📜 #ዋናው_ትውስታ!
የስፖርት ልብሶች ከየት ወዴት?
#ክፍል_አንድ
● የስፖርት አልባሳት ኢንዲስትሪ ከአጀማመሩ አንስቶ እስከ አለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ያሳየው ለውጥ እጅግ በጣም አስደናቂ ነው። የስፖርት ልብሶች በየጊዜው እየተሻሻሉ ወደ የላቀ ሁለንተናዊ ደረጃ እየደረሱ ነው። ይህንን የስፖርት ልብሶችን ታሪክና ለውጥ በአጭር እይታ እንመለከታለን።
● በ 19ኛው ክፍለ ዘመን ስፖርት በተደራጀ መንገድ እየተዘወተረ ሲመጣ ብሎም ለአትሌቲክስ ውድድሮች ተስማሚ አለባበስ ስላስፈለገ የስፖርት ልብሶች ተቀባይነታቸው እያደገ መጣ። ዛሬ ላይ ስንመለከታቸው የሚያስቁን፣ ለመልበስም አዳጋች የሆኑት የወቅቱ ስፖርታዊ አለባበሶች በጊዜው በጣም ተወዳጅ የነበሩና እንደ ፋሽንም ይቆጠሩ የነበሩ ናቸው።
● በክፍለ ዘመኑ መገባደጃ ላይ የስፖርት ውድድሮች የበለጠ አፎካካሪ እየሆኑ ሲሄዱ አትሌቶችና ተጫዋቾች ለተሻለ አፈፃፀምና ምቾት ልዩ ልብስ እንደሚያስፈልጋቸው ይበልጥ እየተገነዘቡ መጡ። ይህን የተረዱት የትጥቅ አምራች ድርጅቶችም ብዙ ገንዘብ ወደ ኢንዱስትሪው ፈሰስ በማድረግ፣ የስፖርት ልብሶችን በማዘመን አሁን ለምናውቃቸውና ለምንወዳቸው ለመልበስ ቀላል የሆኑ፣ ምቹና እንደልብ የሚያንቀሳቅሱ ልብሶች መመረት መጀመር ትልቁን መሰረት እንደጣሉ የታሪክ መዛግብት ያስረዱናል።
#ይቀጥላል...
Instagram | Facebook | TikTok
🏅ዋናው ወደፊት...
@wanawsportwear

#ክፍል_ሁለት
● በ20ኛው ክፍለ ዘመን የስፖርት ልብሶች ዲዛይን በፋሽን ኢንዱስትሪው መዘመን እና በጨርቅ ቴክኖሎጂ ማደግ ምክንያት እጅጉን ተሻሻለ። እ.ኤ.አ. በ1920ዎቹ ውስጥ ከታዩ ተጠቃሽ እድገቶች መካከል ንፋስ መከላከያ ያላቸው ቀላል ጃኬቶች ብሎም ውሃንና የአየር ንብረት ለውጦችን የሚቋቋሙ ጃኬቶች፣ ወደ መዝናኛ ስፖርቶች የሚያደሉ አልባሳት ይጠቀሳሉ።
● የ20ኛው ክፍለ ዘመን እየገፋ ሲሄድ፣ የስፖርት ልብሶች ከተለዋዋጩ የፋሽን ባህል ጋር እየተላመዱ መጡ። እንደ ቶሚ ሂልፊገር እና ራልፍ ላውረን ያሉ ታዋቂ ዲዛይነሮች ብቅ ሲሉም በ1970ዎቹ የስፖርት ልብስ ፋሽን ታላቅ ለውጥ አሳየ። ለታየው ለውጥ እንደ ዋነኛ ማሳያነት የሚቆጠረውም #የቱታዎች በአትሌቲክስ ፋሽን ውስጥ የላቀ እንቅስቃሴ ምልክት መሆንና ታዋቂነታቸው በእጅጉ መጨመሩ ነው። ቱታዎች በዕለት ከዕለት የስፖርት እንቅስቃሴዎች ውስጥም ተዘውትረው መለበስ ጀመሩ።
● እ.ኤ.አ. በ 1980-90ዎቹ በስፖርት ልብስ እና በዕለት ከዕለት ፋሽን መካከል ያለውን ድንበር ያደበዘዘ ጉልህ አዝማሚያ ታየ። ይህ የፋሽን እንቅስቃሴ ምቾትን፣ ተግባራዊነትን እና ውበትን በማጣመር በአትሌቲክስ ልብሶችና የዕለት ከዕለት ልብሶችን ውህድነትን አስተዋወቀን። እንደ የጂም ልብሶች፣ ባለኮፍያ ሹራቦች፣ ስኒከር ጫማዎች ወዘተ ያሉ አልባሳት ከጂም ባሻገር እንደ ፋሽን የሚለብሱ ሆኑ፣ ይህም በጊዜው የሰዎችን የበለጠ ዘና ያለ እና ንቁ የአኗኗር ዘይቤን መከተል መጀመርን ያሳየን ነበር።

#ክፍል_ሶስት - የመጨረሻ ክፍል
● ከ1970ዎቹ እስከ 2000ዎቹ እንደ ቶሚ ሂልፊገር እና ራልፍ ላውረን ያሉ ዲዛይነሮች ብቅ በማለታቸው የስፖርት ልብስ ፋሽን በከፍተኛ ደረጃ ማደግን ተመልክተናል። የቱታዎች ታዋቂ የአትሌቲክስ አልባሳት መሆንንና በዕለት ከዕለት አለባበስ ዘንድ ተወዳጅነት ማግኘትንም አይተናል፣ ዛሬ ከ2000ዎቹ በኋላ ስለነበረው አስደናቂ ለውጥ እንመለከታለን።
● በ2000ዎቹ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስፈላጊ እየሆነ በመጣ ቁጥር የግል ዘይቤንና እሴቶችን በማንፀባረቅ በአፈፃፀም የላቁ የስፖርት ልብሶች ፍላጎት እየጨመረ ሄደ። ቀጥሎም የ #ስኒከር_ጫማዎች 2000ዎቹን አጥለቀለቁ፣ እንደ ናይክ፣ አዲዳስ እና ጆርዳን ያሉ ታዋቂ ብራንዶችም ገበያውን በፍጥነት ተቆጣጠሩ። እነዚህ የስፖርት አልባሳት ብራንዶች አክለውም ከስፖርቱ አልፈው ተደራሽነታቸውን በማስፋት በስፖርት እና ፋሽን መካከል ውህደትን በመፍጠር፣ ከፋሽን ዲዛይነሮች እና ታዋቂ ሰዎች ጋር ይበልጥ በመተባበር የተጠቃሚዎች የዕለት ከዕለት ህይወት አካልም ሆኑ።
● በአጠቃላይ እ.ኤ.አ. 2000ዎቹ ውስጥ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ መጨመር፣ በቴክኖሎጂ እድገቶች፣ በስኒከር ባህል ማደግ፣ እና በስፖርትና ፋሽን ውህደት አማካኝነት በስፖርት ልብስ ታሪክ ውስጥ ታላቅ የለውጥ ጊዜን አሳይተውናል። እነዚህ ለውጦች ዛሬም የስፖርት አልባሳት ኢንዱስትሪውንና የተጠቃሚዎችን ምርጫዎች መቅረፅን ቀጥለዋል። የቴክኖሎጂ፣ የዘላቂነት እና የዲዛይን ጥበብ በፍጥነት መገስገስ የስፖርት አልባሳትን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እጅጉን ብሩህ ያደርገዋል።
Instagram | Facebook | TikTok
🏅 ዋናው ወደፊት...

ቀዳሚው የማሊያ ስፖንሰርሺፕ የቱ ነበር?
ብዙ የእግር ኳስ ታሪክ ጸሃፍት እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ የማሊያ ላይ ስፖንሰርሺፕ ጽንሰ-ሃሳብን ወደ እግር ኳስ ስፖርት ዓለም በተወሰነ ረገድ በማስተዋወቅ “ፔናሮል” የተባለውን የኡራጓይ እግር ኳስ ክለብ ጀማሪ ቢያደርጉትም፣ የታሪክ መዛግብት ግን የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ "አይንትራክት ብራውንሽቫይግ/Eintracht Braunschweig" እ.ኤ.አ በ1973 “ዬገርማይስተር/Jägermeister” ከተባለው ብራንድ ጋር የማሊያ ስፖንሰር ስምምነት በማድረግ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው ኘሮፌሽናል ቡድን እንደነበር ያሳዩናል።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የስፖርት ስፖንሰርነቶች ለስፖርት ቡድኖች እና ለስፖርት ብራንዶች ዋነኛ የገቢ ምንጭ ሆነዋል።

የዓለማችን እጅግ ታዋቂው ጫማ - ኤይር ጆርዳን!
በዓለማችን ላይ እጅግ ታዋቂና ተወዳጅ ከሆኑት የስፖርት ብሎም የአዘቦት ጫማዎች መካከል ዋነኛ የሆነው የመጀመሪያው የናይክ ኤይር ጆርዳን (Nike Air Jordan) ጫማ በወቅቱ የአሜሪካው ቺካጎ ቡልስ ቅርጫት ኳስ ቡድን ተጫዋች ለነበረው ለእውቁ የቅርጫት ኳስ ጥበበኛ ማይክል ጆርዳን እ.ኤ.አ. ህዳር 17 ቀን 1984 በልዩ ሁኔታ ተመርቶ፣ ለህዝብ በይፋ የቀረበው እ.ኤ.አ በሚያዝያ 1 ቀን 1985 ነበር።