የሴቶች የስራ ፈጠራ፣ የሙዚቃና የግጥም ውድድር !
ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ በያዝነው የአውሮፓውያን ወር ከማርች8-31, 2022 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡
1 የግጥምና የሙዚቃ ተሰጥኦ ውድድር
ባንካችን የግጥምና የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ በእዚህም መሰረት አንደኛ ለምትወጣው የብር 50000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 30000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 20000 ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡

በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth መቀላቀል ይኖርባችኋል፡፡ በመቀጠልም በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦየን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት(3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ኢ-ሜይል መላክ ይኖርባችኋል፡፡
እንዲሁም በግጥም ዘርፍ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተሳታፊዎች ከ20 መሰመር ስንኝ ያልበለጠ ስለሴት ወይም ሴትነት የተዘጋጀ ግጥም ከዚህ በታች በተቀመጠ ኢ-ሜይል መላክ ይኖርባችኋል፡፡
[email protected]
2) የስራ ፈጠራ ውድድር
የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ካሉት 10 ዲስትሪክቶች ከእያንዳንዱ ሶስት(3) የስራ ፈጣሪዎችን በአጠቃላይ 30 የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት10 ቀን 2014 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በእዚህ አጋጣሚ ለሴቶች ደንበኞቻችን የተዘጋጁትን የመደበኛ አደይና የወለድ አልባ ዘሃራ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቅሞችን እንድታገኙ እንጋብዛለን፡፡
መልካም የሴቶች ቀን! #Ican

Facebook (https://www.facebook.com/BoAeth)
Bank of Abyssinia
A private commercial Bank based in Ethiopia The Gambia st, Legehar, Bank of Abyssinia Head Office,, Addis Ababa, Ethiopia
በግጥም ስራዎች ላይ የሚደረገው ምርጫ ተጠናቋል፣ አሁን ደግሞ በሙዚቃ ምርጫ ላይ ይሳተፉ!
#Ican
ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ” ዘመቻ የውድድር ሥራዎች ማቅረቢያ ቀን እሑድ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በውድድሩም 318 በግጥም፣ እንዲሁም 33 በድምፅ በአጠቃላይ 351 ተሳታፊዎች ስራቸውን አቅርበዋል፡፡ ለውድድር ከቀረቡት የሙዚቃና የግጥም ስራዎች ውስጥም ከእያንዳንዱ ዘርፍ አስር አስር ስራዎች በባለሙያዎች ተገምግመው ለመጨረሻው የታዳሚዎች ምርጫ የተለዩ ሲሆን፣ አርቲስት ጌትነት እንየው፣ ገጣሚ ረድኤት ተረፈ እና ገጣሚ የሺወርቅ ወልዴ የግጥም ስራዎችን በመገምገም፣ እንዲሁም ሙዚቀኛ የሹምነሽ ታዬ እና ሙዚቀኛ ሜሮን ረጋሳ የሙዚቃ ስራዎችን በመገምገም ስራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡በቀጣይም ከእያንዳንዱ ማለትም ከግጥምና ሙዚቃ ዘርፍ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚወጡት ባለተስጥኦዎች በአድማጭና አንባቢ ድምፅ 50% ፣እንዲሁም በዳኞች 50% ነጥብ የሚለዩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር የተለዩት አስር የሙዚቃ ስራዎች በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ የቀረቡ በመሆኑ ይህን ሊንክ በመጠቀም https://fb.watch/c7Rm3F8uXy/ ከዛሬ መጋቢት 24፣ 2014 እስከ መጋቢት 26 ቀን 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ የተወዳዳሪዎችን በምስሉ ላይ የሚገኘውን መለያ ኮድ በመጠቀምና የመረጣችሁትን በኮመንት ሥፍራ ላይ በመፃፍ የድምፅ አሰጣጥ ተሳትፎ እንድታደርጉ እንጋብዛለን፡፡
መልካም ዕድል ለተሳታፊዎች!
በግጥም ስራዎች ላይ ምርጫ በማካሄድ የድምጽ ተሳትፎ ላደረጋችሁ እናመሰግናለን፡፡
በየአመቱ ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ “እችላለሁ”የግጥምና የሙዚቃ ውድድር አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!
በቀጣይም የሽልማት ሥነ-ስርዓቱ የሚካሄድበትን ቀን በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
#Ican #Banking #BankofAbyssinia #AbyssiniaBank #Ethiopia #Adey #Zahrah #የሁሉም_ምርጫ
የ”እችላለሁ” የሴቶች የስራ ፈጠራ ውድድር አሸናፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
ባንካችን አቢሲንያ የሴቶች የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ለአሸናፊዎቹ ከገበያው ባነሰ የወለድ ምጣኔና ካለምንም መያዣ እስከ ብር 300,000.00(ሶስት መቶ ሺ ብር ) ድረስ ብድር ማመቻቸቱ ይታወሳል፡፡ ስራቸውን ለማሳደግ የሚተጉ ዜጎችን ለማበረታታት ባንካችን ከጎናቸው መቆሙን የሚቀጥልበት ሲሆን ከ”እችላለሁ” ውድድር አሸናፊዎች የተወሰኑት ያላቸውን አስተያየት ለዛሬ አቅርበንላችኋል፡፡

#BankofAbyssinia #ICAN #woman #የሁሉም_ምርጫ
2ኛ ዙር እችላለሁ!
የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃ፣ የግጥምና የቲክቶክ ቪዲዮ ውድድር !

ባንካችን በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ በያዝነው የአውሮፓውያን ወር ከማርች 8-31, 2023 ድረስ በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት አድርጓል፡፡

1) የግጥም፣ የሙዚቃና የቲክቶክ ቪዲዮ ተሰጥዖ ውድድር
ይህ ውድድር የሚከናወነው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓም. ሲሆን ባንካችን የግጥምና የሙዚቃ ተሰጥኦ ያላቸውን ሴት ተሳታፊዎችን በማወዳደር በባለሙያና በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰጥ የህዝብ ድምጽ የተለዩ አሸናፊዎችን በየደረጃው ይሸልማል፡፡ በዚህም መሰረት አንደኛ ለምትወጣው የብር 100,000፣ ሁለተኛ ለምትወጣው የብር 60,000 እንዲሁም ሶስተኛ ለምትወጣው የብር 30,000 ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡
በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች አስቀድማችሁ የአቢሲንያ ባንክ የፌስቡክ ገፅን https://www.facebook.com/BoAeth/ መወዳጀት ይኖርባችኋል፡፡ በመቀጠልም በሙዚቃው ዘርፍ ተሰጥኦዬን ያሳያል የምትሉትን ከሶስት (3) ደቂቃ ያልበለጠ የሙዚቃ ሥራ ያለ ሙዚቃ መሣሪያ በቪዲዮ ሰርታችሁ ከዚህ በታች በተቀመጠው ቴሌግራም መላክ ይኖርባችኋል፡፡
በግጥም ዘርፍ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተሳታፊዎች ከ20 መሰመር ስንኝ ያልበለጠ ስለሴት ወይም ሴትነት የተዘጋጀ ግጥም ከዚህ በታች በተቀመጠ የቴሌግራም አድራሻ መላክ ይኖርባችኋል፡፡
እንዲሁም በተመረጡ ቲክቶከሮች መካከል ባንካችን ለሴት ደንበኞቻችን ያዘጋጃቸውን አደይና ዘሃራ የቁጠባ ሂሳቦችን በተለየ መንገድ የማስተዋወቅ ውድድር ይካሄዳል፡፡
የቴሌግራም አድራሻ------------0973875782 ወይም 0953433355

2) የሥራ ፈጠራ ውድድር
የሴት ሥራ ፈጣሪዎችን ለማበረታት ባንኩ ካሉት 10 ዲስትሪክቶች ከእያንዳንዱ አምስት(5) የስራ ፈጣሪዎችን በአጠቃላይ 50 የሥራ ፈጣሪ ሴቶችን በመምረጥ በአነስተኛ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የብድር አገልግሎት ለመስጠት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቶችን የምታሟሉ የሥራ ፈጣሪዎች አቅራቢያችሁ ባሉ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ፅ/ቤቶች በመቅረብ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓም. ባሉት ቀናት ብቻ በፁሑፍ ጥያቄያችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለሴቶች ደንበኞቻችን የተዘጋጁትን የመደበኛ አደይና የወለድ አልባ ዘሃራ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቅሞችን እንድታገኙ እንጋብዛለን፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ከዚህ በታች ያግኙ፡፡
መልካም የሴቶች ቀን!
#Ican
# 2ኛ ዙር እችላለሁ! ተራዝሟል

ማርች 8 የሚከበረውን የሴቶች ቀን አስመልክቶ ሴት ባለተሰጥኦዎችን በማሳተፍ በባንካችን ሲካሄድ የነበረው የ የ2ኛው ዙር “እችላለሁ” ዘመቻ የውድድር ሥራዎች ማቅረቢያ ቀን ተራዘመ!
//
ባንካችን በየዓመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ ፣ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓም. ድረስ የ2ኛው ዙር እችላለሁ የሴቶች የሥራ ፈጠራ፣ የሙዚቃ፣ የግጥምና የቲክቶክ ቪዲዮ፤በሁለት የተከፈሉ ውድድሮችን አዘጋጅቶ ለተሳታፊዎች ክፍት ማድረጉ ይታወቃል፡፡
አንዳንድ ተሳታፊዎች የኢንተርኔት መቆራረጥ ስራቸውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ለመላክ እንዳላስቻላቸው ስላሳወቁን እንዲሁም ለተሳታፊዎች ሰፋ ያለ ዕድል መሰጠቱ ተገቢ ነው ብሎ ባንካችን ስላመነ የውድድር ሥራዎችን የማስረከቢያ ቀን እስከ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
በዚህም መሠረት በመርሃ-ግብሩ መሳተፍ የምትፈልጉ ሴት ተወዳዳሪዎች የምትወዳደሩበትን የጥበብ ሥራ በቴሌግራም አድራሻ------------0973875782 ወይም 0953433355 መላክ ትችላላችሁ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለሴቶች ደንበኞቻችን የተዘጋጁትን የመደበኛ አደይና የወለድ አልባ ዘሃራ አገልግሎቶችን በመጠቀም የተሻሉ ጥቅሞችን እንድታገኙ እንጋብዛለን፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ለመመልከት ከታች የሚገኘውን የቴሌግራም ሊንክ መጠቀም የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
https://yangx.top/BoAEth/803
#Ican
ባንካችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ አካል የሆነውንና ለሁለተኛ ጊዜ ከአለም አቀፉ የሴቶች ቀን “ማርች 8” ጋር በተያያዘ ”እችላለሁ’’ በሚል መሪ ቃል በሴት ባለተሰጥኦዎች መካከል በግጥም፤በሙዚቃ፤ በቲክቶክ የማህበራ ሚዲያ አነሳሽነት እንዲሁም ሴት የስራ ፈጣሪዎች መካከል ባከናወነው ውድድር በየዘርፉ ከ1ኛ-3ኛ ለወጡት ተወዳዳሪዎች ሚያዚያ 20 ቀን 2015 ዓም. በማሪዮት ኢንተርናሽናል ሆቴል ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ሽልማትና የምስክር ወረቀት አበርክቷል፡፡

በዚህ መርሃ ግብር የድምፅ፤የግጥምና የቲክቶክ ተወዳዳሪች ተሰጥኦ ያላቸው እንስቶች እንዲወዳደሩ በማድረግ ስራቸውን ካቀረቡት 37 የድምፅ ተወዳዳሪዎች፤ 326 የግጥም ተወዳዳሪዎች እና 18 ቲክቶከሮች መካከል በዳኞችና በአድማጭ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ድምፅ ያገኙት ሶስት ሶስት አሸናፊዎች ተለይተው ለሽልማት በቅተዋል፡፡

በሥነስርዓቱም በሶስቱም ዘርፍ 1ኛ ለወጡት የብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ 2ኛ ለወጡት የብር 60,000.00(ስልሳ ሺህ ብር) እንዲሁም 3ኛ ለወጡት የብር 30,000.00 (ስላሳ ሺህ ብር) ሽልማት የተበረከተ ሲሆን በፕሮግራሙም ላይ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡በዚህም

በግጥም ዘርፍ
1ኛ ዮዲት መኮንን
2ኛ በአምላክ በለው
3ኛ ፋንታነሽ አበባው
በሙዚቃ ዘርፍ
1ኛ ህይወት ሰለሞን
2ኛ ሀመልማል ቃለአብ
3ኛ ኤደን አበባየሁ
በቲክቶክ ዘርፍ
1ኛ ዮርዳኖስ ሽመልስ
2ኛ በእምነት ከፍያለው
3ኛ ወንጌላዊት እንድርያስ


በሌላ በኩል የውድድሩ ሌላኛው አካል በነበረው የተሻለ የሥራ ፈጠራዎችን የማቅረብ ውድድር ላይ ለአሸናፊዎቹ ከገበያው በአነሰ የወለድ ምጣኔና ካለመያዣ እስከ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ድረስ ብድር መመቻቸቱ ተገልጿል፡፡በዚህም ዘርፍ ለ50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳቸው የ500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር) ብድር በድምሩ 25,000,000(ሀያ አምስት ሚሊዮን ብር) ብድር መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡
#Ican #Adeysaving #zaharasaving #women saving
ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውና የተለያዩ ውድድሮችን ያካተተው 3ኛው ዙር “እችላለሁ”ዘመቻ በይፋ ተጀምረ!


ባንካችን አቢሲንያ የሴቶችን የፋይናንስ አካታችነት (Financial Inclusion) ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለመወጣት ለሴቶች የተሻለ ጥቅም የሚያስገኙ አደይና ዛሃራ የተሰኙ የሴቶች የቁጠባ ሂሳቦችን ማቅረቡ ይታውቃል፡፡ አገልግሎቱን መሰረት በማድረግ በየአመቱ የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) አስመልክቶ ለሶስትኛ ጊዜ እችላለው በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ውድድር ይፋ አድርጓል ።ውድድሩ የካቲት 29 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓም. ድረስ በሶስት የተለያዩ የውድድር ዘርፎች የሚካሂድ መሆኑን አስታውቋል። #ICAN
ባንካችን አቢሲንያ የአለም አቀፉን የሴቶች ቀን ማርች 8 በማስመልከት ለ 3ኛ ግዜ “ እችላለሁ “ በሚል መሪ ቃል ልዩ ልዩ ዉድድሮችን ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 21 እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህ መርሀ ግብር ላይ በግጥም፣ በሙዚቃ፣ በቲክቶከሮች መካከል የሚደረግ ዉድድር የሚከናወን ይሆናል፡፡ ከዚህ በፊት ባንኩ በሁለት ዙር ባከናወናቸዉ የ “ እችላለሁ “ ዘመቻ በመጀመሪያዉ ዙር ለ 27 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳንዳቸዉ 300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብር ) በሁለተኛዉ ዙር ደግሞ ለ 50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳንዳቸዉ 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር ) በዝቅተኛ ወለድ ያለመያዣ ብድር አዘጋጅቶ ለባለእድለኞች መስጠቱ ይታወሳል፡፡
በዚህ ዙርም በተመሳሳይ ለ 50 የስራ ፈጣሪ ሴቶች ለእያንዳንዳቸዉ 500,000 (አምስት መቶ ሺ ብር ) ያዘጋጀን ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ሴቶች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡ ከባለፈው ዓመት የእድሉ ተጠቃሚዎች መካከልም ሁለቱ አሸናፊዎች ያሉትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
ዝርዝር የብድር እንዲሁም የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ከዚህ በታች የሚገኘውን የቴልግራም ሊንክ ያግኙ፡፡
https://yangx.top/BoAEth/1146
#march8 #womansday #ican #Savings #enterpreneur
#BankofAbyssinia #Abyssinia #Banking #BankingService #Digital #DigitalEthiopia #DigitalPayment #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ