TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
የግራም ፖተር የቼልሲ ቀጣይነት ?

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ግራም ፖተር በውጤት ማጣት ላይ ሲገኙ ካለፉት አስራ ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት #ሁለቱን ብቻ ነው።

ቡድኑ በዝውውር መስኮቱ በርካታ ሚልዮኖቹን ቢያወጣም በደረጃ ሰንጠረዡ ዘጠነኛ ላይ ተቀምጠው ከሻምፒየንስ ሊግ ደረጃው #በአስር ነጥቦች ርቀው ይገኛሉ።

የክለቡ ደጋፊዎች አሰልጣኙ ለክለቡ ትክክለኛው ሀላፊ ነው ወይ የሚል ጥያቄ በማንሳት ላይ እንደሆኑ ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ዘግበዋል።

የክለቡ ከፍተኛ ባለስልጣናት በአሰልጣኝ ግራም ፖተር እምነት #ሲያሳድሩ በወራት ሳይሆን በዓመቱ ውስጥ በሚሰሯቸው ስራ #እንደሚገመገሙ ተነግሯል።

አሰልጣኝ ግራም ፖተር በዘንድሮው የውድድር ዓመት ቼልሲን በቀጣይ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሚያሳትፈውን ደረጃ ማስያዝ #ተቀዳሚው ስራቸው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe