WANAW SPORT
10.6K subscribers
2.52K photos
53 videos
1.29K links
የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ በኢትዮጵያ 🇪🇹 Sportswear provider in Ethiopia!

📍ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለተጨማሪ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።
加入频道
📜 #ዋናው_ትውስታ!

የስፖርት ልብሶች ከየት ወዴት?

#ክፍል_ሁለት

● በ20ኛው ክፍለ ዘመን የስፖርት ልብሶች ዲዛይን በፋሽን ኢንዱስትሪው መዘመን እና በጨርቅ ቴክኖሎጂ ማደግ ምክንያት እጅጉን ተሻሻለ። እ.ኤ.አ. በ1920ዎቹ ውስጥ ከታዩ ተጠቃሽ እድገቶች መካከል ንፋስ መከላከያ ያላቸው ቀላል ጃኬቶች ብሎም ውሃንና የአየር ንብረት ለውጦችን የሚቋቋሙ ጃኬቶች፣ ወደ መዝናኛ ስፖርቶች የሚያደሉ አልባሳት ይጠቀሳሉ።

● የ20ኛው ክፍለ ዘመን እየገፋ ሲሄድ፣ የስፖርት ልብሶች ከተለዋዋጩ የፋሽን ባህል ጋር እየተላመዱ መጡ። እንደ ቶሚ ሂልፊገር እና ራልፍ ላውረን ያሉ ታዋቂ ዲዛይነሮች ብቅ ሲሉም በ1970ዎቹ የስፖርት ልብስ ፋሽን ታላቅ ለውጥ አሳየ። ለታየው ለውጥ እንደ ዋነኛ ማሳያነት የሚቆጠረውም #የቱታዎች በአትሌቲክስ ፋሽን ውስጥ የላቀ እንቅስቃሴ ምልክት መሆንና ታዋቂነታቸው በእጅጉ መጨመሩ ነው። ቱታዎች በዕለት ከዕለት የስፖርት እንቅስቃሴዎች ውስጥም ተዘውትረው መለበስ ጀመሩ።

● እ.ኤ.አ. በ 1980-90ዎቹ በስፖርት ልብስ እና በዕለት ከዕለት ፋሽን መካከል ያለውን ድንበር ያደበዘዘ ጉልህ አዝማሚያ ታየ። ይህ የፋሽን እንቅስቃሴ ምቾትን፣ ተግባራዊነትን እና ውበትን በማጣመር በአትሌቲክስ ልብሶችና የዕለት ከዕለት ልብሶችን ውህድነትን አስተዋወቀን። እንደ የጂም ልብሶች፣ ባለኮፍያ ሹራቦች፣ ስኒከር ጫማዎች ወዘተ ያሉ አልባሳት ከጂም ባሻገር እንደ ፋሽን የሚለብሱ ሆኑ፣ ይህም በጊዜው የሰዎችን የበለጠ ዘና ያለ እና ንቁ የአኗኗር ዘይቤን መከተል መጀመርን ያሳየን ነበር።

#ይቀጥላል...

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear‌‌