪ አቶ ኃይሌ ብርሃኔ አስታውቀዋል።

ምንጭ፦Woreta city communication affairs(Mulusew)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ፣ ቡራዩ፣ አ.አ.፣ አሶሳ....

በተለያዩ ጊዜያት በቡራዩ፣ ሀዋሳ፣ አዲስ አበባና አሶሳ በተከሰቱ ግጭቶች የየፀጥታ ሀይሉና #አመራሩ እጅ እንደነበረበት ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ።

በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተደራጀ የድንበር ተሻጋሪ እና አገራዊ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ #ፍቃዱ_ፀጋ እንደተናገሩት በቡራዩ፣ ሀዋሳና አዲስ አበባ በተከሰቱ ግጭቶች እጃቸውን ያስገቡ የፀጥታና የአመራር አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ ሲሆን በአሶሳ ግጭት የተጠረጠሩ አመራሮች ያለመከሰስ መብት በማንሳት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በቡራዩ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት የ37 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን 109 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ከተጠርጠሪዎቹ ውስጥ 81 የተያዙ እና 28 ደግሞ በፍርድ ቤት ማዘዣ ወጥቶባቸው እየታደኑ ነው ብለዋል አቶ ፍቃዱ።

በአዲስ አበባ ከተማ በተከሰተው የጸጥታ ችግር የ28 ግለሰቦች ህይወት ያለፈ ሲሆን ሁለት ግለሰቦችም ማንነታቸው ሳይታወቅ ቀርቷል፤ ግጭቱን በማነሳሳት እና በተሳታፊነት የተጠረጠሩ ግለሰቦችና የፀጥታ አካላት ላይም ክስ ተመስርቷል።

#በሐዋሳ_ከተማ በወላይታና ሲዳማ ብሄሮች መካከል ግጭት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱና ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ከ90 በላይ ግለሰቦች ላይ በሶስት መዝገብ ክስ መመስረቱንም አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል። የሐዋሳ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ ከዚህ ጋር በተያያዘ መጠርጠራቸውም ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ በግድያ፣ በግድያ ሙከራና በከባድ #ውምብድና ስለመጠርጠራቸው አቶ ፍቃዱ ጨምረው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ ስታንዳርድ የዜና ማሰራጫ ድረ-ገፅ ማምሻዉን በቲዊተር ገፁ በዘገበዉ መሠረት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የፕረስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ #ቢልለኔ_ስዩም እና ምክትላቸዉ #ሔለን_ዮሴፍ ከሥልጣን #አልተሻሩም፤ አቶ ካሳሁን ጎፌም #አልተሾሙም፤ አቶ #ንጉሱ_ጥላሁን ግን በፕሬስ ሴክሪታሪያቱ አማርኛ ክፍል እንዲሠሩ ተዛዉረዋል ሲል ዘግቧል።

ምንጭ፦ አዲስ ስታድንዳርድ

🔹ሀላፊዎቹ ስለመተካታቸው በርካታ የመንግስት እና የግል የሀገር ውስጥ የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች የሚወጡ ከሆነ ወደእናተ እናደርሳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

በቦሌ ክፍለ ከተማ #በጦር_መሳሪያ የተደገፈ #ዘረፋ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ 24 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች፥ በትናንትናው እለት ከሌሊቱ 7 ሰዓት ከ20 የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ – 3 – 30212 ኦ.ሮ የሆነ ሚኒባስ ተሸከርካሪ በመያዝ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ህብረተሰቡ አስቀድሞ ለፖሊስ በሰጠው #ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ሰሚት ሴንትራል ሆቴል አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን፥ የሰሚት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር #ካሳሁን_ፍቃዱ ተናግረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም አንድ ሽጉጥ፣ ስምንት ጥይት፣ ሁለት ፓውዛ መብራቶች፣ የብረት መቁረጫ፣ 20 ማዳበሪያዎች እና ከተር እንደተገኘባቸውም ነው ምክትል ኮማንደሩ የተናገሩት። አሁን ላይም ፖሊስ ምርመራውን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በቦሌ ክፍለ ከተማ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሚውሉ ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ ገመዶችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በህብረተሰቡ ትብብር ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን አስታውሰዋል።

ህብረተሰቡም ጥቆማዎችን በመስጠትና መሰል ተግባራትን በመከወን እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የጥበቃ ሰራተኞች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia