ወደ ባንክ ቅርንጫፍ መሄድ ሳይጠበቅብዎ በቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን ከእሁድ እስከ እሁድ ለ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት ያግኙ።


#BankofAbyssinia #BankingServices #ITM #VirtualBanking #DigitalBanking #MoneyTransfer #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
የዛይ ራይድ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች የአቢሲንያ ባንክን እንዲሁም የውጭ ባንኮችን ቪዛ ካርድ በመጠቀም የአገልግሎት ክፍያቸውን በብር እንዲሁም በውጭ ሀገር ገንዘብ መክፈል የሚችሉበት አሠራር ተዘርግቶ አገልግሎቱ ተጀምሯል፡፡


አቢሲንያ በዲጂታል ክፍያ ግንባር ቀደም ከሆነው ከቪዛ ጋር የዲጂታል ንግድን (E-Commerce) ለማቀላጠፍ የሚያስችለውን የቪዛ ሳይበር ሶርስ Visa CyberSource Payment Gateway Technology የኦንላይን ክፍያ አማራጭ በማቅረብ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ቀዳሚ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ፣ ዘመን ከወለዳቸው ቴክኖሎጅዎች ጋር ራሱን በማላመድ የዲጂታል ንግድን በኢ-ኮሜርስ የክፍያ አማራጭ አገልግሎቱን መስጠት ከጀመረ ከ2 ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡
ባንካችን የዲጂታል ንግድን የሚያቀላጥፍ የክፍያ አማራጭ E-Commerce payment gateway ቴክኖሎጂን ለደንበኞቹ በማቅረብ የአገልግሎት አሰጣጡን በማቀላጠፍ አሁንም እየሠራ የሚገኝ ሲሆን፣ E-Commerce payment gateway ድረ-ገጽን (website) ወይም መተግበሪያዎችን (App) በመጠቀም በቪዛ አልያም በማስተር ካርድ ኦንላይን ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ በተለያዩ ንግድ ሥራ ላይ የተሠማሩ ተቋማት፤ በውጪ አገር ያሉ ደንበኞቻቸው አቢሲንያ payment gateway የክፍያ አውታር ጋር ዌብ ሳታቸውን ወይም መተግበሪያቸውን በማገናኘት ከመላው ዓለም በኦን ላይ ክፍያዎችን የሚቀበሉበት ሥርዐት ነው፡፡
ዛይ ራይድም በዚህ ረገድ ለደንበኞቹ የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ በማሰብ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያን በቀላሉ በካርድ መፈጸም እንዲቻል አሰራሩን ከባንካችን ጋር በማስተሳሰር ተግባራዊ ያደረገው የዲጅታል ክፍያ ስርአት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ዲያስፖራውን ጨምሮ ከውጭ ሀገር የሚመጡ ግለሰቦች እንዲሁም በዚህ ሀገርም የሚገኙ ተገልጋዮች ጥሬ ገንዘብ መጠቀም ሳያስፈልጋቸው የባንካችንን ቪዛ ካርድ እና የውጭ አገር ባንኮችን አለምአቀፍ ካርድ ተጠቅመው ክፍያ መፈጸም መቻላቸው፣ በዘርፉ ፈር ቀዳጅ የሚያደርገን ሲሆን፣ ለሀገራችንም የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብሎ ባንካችን ያምናል፡፡
ይህ ቅንጅት ማንኛውም ሰው Zay Ride የስልክ መተግበሪያን ከPlayStore ወይም ከAppStore በማውረድ የአቢሲኒያ ቪዛ ካርዱንና አለምአቀፍ ካርዶችን ተጠቅሞ የጉዞ አገልግሎቱን ክፍያ በብር ወይም በውጭ ሀገር ገንዘብ በቀላሉ መክፈል ያስችለዋል፡፡
የሀዘን መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩት አቶ ዱባለ ጃሌ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው አቢሲንያ ባንክ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ይወዳል ። አቶ ዱባለ ጃሌ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፉ ታላቅ ሰው ነበሩ ። አቶ ዱባለ ጃሌ ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባትና እኚህ አንጋፋ የባንክ ባለሙያ ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ሕመም እየተቸገሩ እንዳለ ባንካችን ተረድቶ፣ ለሕክምና ወጪያቸው ይረዳቸው ዘንድ የብር 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ድጋፍ በባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ በኩል ተበርክቶላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ አቢሲኒያ ባንክ ለቤተሰቦቻቸውና የቅርብ አጋሮቻችው መፅናናትን ይመኛል።
ባንካችን አቢሲንያ ማህበረሰቡ አዘውትሮ የሚከታተላቸውን ሚዲያዎች እና ፕሮግራሞች/የመረጃ አቅርቦቶች በጥናት ለመለየት እንዲያስችለው መጠይቅ (questionnaire) በማዘጋጀት መረጃ እያሰባሰበ ነው፡፡ እርስዎም መጠይቁን በመሙላት በጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ በታላቅ አክብሮት እንጠይቅዎታለን፡፡ እባክዎን መጠይቁን (questionnaire) ለመሙላት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡
https://forms.gle/Cj8qzuWrN8onE5u17
መቆጠብ ያሸልማል! እንሸልምዎ!

አቢሲንያ ባንክ ደንበኞቹን ለማበረታታት የ5ኛ ዙር "የእንሸልምዎ" የሽልማት መርሐ ግብርን እንዲሁም 4ኛ ዙር "መቆጠብ ያሸልማል" መርሐ ግብርን እያካሄደ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በ4ኛው ዙር መቆጠብ ያሸልማል መርሐ-ግብር ከብር 200 ጀምሮ ሲቆጥቡ አይሱዙ ISUZU NPR እና ትራክተርን ጨምሮ 160 ሽልማቶች እንዲሁም በ5ኛው ዙር የእንሸልምዎ መርሐ-ግብር የተላከልዎትን የውጭ ሀገር ገንዘብ በቅርንጫፎቻችን ሲቀበሉ፣ ሲመነዝሩና፣ ዓለም አቀፍ ካርዶችን በመጠቀም ክፍያዎች ሲፈፅሙ በቱርክ የ5 ቀን ቆይታን ጨምሮ የተለያዩ አጓጊ ሽልማቶች ለባለ ዕድለኞች ተዘጋጅተዋል! ከ800 በላይ በሆኑ ቅርንጫፎቻችን ከብር 200 ጀምሮ በመቆጠብ ከተዘጋጁ አጓጊና በርካታ ከሆኑ ሽልማቶች ውስጥ አሸናፊ ለመሆን ራስዎን እጩ ያድርጉ፡፡
አብዝተው በመቆጠብ የመሸለም እድልዎን ያስፉ!
ደጋግመው በተቀበሉ፣ በመነዘሩና ግብይቶችን በፈፀሙ ቁጥር አሸናፊ የመሆን ዕድልዎ እየሰፋ ይሄዳል፡፡
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#BankofAbyssinia #remittance #Banking #BankingService #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ባላችሁበት ሆናችሁ የአፖሎ ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ፊታችሁንና መታወቅያችሁን ስካን በማድረግ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በማስገባት 5 ደቂቃ ባልፈጀ ጊዜ ውስጥ የአቢሲንያ ባንክ አካውንት መክፈት ትችላላችሁ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ገንዘብ ገቢ ለማድረግ ባንክ ሊዘጋብኝ ነው ብለው አይቻኮሉ፡፡ በማንኛውም ጊዜ፣ በማንኛውም ቀን የኢንዱስትሪው ቀዳሚ በሆኑት፣ 24 ሰዓት በማያንቀላፉት የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎቻችን ገንዘብዎን ተቀማጭ ያድርጉ፡፡

#BankofAbyssinia #remittance #Banking #BankingService #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ባንካችን አቢሲንያ ማህበረሰቡ አዘውትሮ የሚከታተላቸውን ሚዲያዎች እና ፕሮግራሞች/የመረጃ አቅርቦቶች በጥናት ለመለየት እንዲያስችለው መጠይቅ (questionnaire) በማዘጋጀት መረጃ እያሰባሰበ ነው፡፡ እርስዎም መጠይቁን በመሙላት በጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ በታላቅ አክብሮት እንጠይቅዎታለን፡፡ እባክዎን መጠይቁን (questionnaire) ለመሙላት ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡
https://forms.gle/Cj8qzuWrN8onE5u17
ባለውለታዎች!

ባንካችን ከ50 አመት በላይ ለሆናቸው ግለሰቦች ያዘጋጀው ልዩ የቁጠባ ሂሳብ ሲሆን ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ ከፍ ያለ የወለድ መጠን የሚያስገኝ እና ከተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ ቅናሽ የሚያገኙበት ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡፡

https://www.bankofabyssinia.com/saving-account/

#BankofAbyssinia #BankingService #SeniorCitzens #WisdomAccount #Savings
ከዴሊቨር አዲስ ይዘዙ
በካርድዎ ይክፈሉ !

ለራስዎ ወይም ለወዳጅዎ ከዴሊቨር አዲስ ሲያዙ የአቢሲንያ ባንክን ቪዛ ካርድ እንዲሁም ቪዛና ማስተር ካርድን በመጠቀም ክፍያዎን ይፈጽሙ፡፡
#VISAcard #Mastercard #CardBanking #E_commerce #Deliveraddis #delivery #ThechoiceforAll
We Are Hiring!

Bank of Abyssinia seeks to hire applicants for the following positions;

1) Job Title: - Senior Credit Underwriter
Place of Work: Addis Ababa
2) Job Title: - Grade I Branch Business Manager-Grand Gato Branch and Office Equipment Technician
Place of Work: Dire Dawa District
3) Job Title: - Banking Business Officer
Place of Work: Adola Branch (Hawassa District)

Use the link below to apply for the vacancy
https://vacancy.bankofabyssinia.com
የ"አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊ በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በጅግጅጋ ከተማ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ተከናወነ፤
የ"አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የአምስተኛ ደረጃን በማግኘት የብር 200,000 ተሸላሚ ለሆነው የጅግጅጋ ተወላጅ ተማሪ ሳልማን አሊ የእንኳን ደስ አለህ አቀባበል በጅግጅጋ ሎተስ ሆቴል በትላንትናው እለት የተከበሩ ገራድ ኩልምዬ ገራድ መሐመድ፣የሱማሌ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ሸህ አህመድ መሐመድ አሊ፣የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ዚያድ አቂል፣የሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ /ተወካይ/ አቶ አብዱላሂ አብዲ፣የሱማሌ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መሐመድ ሁሴን፣የሱማሌ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙህዲን አበዲ ፋራሃ ፣ የሱማሌ ክልል ክህሎትና ስራ ፈጠራ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ሂቦ አህመድ፣ የሱማሌ ክልል ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ኡባህ አህመድ፣ የሱማሌ ክልል ኘሬዝዳንት ጽ/ቤት አማካሪ አቶ ካሣሁን መሐመድ ፣ የባንካችን የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣የባንካችን የበላይ የስራ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ተወዳዳሪው ‘‘Smart Home System Lighting And Surveillance’’ በሚል ድርጅት ስም አሸናፊ በመሆን ሽልማቱ ሊበረከትለት ችሏል፡፡
በኅዳር ወር 2015 ላይ በይፋ የተጀመረውና ላለፉት ወራት ሲካሄድ የቆየው "አሚን አዋርድ" የሥራ ፈጠራ ውድድር መጠናቀቁን ተከትሎ በሥራ ፈጠራቸው ይዘት እና ችግር ፈቺነታቸው ለተመረጡ 5 ተወዳዳሪዎች የእውቅናና የሽልማት መርሐ-ግብር የተከናወነ ሲሆን፣በውድድሩ ላይ ከ1ኛ - 5ኛ ለወጡ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ በሽልማት መልክ ከተሰጠው ብር 2.5 ሚሊዮን የገንዘብ ሽልማት ባሻገር ከ6ተኛ- 20ኛ ለወጡ ተሳታፊዎችም የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
በዚህ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተወዳዳሪው የጅግጅጋ ከተማን ወክሎ ባስመዘገበው ውጤት ደስ መሰኘታቸውንና በተጨማሪም ላስመዘገበው ውጤት እውቅናን የሰጡ ሲሆን ባንካችን በስራ ፈጠራ ዙሪያ እየሰራ ያለውን ተጨባጭ ስራ በማድነቅ መሰናዶው እንዲቀጥል ከባንካችን ጎን እንዲሆኑ፤ተወዳዳሪውም የፈጠራ ውጤቱን ወደ ተግባር ለመቀየር በሚያረገው ጥረት ሂደት ምንግዜም በራቸው ክፍት መሆኑንና ሌሎችም የፋይናንስ ተቋማት የአቢሲንያ ባንክን ዓርአያ በመከተል ወጣት የስራ ፈጣሪዎችን እንዲያበረታቱ በመድረኩ ገልጸዋል፡፡