ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” ዘመቻ መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውድድሩም 329 በግጥም፣ እንዲሁም 37 በድምፅ በአጠቃላይ 366 ተሳታፊዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን በድምጽ ከተወዳደሩት ውስጥ ሁለት ተወዳዳሪዎች በውድድር ህጉ ውስጥ የተከለከለውን የሙዚቃ መሳሪያ መጠቀም ህግ በመተላለፋቸው ምክንያት ከውድድሩ ተሰርዘዋል፡፡ ለውድድር ከቀረቡት የሙዚቃና የግጥም ስራዎች ውስጥም ከእያንዳንዱ ዘርፍ አስር አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ ገጣሚ የዝና ወርቁ፣ ገጣሚ የምወድሽ በቀለ እና ገጣሚ የሺወርቅ ወልዴ የግጥም ስራዎችን በመገምገም፣ እንዲሁም የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት የሹምነሽ ታዬ እና ሜሮን ረጋሳ እንዲሁም ድምጻዊት ጠረፍ ካሳሁን የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡በቀጣይም ከእያንዳንዱ ማለትም ከግጥምና ሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭ እና አንባቢ ድምፅ 30% ፣እንዲሁም በዳኞች 70% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የሙዚቃ ስራዎች በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ የቀረቡ በመሆኑ ይህን ሊንክ በመጠቀም https://fb.watch/j_qrQrTIcF/ ከዛሬ ሚያዝያ 10፣ 2015 እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በፌስ ቡኩ ልጥፍ ኮመንት መስጫ ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡
በቀጣይም የተለዩት የግጥም ስራዎች እንዲሁ ለምርጫ የሚቀርቡ በመሆኑ ይከታተሉ፡፡
መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!
ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” ዘመቻ መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውድድሩም 329 በግጥም፣ እንዲሁም 37 በድምፅ በአጠቃላይ 366 ተሳታፊዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን በድምጽ ከተወዳደሩት ውስጥ ሁለት ተወዳዳሪዎች በውድድር ህጉ ውስጥ የተከለከለውን የሙዚቃ መሳሪያ መጠቀም ህግ በመተላለፋቸው ምክንያት ከውድድሩ ተሰርዘዋል፡፡ ለውድድር ከቀረቡት የሙዚቃና የግጥም ስራዎች ውስጥም ከእያንዳንዱ ዘርፍ አስር አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ ገጣሚ የዝና ወርቁ፣ ገጣሚ የምወድሽ በቀለ እና ገጣሚ የሺወርቅ ወልዴ የግጥም ስራዎችን በመገምገም፣ እንዲሁም የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህራን የሆኑት የሹምነሽ ታዬ እና ሜሮን ረጋሳ እንዲሁም ድምጻዊት ጠረፍ ካሳሁን የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በቀጣይም ከእያንዳንዱ ማለትም ከግጥምና ሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭ እና አንባቢ ድምፅ 30% ፣እንዲሁም በዳኞች 70% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የግጥም ስራዎች በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ የቀረቡ በመሆኑ ይህን ሊንክ በመጠቀም https://bit.ly/41n5N6a ከዛሬ ሚያዝያ 11፣ 2015 እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ በምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በፌስ ቡኩ ልጥፍ ኮመንት መስጫ ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡

መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!
ዛይራይድ በጋራ ሠርተን በጋራ እንደግ እያለ ባለቤትነቱን የሕዝብ ለማድረግ ለአሽከርካሪዎች እና ለማኅበረሰቡ የጀመረዉን የእክሲዮን ሽያጭ ቀጥሏል!
በዚህም መሰረት የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1,000 (አንድ ሺህ) ብር፣ የትንሹ አክሲዮን ግዢ ብዛት ለአሽከርካሪዎች 25 (ሃያ አምስት) አክስዮን ወይም ሃያ አምስት ሺህ (25,000) ብር ሲሆን ከአሽከርካሪዎች ውጪ ላሉት የማህበረሰባችን ክፍል ደግሞ 75 (ሰባ አምስት) አክስዮን ወይም ሰባ አምስት ሺህ (75,000) ብር ነው፡፡ የትልቁ አክስዮን ግዢ መጠን ደግሞ ለሁሉም አክስዮን ገዢዎች 5,000 (አምስት ሺህ) አክስዮን ወይም 5 ሚሊዮን ብር መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን፡፡ የክፍያ አፈጻጸምን በተመለከተ ደግሞ ለማንኛውም የአክስዮን መጠን ግዢ ክፍያ በቅድሚያ (በአክስዮን ግዢ ወቅት) በአንድ ጊዜ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን እያሳወቅን አክስዮኑን Visa እና Mastercard ተጠቅመው መግዛት እንደሚችሉ ስንገልፅ በደስታ ነው::
የአክስዮን ግዢውን በኦንላይን ለመፈፀም ከታች የሚገኘውን የዛይራይድ መስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡፡
www.zayride.com
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባንካችን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ኢድ ሙባረክ!


#AbyssiniaAmeen #IFB #bankofabyssinia
#Banking #BanksinEthiopia #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
We Are Hiring!

Bank of Abyssinia seeks to hire applicants for the positions of
1) Grade I Branch Business Manager

Place of Work: Chelelektu Branch (Hawassa District)
2) Senior Credit Underwriting Officer
Place of Work: Addis Ababa

Use the link below to apply for the vacancy
https://vacancy.bankofabyssinia.com
አፖሎን ተጠቅመው ቪዛ ካርድ ሲያዙ በ72 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ በተመችዎት ቦታ ካርድዎን እናደርስሎታለን

መተግበሪያውን ኣውርደው ካርድዎን ይዘዙ።

https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
ባንካችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ አካል የሆነውንና ለሁለተኛ ጊዜ ከአለም አቀፉ የሴቶች ቀን “ማርች 8” ጋር በተያያዘ ”እችላለሁ’’ በሚል መሪ ቃል በሴት ባለተሰጥኦዎች መካከል በግጥም፤በሙዚቃ፤ በቲክቶክ የማህበራ ሚዲያ አነሳሽነት እንዲሁም ሴት የስራ ፈጣሪዎች መካከል ባከናወነው ውድድር በየዘርፉ ከ1ኛ-3ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓም. በማሪዮት ኢንተርናሽናል ሆቴል ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ሽልማትና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

በዚህ መርሃ ግብር የድምፅ፤የግጥምና የቲክቶክ ተወዳዳሪች ተሰጥኦ ያላቸው እንስቶች እንዲወዳደሩ በማድረግ ስራቸውን ካቀረቡት 37 የድምፅ ተወዳዳሪዎች፤ 326 የግጥም ተወዳዳሪዎች እና 18 ቲክቶከሮች መካከል በዳኞችና በአድማጭ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ሶስት ሶስት አሸናፊዎች ተለይተው ለሽልማት በቅተዋል፡፡

በሥነስርዓቱም በሶስቱም ዘርፍ 1ኛ ለወጡት የብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ 2ኛ ለወጡት የብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) እንዲሁም 3ኛ ለወጡት የብር 30,000.00 (ስላሳ ሺህ ብር) ሽልማት የተበረከተ ሲሆን በፕሮግራሙም ላይ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡በዚህም

በግጥም ዘርፍ
1ኛ ዮዲት መኮንን
2ኛ በአምላክ በለው
3ኛ ፋንታነሽ አበባው
በሙዚቃ ዘርፍ
1ኛ ህይወት ሰለሞን
2ኛ ሀመልማል ቃለአብ
3ኛ ኤደን አበባየሁ
በቲክቶክ ዘርፍ
1ኛ ዮርዳኖስ ሽመልስ
2ኛ በእምነት ከፍያለው
3ኛ ወንጌላዊት እንድርያስ


በሌላ በኩል የውድድሩ ሌላኛው አካል በነበረው የተሻለ የሥራ ፈጠራዎችን የማቅረብ ውድድር ላይ ለአሸናፊዎቹ ከገበያው በአነሰ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ድረስ ብድር መመቻቸቱ ተገልጿል፡፡በዚህም ዘርፍ ለ50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳቸው የ500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) ብድር በድምሩ 25,000,000(ሀያ አምስት ሚሊዮን ብር) ብድር መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
#Ican #Adeysaving #zaharasaving #women saving