Trust Agro-consulting and farming P.L.C ትረስት አግሮ-ኮንሰልቲንግ ኤንድ ፋርሚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
6.44K subscribers
1.24K photos
36 videos
4 files
291 links
Trust Agro-consulting is a multi-dimensional agricultural consulting firm based in Bishoftu, Ethiopia that operates across the country.
Email: [email protected]
celphone:
+251919076607
+251932314562
加入频道
ገበያ አይዋሽም!

#Ethiopia | የእንቁላል ዋጋ ተወዷል። ጾም ገብቶም ዋጋው አልወረደም። ይህ ለምን ሆነ? ይህ የሆነው ለገበያው እየቀረበ ያለው የእንቁላል መጠን ከፍላጎቱ ያነሰ ስለሆነ ነው።

የእንቁላል ዋጋ ወርዶ 5 ብር የደረሰበት ጊዜ ነበር። ያኔ ብዙ የእንቁላል ዶሮ የሚያረባ ሰው ነበር። ሆኖም የመኖ ዋጋ ውድ ነበር። አርቢውም ከዛሬ ነገ ይሻላል በሚል እየከሰረ ዶሮ ማርባቱን ቀጠለ።

መኖ ለምን ተወደደ? የመኖ ዋና ግብዓቶች በቆሎና አኩሪ አተር በፀጥታ ችግር፣ ከውጭ የሚመጡ ግብዓቶች ዋጋ ደግሞ በዶላር ምንዛሪ መወደድ ምክንያት የመኖ ዋጋ ናረ። በዚህ የተነሳ ዶሮ አርቢዎቹ ከሰሩ። በኪሳራ መቀጠልም አልቻሉም። መኖ መግዣ እስኪያጡ ተቸገሩ።

የከሰሩ አርቢዎች የገና በዓልን ጠብቀው የእንቁላል ዶሮዎችን ለበዓል እርድ ሸጡ። ከዚያ በኋላ የእንቁላል እጥረት ተፈጠረ፤ ዋጋውም ቀስ እያለ ወደላይ ወጣ። ከ8 ብር ተነስቶ 9፣ 10፣ 12፣ 15፣ 17 እያለ የእንቁላል ዋጋ 20 ብር ገባ። አሁን መኖውን የሚመጥን ዋጋ ላይ ነው።

የሁዳዴ ጾም ሲገባ የእንቁላል ዋጋ ይቀንሳል ቢባልም ዋጋው አልቀነሰም። ምክንያቱም ፍላጎቱ አልቀነሰም። የረመዳን መግባትም ዋጋውን እንዳይቀንስ ያደርገዋል።

Trust the market. ገበያን እመነው። ገበያ አይዋሽም። ገበያ የሚመራው በአቅርቦትና ፍላጎት የሚዛን ጨዋታ ነው። ዋጋ የሚንረውም፣ ግርግር የሚበዛውም እጥረት ሲኖር ነው።

ገበያን እመነው!

የነዳጅ እጥረት አለ። ለዚህ ምልክቱ በየቦታው የሚታየው ሰልፍ ነው። እጥረት ከሌለ በቀር ያ ሁላ ሰልፍ አይኖርም። በቂ ነዳጅ አለ ቢባልም በየማደያው ያለው ሰልፍ አሳሳቢና እጥረት መኖሩን ጠቋሚ ነው።
በተለይ የናፍጣ እጥረት አሳሳቢ ነው። የጭነት መኪና ሲቆም የሸቀጦች አቅርቦት ይዳከማል፣ ዋጋቸውም ይንራል። ነገሩ ተያያዥ ነው። ችግሩን ለመፍታት ግን ውስብስብ አይደለም።

እንዲህ እጥረት ሲኖር የነዳጅ ዋጋ በኩንትሮባንድ ይሀን በቀጥታ ዋጋው ይጨምራል። መንግስትም የዋጋ ጭማሪ ያደርጋል።

እያለ እያለ የወር ወጪህ ይንራል።

የኢኮኖሚው ብልሃት ገና አልተገኘም።
እንደ ህዝብ ብዛታችን በአስደንጋጭ ፍጥነት ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው። አሁን ከ130 ሚሊየን በላይ ሆነናል። ከዓለም ሀገራት ጋር ሲነጻጸር ቀድሞ ከነበርንበት 12ኛ ደረጄ ጃፓንና ሜክሲኮን ቀድመን 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠናል። ኢኮኖሚያችን ግን 100ኛ ደረጃ ላይም የለም።

የህዝብ ቁጥር ሲያድግ ፍላጎት ይጨምራል። ምግብ ልብስ መጠለያ፣ መድሃኒት፣ ነዳጅ፣... ፍላጎታቸው ይጨምራል። በዚያው ልክ አቅርቦት ካልጨመረ በስተቀር የፍላጎት ናዳው ችግር ውስጥ ይከተናል።

መፍትሔው አንድና አንድ ነው። አቅርቦትን መጨመር!

አቅርቦት ለመጨመር ምርትን ማብዛት ነው። ለዚህ መፍትሔው ታክስ ቀንሶ አምራች ኢንቨስተርን መሳብ፣ ሠራተኛን ማሰልጠን፣ መሬት በስፋት ማቅረብ እና የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ማስፋት ናቸው። እነዚህ ሁሉ ግን የፖሊሲ ማሻሻያ ይፈልጋሉ።

የፖሊሲ ለውጥ በ6 ወራት ውስጥ የተጠበቀው ውጤት ካልታየ ችግር አለ።

የኢኮኖሚያችን መፍትሔ ብዙ ምርምር አይፈልግም። ያልታረሱትን መሬቶች ማረስ፣ ታክስ ቀንሶ ኢንቨስተሮችን መሳብ፣ የንግድ ስርዓቱ ላይ ያለ ቁጥጥርን መቀነስ፣ የፀጥታ ችግርን መፍትሔ መስጠት እና የመንግስት ሠራተኛን ቀንሶ አምራች ኃይል ማድረግ ናቸው።

ለምን ዙሪያ ጥምጥም እንደምንሄድ አይገባኝም።

የፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ምን እያደረገ ነው?

ከየትም የሚገኝ ጠቃሚ ተሞክሮ ስናይ ትምህርት ወስዶ መፍትሔ ማምጣት ላይ ማተኮር  አስፈላጊ ነው።

ገበያ አይዋሽም! ኑሮ ከተወደደ ችግሩ ያለው ፖሊሲው ላይ ነው።

የደራው መጽሔት፤ ፀሐይ አትጠልቅም!

#get toughe Zer
ሃሳብ፣ መረጃ፣እውቀት ለሁላችንም በተለይ በእርባታ ውስጥ ላለን እና መግባት ለምንፈልግ በእጅጉ ይጠቅመናል።
ለዚህም ነው ከሃሳብ እስከ ተግባር  በሙሉ አቅማችን የምናስተምረው።
የ44ኛ ዙር ሰልጣኞች ፎቶ በከፊል።
45ኛ ዙር ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ስልጠና
❇️ በ600ሺ ብር ኢንቨስትመንት በየወሩ 100ሺ ብር ትርፍ የሚያገኙበት የዘመናችን ምርጥ ቢዝነስ
🔰ከመጋቢት 11-13 ለተከታታይ 3ቀናት
🔰እጅግ በምቹ ስፍራ በተመጣጣኝ ዋጋ
🔰 ከስልጠና በኃላ ፋርም  እናቋቁማል
🔰  የስልጠና ፓኬጅ፡ ምዝገባ፣ስልጠና፣ሰርተፍኬት፣ሻይ ቡና፣ደብተር፣የፋርም ጉብኝት
🔰 የስልጠና ዋጋ፡ 2950 ቫትን ጨምሮ
🔰 የስልጠና ቦታ፣ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ
🔰 ለመመዝገብ
ማስፈጠርያውን  ተጭነው ይሙሉ: https://forms.gle/3s8cyUz5u2TWxE9j8
🔰 አልያም በ0932042222/0116677008 ይደውሉ