TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
TIKVAH-SPORT
ሉሲዎቹ ተጋጣሚያቸውን ቀጣይ ሳምንት ያውቃሉ ! የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለፓሪሱ የኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን ተጋጣሚውን በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚኖረው የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ያውቃል። በኦሎምፒኩ ላይ አፍሪካን በመወከል ሁለት ሀገራት ብቻ ተሳታፊ የሚሆን ሲሆን የማጣርያው ውድድር አራት ዙሮች ይኖሩታል። በዚህም መሰረት :- 👉 የመጀመሪያ ዙር :- ሐምሌ 4 - 18/2015…
ሉሲዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?

የ2024ቱ የሴቶች ኦሎምፒክ ውድድር ማጣሪያ ጨዋታዎች የምድብ ድልድል ነገ ማክሰኞ ይፋ የሚደረግ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ሉሲዎቹ ) ቋት አራት ውስጥ ተካተዋል።

የምድብ ድልድሉ ቋት ምን ይመስላል ?

👉 ቋት አንድ :- ማሊ ፣ ጊኒ ፣ ሴራሊዮን እና ጊኒ ቢሳው

👉 ቋት ሁለት :- ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ አይቮሪኮስት እና ጋና

👉 ቋት ሶስት :- ቻድ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ፣ ኮንጎ ብራዛቪል እና ሩዋንዳ

👉 ቋት አራት :- #ኢትዮጵያ ፣ ሞዛምቢክ ፣ ናሚቢያ እና ዩጋንዳ ሆነው ተቀምጠዋል።

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ሉሲዎቹ ) ከቋት ሶስት ሀገራት ጋር በምድብ ድልድሉ ይገናኛሉ ተብሎ #ይጠበቃል

- ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ ፣ ናይጄሪያ ፣ ዛምቢያ ፣ ካሜሩን ፣ ቱኒዝያ እና ቦትስዋና በመጨረሻው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ባሳዩት አቋም ምክንያት የመጀመሪያው ዙር ማጣርያ የማይወዳደሩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴካፋ ውድድር ላይ የሀገር ለውጥ ተደረገ !

በጎረቤት ሀገር ኬንያ አዘጋጅነት ለማድረግ ታቅዶ የነበረው የሴካፋ ሴቶች ከ 18ዓመት በታች ውድድር የቦታ ለውጥ ተደርጎበት ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እንደሚደረግ አወዳዳሪው አካል በይፋ አሳውቋል።

ውድድሩ በበጀት መዘግየት ምክንያት ቀድሞ ተቀምጦለት ከነበረው ቀን ወደፊት ተገፍቶ ከ ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 1/2015 ዓ.ም ታንዛኒያ ቻማዚ ስታዲየም እንደሚደረግ ተገልጿል።

በውድድሩ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት አባል ሀገራት እንደሚሳተፉ ሲጠበቅ ኬንያ ከተማሪዎች ፈተና እና የትምህርት ቤት ውድድሮች ጋር በተያያዘ በውድድሩ እንደማትሳተፍ ተዘግቧል።

ተሳታፊ ሀገራት እነማን ናቸው ?

👉 #ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ቡሩንዲ ፣ ሩዋንዳ እና ዛንዚባር መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለሀገሬ 🇪🇹 ክብር ስል ሪከርዱን አስመልሳለሁ " አትሌት ለተሰንበት ግደይ 

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ 5000ሜትር ሪከርድ በኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ከሀገራችን ስለተወሰደበት መንገድ ስትናገር ቁጭት ውስጥ ሆና ነው።

የ 1500ሜትር የገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ ከዛም በቀናት ልዩነት የራሷ የ 5000ሜ ሪከርድ በፌዝ ኪፕዬጎን ሲሰበር መመልከት " የሀገር ክብር " እንደመነካት ነው ትላለች።

" የሚፈለገው ብር አይደለም ሁለቱ ሪከርድ ከሀገራችን ሲወጣ በጣም ተበሳጭቻለሁ " የምትለው ለተሰንበት ግደይ " ይህን ሪከርድ እንደማስመልስ ቃል እገባለሁ ለራሴ #ሳይሆን ለሀገሬ #ኢትዮጵያ ክብር ስል " ትላለች።

በስተመጨረሻም " ኢትዮጵያ ሀገራችን ሁሌም የወርቅ ሀገር እንድትሆንልኝ እመኛለሁ " ስትል ንግግሯን ትቋጫለች።

የአለም ሻምፒዮናው በነገው ዕለት ሲጀምር በ 10,000ሜትር ፍፃሜ የምትወዳደረው ለተሰንበት ግደይ እንደ ኦሪገን ውድድር ሁሉ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ ለማምጣት ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች የማጣሪያ ውድድር መካሄዱን ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ለሜቻ ግርማ ፣ አብርሃም ስሜ እና ጌትነት ዋለ ተወክላለች።

🇪🇹🇪🇹 ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የ1,500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር መካሄዱን ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ሂሩት መሸሻ ፣ ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ተወክላለች።

በውድድሩ ሁለተኛ ምድብ የምትገኘው ድርቤ ወልተጂ ውድድሯን ማድረግ ጀምራለች።

🇪🇹🇪🇹 ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የሴቶች 10,000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር መካሄዱን ጀምሯል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ለምለም ሀይሉ እና እጅጋየሁ ታዬ ተወክላለች።

🇪🇹🇪🇹 ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ !

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በ5000ሜ ይወክል የነበረው ጥላሁን ሀይሌ ዛሬ  ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።

አትሌቱ ለወራት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሃንጋሪ ቢያመራም  ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል።

በዚህም ምክንያት አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ከአሰልጣኙ ጋር ከተማከረ በኃላ ዛሬ ከሰዓት ወደ #ኢትዮጵያ ማቅናቱ ታውቋል።

አትሌቱ ከዝርዝሩ ወጪ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በውሳኔው ማዘኑን እና ቅሬታውን በማህበራዊ ሚዲያ ካሰማ በኃላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።

ይሄም አትሌቱ ዜግነቱን #ይቀይራል የሚል ቢሆንም አትሌቱ ዜግነቱ መቀየር ሀሳቡም #እንደሌለው እና በቀጣይ ጠንክሮ በመስራት ኢትዮጵያን ወክሎ አቅሙን ማሳየት እንደሚፈልግ ለናሽናል ስፖርት ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ

በ5000 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ 13ኛ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ዛሬ ከነጉዳቷ ወደ ውድድር የገባች ሲሆን የተሻለ መተጋገዝ ቢደረግ ኖሮ ጥሩ ውጤት ይገኝ እንደነበር ከሩጫው መጠናቀቅ በኃላ ለ " ልዩ ስፖርት " ድረገፅ በሰጠችው አጭር ቃለምልልስ ገልጻለች።

ጉዳፍ ፀጋይ ፦

" ትንሽ እግሬ ተልጦ ነበር ፤ ሁለት ቀን ልምምድ አልሰራሁም እዚ ሙቀትም ስለነበር ፤ እግሬ ተልጦ ነው ወደዛሬው ውድድር የገባሁት።

ይህም ቢሆን ግን እኔ ነኝ የመራሁት ዙሩን ማለት ይቻላል። የተነጋገርነው ነገር በየ600 ለመተጋገዝ ነው ግን ሁሉንም እኔ ስለመራሁት ፊት ተሁኖ ስቆይ መቋቋም ስለማይቻል እሱ ጋር ነው ያጠፋሁት እንጂ ጠብቄ ብሄድ ኖሮ የተሻለ ውጤት ይመጣ ነበር።

የነበረብኝ ጉዳት ስሜት አለው በእርግጥ ግን እራሴን ጠብቄ መሀል ሆኜ ብሄድ ኖሮ ጥሩ ነገር ይኖር ነበር።

ውድድሩ ተይዞ ነበር ፤ #እለፉ_እያልኳቸው ነበር ልጆቹን ግን ሊያግዙኝ አልቻሉም። "

ፎቶ፦ @tikvahethsport (Hungary, Budpest)

@tikvahethiopia
TIKVAH-SPORT
ሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ ተመረጠች ! በግብፅ ካይሮ እየተካሄደ በሚገኘው የካፍ ስራ አስፈፃሚ ስብስባ በቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫን የሚያስተናግዱ ሀገራት ይፋ ተደርገዋል። በቀጣይ በ 2025 የሚደረገውን የአህጉሪቱን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር #ሞሮኮ መመረጧ ተገልጿል። ሞሮኮ ውድድሩን ለማዘጋጀት ምን አቀርባ ነበር ? - በአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሁሉም ሀገራት የራሳቸው…
ምስራቅ አፍሪካዊያኑ የአፍሪካ ዋንጫ ያዘጋጃሉ !

የ 2027 36ኛው የአፍሪካ ዋንጫን በጋራ እንዲያስተናግዱ ካፍ ኬንያ ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳን መምረጡን ይፋ አድርጓል።

ሶስቱም ሀገራት ከዚህ ቀደም የአፍሪካ ዋንጫውን አዘጋጅተው የማያውቁ ሲሆኑ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

ሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዛምቢያ ፣ ቦትስዋና እና ሴኔጋልን በመብለጥ የአህጉሪቱን ትልቅ ውድድር ለማዘጋጀት የተሻለውን ድምፅ ማግኘት ችለዋል።

በአፍሪካ ዋንጫው ታሪክ ሶስት ሀገራት አንድን ውድድር ሲያዘጋጁ የ 36ኛው አፍሪካ ዋንጫ በታሪክ #ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

የአፍሪካ ዋንጫው ወደ ምስራቅ አፍሪካ ሲመጣ ከ እ.ኤ.አ 1976 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ለመጨረሻ ጊዜ ከምስራቅ አፍሪካ ውድድሩን ያዘጋጀችው ሀገራችን #ኢትዮጵያ ስትሆን ግብፅ የውድድሩ አሸናፊ እንደነበረች ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የ21ኛው ዙር ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ውድድር 16ሺ ተሳታፊዎችን በማካተት የፊታችን መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

የ 2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር ምዝገባ በተጀመረ የተወሰኑ ቀናት ውስጥ 10ሺ ቦታዎች የተሸጡ ሲሆን ቦታዎቹ ሊጠናቀቁ ጥቂት ቦታዎች ብቻ ቀርተዋል።

ሩጫን የአኗኗር ዘይቤ ማድረግ ራዕዩ አድርጎ እየሰራ ያለው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሌሎች ውድድሮቹ ላይ እንደሚያደርገው ሁሉ ለዚህም ውድድር የአራት ሳምንታት የልምምድ ፕሮግራም ባሳለፍነው እሁድ አስጀምሯል፡፡

በውድድሩ ከ1-3 የሚወጡ ተሳታፊዎች ልዩ ሽልማት ከውድድሩ አጋር ስንቅ ማልት የሚበረከትላቸው ሲሆን የዘንድሮ ውድድር በአትሌቲክስ ዘርፉም እንደወትሮው ሁሉ ለአዳዲስ እና ነባር ተወዳዳሪዎች ክፍት ይደረጋል።

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሚመጣው ሳምንት ላይ ምን ለማድረግ አስባችኋል?! 🤔

መጀመሪያ ከታች የተመረጡት የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በመገኘት ክፍያ በመፈፀም ለ2016 ሳፍሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ ይመዝገቡ! 🏃🏾‍♀️🏃🏾‍♀️🏃🏾‍♀️

🏦 ፒያሳ
🏦 አድዋ አደባባይ (መገናኛ)
🏦 ቦሌ ኖክ
🏦 ጣና (መርካቶ)
🏦 ልደታ
🏦 ቄራ
🏦 ንፋስ ስልክ
🏦 ሰሚት ሳፋሪ
🏦 መካኒሳ
🏦 ጦር ኃይሎች

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
3 ሳምንታት ብቻ!

Feel the Freedom, Own the Finish Line at the 2024 Safaricom Women first 5km 🫶

Book your place before it's too LATE!

See you on 17 May 2024📅

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
🌸 Get ready, ladies! March is your month!

Join us for the 2024 Safaricom Women First 5 km on 17 March 2024. Let's celebrate strength, empowerment, and sisterhood together! 🏃‍♀️💪

Book your place before it's too LATE!😉

☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #SafaricomEthiopia
ተመዘገብሽ⁉️🦻

🚨ምዝገባ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀሩት!

20 ድንቅ ዓመታት ከድንቅ ሴቶቻችን ጋር! 21ኛው ዙርስ?! አብረን አንሮጥም!?!

የ2016 ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ሩጫ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል!

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
ሴቶች! በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ለመድመቅ ዝግጁ?!

👩 የ2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይካሄዳል!

ሳያመልጣችሁ አሁኑኑ ተመዝገቡ!

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
ከህፃን እስከ አዋቂ የሆነች ጀግና ሴት የምትሳተፍበት ዉድድር።💪

👩 የ2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይካሄዳል።

ሳያመልጣችሁ አሁኑኑ ተመዝገቡ!

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
"ይህ መደበኛው የ5ኪ.ሜ. ውድድር ሳይሆን የጠዋት ካርኒቫል ነው።"

~ መሰረት ደፋር የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. አምባሳደር

👩 የ2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይካሄዳል።

ሳያመልጣችሁ አሁኑኑ ተመዝገቡ!

ነይ እንሩጥ!

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
ከህፃን እስከ አዋቂ የሆነች ጀግና ሴት የምትሳተፍበት ዉድድር።💪

👩 የ2016 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ይካሄዳል።

ሳያመልጣችሁ አሁኑኑ ተመዝገቡ!

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ከፈለጉ👇
☎️ +251116635757

ነይ እንሩጥ!

#GreatEthiopianRun #Ethiopia #ኢትዮጵያ #investinwomen #CheersTo21 #DashenBank #SafaricomEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹🇰🇷 እውነተኛ ቁርጠኝነት፣ ታላቅ ማስታወሻ! 🇪🇹🇰🇷

ታላቅ ክብር በደቡብ ኮሪያ፣ ሴኡል ማራቶን የኮሪያ ዘማች ወታደሮቻችንን ለማክበር በመጪው እሁድ በባዶ እግሩ ለሚሮጠው ኤርሚያስ አየለ። የተሳካ እና የማይረሳ ሩጫ እንዲሆንልህ ጥንካሬና ጉልበትን ዋናው ስፖርት ይመኛል።

Huge respect to Ermias Ayele who is running barefoot in the Seoul Marathon this Sunday to honor our Korean War Veterans! That's true dedication and a powerful tribute. Sending you strength and positive energy for a safe and memorable run.

#SeoulMarathon #Ethiopia #BarefootForHeroes
#ሴኡልማራቶን #ኢትዮጵያ
#የባዶእግርጀግኖች

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
🇰🇷🇪🇹 ባዶ እግር ለጀግኖች - Barefoot For Heroes 🇰🇷🇪🇹

በትናንትናው ዕለት #በሴኡልማራቶን ላይ በባዶ እግሩ ሮጦ የኮሪያ ዘማች ወታደሮቻችንን በደቡብ ኮሪያ ላከበረው አስደናቂው ኤርሚያስ አየለ ዋናው ስፖርት አድናቆቱን ይገልፃል። ቀላል ያልሆነውን በባዶ እግር መሮጥ ለማሳካት ያደረከው ቁርጠኝነት እውነተኛ ስፖርታዊ ጀግና መሆንህን ያሳየ ነው።

Standing ovation for the incredible Ermias Ayele who honored our troops in South Korea at the #SeoulMarathon this Sunday. Running barefoot is no easy feat, and your dedication to the cause is truly inspiring. Wanaw Sport typically champions the best in running, we celebrate your commitment and sacrifice. You're an embodiment of true sportsmanship!

#Wanaw #BarefootForHeroes
#Ethiopia #SeoulMarathon
#ዋናው #ባዶእግርለጀግኖች
#ኢትዮጵያ #ሴኡልማራቶን

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear