TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ተጠናቀቀ | ማንችስተር ዩናይትድ 1 - 1 ፉልሀም
ካቫኒ ብራየን

• ቀዳሚዋን ጎል ያስቆጠረው ኤዲሰን ካቫኒ በሊጉ ያስቆጠረው አስረኛው ጎሉ ሆኖ ተመዝግቧል ።

• ዴቪድ ዴህያ ለመጀመሪያ ጊዜ #በሊጉ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ኤዲሰን ካቫኒ በውድድር አመቱ አስር እና ከዚያ በላይ ጎሎችን ለዩናይትድ ያስቆጠረው ሶስተኛው ተጫዋች ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዣቪ አዲስ ሪከርድ ለማስመዝገብ ተቃርቧል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ዛሬ ምሽት ከ ማዮርካ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ሽንፈት #ካልገጠማቸው አዲስ ታሪክ እንደሚያስመዘግቡ ተነግሯል።

ከሜዳቸው ውጪ ባለፉት አስራ ሰባት ጨዋታዎች #በሊጉ ያልተሸነፉት ባርሴሎናዎች በምሽቱ ጨዋታ አቻ ወይም ድል ከቀናቸው የዚነዲን ዚዳን ለአስራ ሰባት ተከታታይ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ሪከርድ እንደሚሰብሩ ይጠበቃል።

ባርሴሎናዎች በአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ስር ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው አስራ ሰባት ጨዋታዎች አስራ ሁለቱን ሲያሸንፉ በአምስቱ አቻ ተለያይተዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ነጥብ ሲጥል ቼልሲ ድል ቀንቶታል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በውድድር ዘመኑ ለአራተኛ ጊዜ አቻ ሲወጡ በሜዳቸው ከ ብራይተን ጋር ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

√ ሮቤርቶ ፊርሚንሆ ሁለት ጎሎች እና ዌብስተር በራሱ ላይ የሊቨርፑልን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ትሮሳርድ በአንፊልድ ሀትሪክ በመስራት የብራይተንን ሶስት ጎሎች ከመረብ አሳርፏል።

√ በአሰልጣኝ ግራም ፖተር የሚመራው ቼልሲ በኦባምያንግ እና ጋላግሀር ጎሎች ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማግኘት ችለዋል።

√ ትሮስራድ ከአስራ አራት ዓመታት በኋላ #በሊጉ #በአንፊልድ ሀትሪክ መስራት የቻለ ተጫዋች ሆኗል።

√ በሌሎች የሊጉ መርሐ ግብሮች #ኤቨርተን እና #ኒውካስትል ተጋጣሚዎቻቸውን ረተዋል።

√ ሊቨርፑል አስር ነጥቦችን በመሰብሰብ #ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ብራይተኖች በአስራ አራት ነጥቦች #አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

√ የለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአስራ ሶስት ነጥብ #አምስተኛ ላይ ሲቀመጡ በቀጣይ ከ ዎልቭስ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

√ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ #አርሰናል እንዲሁም ብራይተን ከ #ቶተንሀም ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#PremierLeague 🇬🇧

√ የቼልሲው ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ ለአምስተኛ ተከታታይ ጨዋታ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጧል።

√ ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በቋሚ አሰላለፍ በመጀመር የሰማያዊዎቹን ግብ የሚጠብቅ ይሆናል።

√ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ በኦልድ ትራፎርድ #በሊጉ በቋሚ አሰላለፍ ላይ ተካቷል።

በዛሬው የሊጉ መርሐ ግብር ምን ይጠብቃሉ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኡና ኤምሬ ስራቸውን በድል ጀምረዋል !

አዲሱ የአስቶን ቪላ አሰልጣኝ ኡና ኤምሬ ቀያይ ሴጣኖቹን 3ለ1 በመርታት ስራቸውን በድል ጀምረዋል።

√ ቤይሊ ፣ ራምሴ እና ሉካስ ዲኜ የአስቶን ቪላን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።

√ የማንችስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ሉክ ሾው አስቆጥሯል።

√ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች በውድድር ዓመቱ #በሊጉ አራተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

√ ቀያይ ሴጣኖቹ በሀያ ሶስት ነጥብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ አስራ አምስት ነጥቦችን የሰበሰቡት ቪላዎች አስራ አራተኛ ላይ ተቀምጠዋል።

√ በሌላ የሊጉ መርሐ ግብር ኒውካስትል ከሜዳው ውጪ በማሸነፍ በሀያ ሰባት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

√ በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፉልሀም እንዲሁም አስቶን ቪላ ከ ብራይተን የሚጫወቱ ይሆናል።

√ ማንችስተር ዩናይትድ እና አስቶን ቪላ በቀጣይ ሳምንት ሐሙስ በ #EFL_CUP ዳግም የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና አል ናስር !

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለአል ናስር የመጀመሪያ ጨዋታውን #በሊጉ የሚያደርግበት መርሐ ግብር የመግቢያ ትኬቶች ተሽጠው #መጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአዲሱ ክለቡ አል ናስር የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ አል ኢቲፋቅ ጋር የሚያደርግ ሲሆን የጨዋታው ስታዲየም መግቢያ ትኬቶች #ከአንድ ሰዓት ባነሰ ግዜ ውስጥ ተሸጠው እንደተጠናቀቁ ተነግሯል።

የአሰልጣኝ ሩዲ ጋርሽያ ስብስብ አል ናስር በሊጉ መርሐ ግብር ከአል ኢቲፋቅ ጋር ጥር 14/2015 ጨዋቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ወሳኝ ድል ተቀዳጅተዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጋብሬል ማርቲኔሊ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ በውድድር አመቱ ሁለተኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ብራዚላዊው ተጨዋች ጋብሬል ማርቲኔል ለአርሰናል ሰላሳ አራተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

አርሰናል ከስምንት ዓመታት በኋላ በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እየተመሩ ማንችስተር ሲቲን #በሊጉ ማሸነፍ ችለዋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

2️⃣ኛ :- አርሰናል ( 2️⃣0️⃣ ነጥብ )

3️⃣ኛ :- ማንችስተር ሲቲ ( 1️⃣8️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ማንችስተር ሲቲ ከ ብራይተን

ቅዳሜ - ቼልሲ ከ አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe