TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ኢትዮ ቴሌኮም‼️

በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚታየውን የኔትወርክ ጥራት #መጓደል በሶስት ወራት ውስጥ መፍታት የሚያስችል የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራ እያከናወነ መሆኑን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ፡፡

መርካቶን ጨምሮ ቦሌ አራብሳ፣ ኃይሌ ጋርመንት፣ ጀሞና፣ ቦሌ አካባቢዎችና በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ቦታዎች የሞባይል ኔትወርክና የኢንተርኔት አገልግሎት ጥራት መጓደል በስፋት ይስተዋላል፡፡

በእነዚህ ቦታዎች ያለውን የኔትወርክ ጥራት መጓደል በአጭር ጊዜ ለመፍታት ኢትዮ-ቴሌኮም ፕሮጀክት ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ በመስሪያ ቤቱ የኔትወርክ ዲቪዥን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ኃይለመስቀል በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

የኔትወርክ ችግሩም የተከሰተው በዋናነት በአካባቢው የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱና በቦታው ያለው ኔትወርክ በመጨናነቁ ነው ብለዋል፡፡

በእነዚህ ቦታዎች ያለውን የኔትወርክ አቅም ለመጨመር የሚስችሉ ዕቃዎች ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ በዚህ ሳምንት መግባታቸውንምአቶ ቴዎድሮስ ገልፀዋል፡፡

በመዲናዋ በተመረጡ ቦታዎች ጥቅም ላይ የሚውሉት ዕቃዎቹ የኔትወርክ ጥራት ችግሩን ከመፍታት ባለፈ ተጨማሪ 500 ሺህ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም አላቸው ብለዋል፡፡

የኔትወርክ ማስፋፊያው ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በሁለት ወር ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ችግሩ እንደሚፈታ ተመልክቷል፡፡

ይህ የመፍትሄ ውጥን በፊትም አሁንም ኔትወርክ በሌለባቸው ቦታዎች መፍትሄ የሚሰጥ ሳይሆን የኔትወርክ ጥራት መጓደል በሚታይባቸው ቦታዎች ማሻሻያዎችን ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በዘላቂነት የሞባይል ኔትወርክና የኢንተርኔት አገልግሎት የመቆራረጥ ችግርን ለመፍታት የኔትወርክ አቅምን ከመጨመር ባለፈ አማራጭ የኤሌክትሪክ ሀይልን ለመጠቀም እተየሰራ እንደሆነም ኢትዮ-ቴሌኮም አስታውቋል ሲል የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች ያጋጠመውን የሰላም #መጓደል ለመቅረፍ በምስራቅ ወለጋ ዞንና በነቀምቴ ከተማ ህዝባዊ ውይይት ሲካሄድ ውሏል። እንዲሁም በትናንትናው ዕለት የኦሮምያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ኋላፊ ረዳት ፕሮፌሰር #ምህረቱ_ሻንቆ ከወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia